Blog Archives

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት ትኩሳት ሲሆን የታየበት አጋጣሚ በርካታ ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱ ይህ ይጎድለዋል፣ እንዲህ ቢደረግ ወይም አንዳንድ ነገር ቢካተትበት በሚል የሚነሱ ጥያቄዎች ከባድ ተቃርኖ ሲገጥማቸው ማየት የተለመደ ነው፡፡ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ወይም ለውጥ በተነሳ ቁጥር፣ ‹‹ሕገ መንግሥቱ የሚነካው በመቃብራችን ላይ ነው፤›› የሚል ጠንካራ አፀፋ ሲሰጥ መስማት የተለመደ ሆኖ ነው የኖረው፡፡ ከሰሞኑም ቢሆን ይህን መሰሉ አተካሮ የተደገመ ይመስላል፡፡ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ያቀረበው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጥናት መነጋገሪያ መሆኑን ተከትሎ፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ጠንካራ ተቃውሞ ማሰማቱ የዚሁ ነፀብራቅ ሆኖ ነበር የታየው፡፡ https://www.ethiopianreporter.com/119227/ አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሀድያ ዞን ደመወዝ እየተከፈለ ያለው ለሆሳህና ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች ብቻ መሆኑ ተነገረ

በሀድያ ዞን ደመወዝ እየተከፈለ ያለው ለሆሳህና ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች ብቻ መሆኑ ተነገረ በደቡብ ክልል ሀድያ ዞን 17 ወረዳዎችና ሦስት የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ፣ ደመወዝ እየተከፈላቸው ያሉት ሆሳህና ከተማ ውስጥ ያሉ የመንግሥት ሠራተኞች ብቻ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡ በሀድያ ዞን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት የመንግሥት ሠራተኞች እንደተናገሩት፣ በዞኑ በተለያዩ መንግሥት መሥሪያ ቤቶች… https://www.ethiopianreporter.com/119168/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ድጋፍ ፕሮግራም የ15 ሚሊዮን ፓውንድ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ

የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ድጋፍ ፕሮግራም የ15 ሚሊዮን ፓውንድ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ በብሪቲሽ ካውንስል በሚመራ የለጋሾች ጥምረት አማካይነት ተግባራዊ እየተደረገ ያለው ሁለተኛው የሲቪል ማኅበራት ድጋፍ ፕሮግራም፣ ባለፉት አምስት ዓመታት የ15 ሚሊዮን ፓውንድ ድጋፍ ኮንትራቶችን እንደፈረመ አስታወቀ፡፡ የተለያዩ የቴክኒካል፣ የተቋም ግንባታና የፋይናንስ ድጋፎችን 173 ለሚሆኑ በኢትዮጵያ የሚሠሩ የሲቪል… https://www.ethiopianreporter.com/119169/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መንግሥት በፈጠረው ችግር አርሶ አደሩ ማዳበሪያ በእጥፍ ዋጋ ለመግዛት መገደዱን ገለጸ

መንግሥት በፈጠረው ችግር አርሶ አደሩ ማዳበሪያ በእጥፍ ዋጋ ለመግዛት መገደዱን ገለጸ መንግሥት በፈጠረው ችግር ምክንያት የ2015/16 ዓ.ም. የምርት ዘመን ተፈላጊውን የአፈር ማዳበሪያ በክልሎች በተለይም በአማራ ክልል በወቅቱ ባለመሰራጨቱ ግብዓቱን ከነጋዴዎች በዕጥፍ ዋጋ ለመግዛት መገደዳቸውን አርሶ አደሮች ተናገሩ፡፡ በአማራ ክልል ማዳበሪያ በአግባቡ አልደረሰንም ያሉ አርሶ አደሮች ከሰሞኑ… https://www.ethiopianreporter.com/119174/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከተሽከርካሪዎች የሚወጡ በካይ ጋዞችን መቆጣጠር የሚያስችል ሕግ ሊወጣ ነው

