ጄኔራል ታደሰ ወረደ እንዲወገዱ ኢሳያስ አፈወርቂ አዟል ሲል ጄኔራል ፃድቃን መናገራቸው እያነጋገረ ነው።

ጀነራሉ እንዲወገዱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ማዘዛቸው ተሰማ!

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጀነራሉ እንዲወገዱ ትእዛዝ መስጠታቸው ተሰምቷል። ኢሳያስ ትእዛዙን የሰጡት ለሕወሓት እንደሆነም ተነግሯል። ይሀን ሚስጥር ያጋሩት ደግሞ ከወራት በፊት የፊልድ ማርሻሉ አማካሪ ሆነው ተሾሙ በሚል ስማቸው የተነሳው ጀነራል ጻድቃን ናቸው። ጀነራል ጻድቃን ከዚህ በተጨማሪ ስለ ፋኖ ኃይሎች እንቅስቃሴ ያልተጠበቀ አስተያየት ሰጥተዋል።

ጀነራል ታደሰ ወረደ የመወገድ አደጋ እንደተደቀነባቸው በአሁኑ ወቅት ከመቀሌ ሸሽተው አዲስ አበባ የሚገኙት ሌ/ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ገልጸዋል፡፡ ህወሓት እና ሻዕቢያ ጀምረውታል የተባለውን ጥምረት ለማጠናከር ጀነራል ታደሰ ወረደ እንቅፋት ሆነዋል የሚል ግምገማ እንዳላቸው ጀነራል ፃድቃን አዲስ በሰጡት ቃለ መጠይቅት ተናግረዋል፡፡

ጀነራሉ በወቅታዊ ጉዳይ ለኤንቢሲ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ መጠይቅት ሻዕቢያ ጀነራል ታደሰ ወረደ መወገድ አለባቸው የሚል ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል ብለዋል፡፡ በዚሁ ቅድመ ሁኔታ መሰረት ጀነራል ታደሰ ወረድን ማስወገድ ለህወሓት የተሰጠ የቤት ሥራ ነው ተብሏል፡፡

ተቀንጭቦ በተሰራጨው በዚህ ቃለ ምልልስ፣ ጀነራል ታደሰ በመፈንቅለ አስተዳደር የተባረሩትን ጌታቸው ረዳ የፕሬዝዳንትነት ሥልጣን ሲረከቡ የፈረሟቸውን ስምንት ነጥቦች አለመፈጸማቸውን ጀነራል ፃድቃን ገልጸዋል፡፡ በዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ዘንድ የፈረሙትን ነጥብ አንዱን አልፈጸሙም ያሉት ጀነራል፣ “ተፈናቃዮችን አልመለስም፣ ከውጭ ኃይሎች ጋር መገናኘቱን አላስቆመም” በማለት ከሰዋል፡፡

በህወሓት አቅራቢነት በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የተሾሙት ጀነራል ታደሰ፣ ህወሓት የጀመረውን የውጭ ግንኙነት ለማስቆም የቃል ኪዳን ሰነድ መፈረማቸው ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ ጀነራሉ ከተሾሙ በኋላ “ጽምዶ” በሚል የተጀመረውን የህወሓት እና የሻዕቢያ ግንኙነት፣ በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ ከሆነ እንደማይቃወሙ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ጀነራሉ በቃለ መጠይቁ የኤርትራ ባለሥልጣናት እንደ ህወሓት እና ፋኖ ያሉ የመንግሥት ተቀናቃኝ ኃይሎችን በማስተሳሰር ኢትዮጵያ የማተራመስ እንቅስቃሴ ውስጥ ገብተዋል ብለዋል፡፡ ህወሓት በግልት ከኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አስተዳደረ ጋር አብሯል ያሉት ጀነራሉ፣ የጀመሩት ግንኙነት ሕዝባዊ ተቀባይነት እንዳገኝ እየራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የሻዕቢያ እና የህወሓትን ጥምረት ለትግራይ ሕዝብ ለማሳመን የሚቀርበው ምክንያት “ወልቃይትን ለማስመለስ ከኢሳያስ ጋር እንተባበራለን” በሚል መሆኑን ጀነራሉ ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም “ሕዝብ ለሕዝብ ቢገናኝ ምን ችግር አለው” የሚል ሀሳብ በማንሳት ግንኙነቱ በሕዝብ ዘንድ ተቃባይነት እንዲያገኝ እየሞከሩ ነው ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ እንደ ጀነራል ፃድቃን ግምግማ የትግራይ ሕዝብ የህወሓትን “ኮርኳሪ” ማደናገሪያ ሀሳብ አይቀበልም ብለዋል፡፡ ህወሓት ከሰሞኑ ከ2 ሺህ በላይ የሕዝብ ተወካይ ናቸው ያላቸውን ካድሬዎች ሰብስቦ ባካሄደው ስብሰባ ከኤርትራ ጋር በሕዝብ ለሕዝብ ስም የተጀመረው ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