ከተሽከርካሪዎች የሚወጡ በካይ ጋዞችን መቆጣጠር የሚያስችል ሕግ ሊወጣ ነው በአበበ ፍቅር ከተሽከርካሪዎች የሚወጡ በካይ ጋዞችን መቆጣጠር የሚያስችል ሕግ ሊወጣ መሆኑን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ ሕግ ካልወጣላቸው ከአሮጌ ተሽከርካሪዎች የሚወጣ ጭስ እስካሁን ድረስ በትክክል የሚታወቅ ሕግ የሌላቸው በመሆኑ፣ ባለሥልጣኑ ሕግ ለማውጣት ሙከራ… https://www.ethiopianreporter.com/119172/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መንግሥት ያፈረሰውን የሸማቾች ጥበቃና ውድድር ባለሥልጣንን መልሶ እንዲያቋቁም ተጠየቀ

መንግሥት ያፈረሰውን የሸማቾች ጥበቃና ውድድር ባለሥልጣንን መልሶ እንዲያቋቁም ተጠየቀ በአዲሱ የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባርን በሚወስነው አዋጅ እንዲፈርስ የተደረገው የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣንን፣ መንግሥት መልሶ እንዲያቋቁመው ጥያቄ ቀረበ፡፡ በመስከረም ወር በ2014 ዓ.ም.  የወጣው አዋጅ ባለሥልጣኑን አፍርሶ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሥር በዴስክ ደረጃ ያዋቀረው.. https://www.ethiopianreporter.com/119177/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎትና ፈቃድ ክፍያን ለመወሰን ረቂቅ መመርያ ተዘጋጀ

የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎትና ፈቃድ ክፍያን ለመወሰን ረቂቅ መመርያ ተዘጋጀ አዳዲስ የክፍያ ተመኖች ግልጽ ማብራሪያ ሊቀመጥላቸው እንደሚገባ ጥያቄ ቀርቧል በኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን የተረቀቀ የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎትና የፈቃድ ክፍያን ለመወሰን ረቂቅ መመርያ ተዘጋጀ፡፡ መመርያው ከኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ፣ ከሬዲዮ ፍሪኩዌንሲ፣ ከቁጥር አስተዳደርና ምደባ፣ እንዲሁም ከሬዲዮ ኮሙዩኒኬሽን፣ ከቴሌኮሙዩኒኬሽን መሣሪያዎች የቴክኒክ… https://www.ethiopianreporter.com/119180/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

‹‹አቅም ያላቸው ጠንካራ ፓርቲዎች ለመገንባት አልታደልንም›› ዲማ ነገዎ (ዶ/ር)፣ አንጋፋ ፖለቲከኛ

‹‹አቅም ያላቸው ጠንካራ ፓርቲዎች ለመገንባት አልታደልንም›› ዲማ ነገዎ (ዶ/ር)፣ አንጋፋ ፖለቲከኛ ዲማ ነገዎ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ለግማሽ ምዕተ ዓመት ያህል የፖለቲካ ትግል ውስጥ ነበሩ። ከአምስት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ በተደረገው የመንግሥት ለውጥ በስደት ከሚኖሩበት አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት፣ ይመሩት የነበረውን የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር… https://www.ethiopianreporter.com/119191/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መንግሥት ለእምነት ተቋማትና ለምዕመኖቻቸው ጥበቃ እንዲያደርግ ተጠየቀ

መንግሥት ለእምነት ተቋማትና ለምዕመኖቻቸው ጥበቃ እንዲያደርግ ተጠየቀ የፖለቲካ ፓርቲዎች በእምነት ተቋማት ላይ የሚወሰድ ዕርምጃ አደጋው የከፋ ነው አሉ የከተማውንና የአገሪቱን ሰላምና ደኅንነት ለማስከበር የተጀመረው ሕግ የማስከበር ሥራ ይቀጥላል›› የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በዮናስ አማረና በኢዮብ ትኩዬ በአዲስ አበባ ከተማ በታላቁ የአንዋር መስጊድ… https://www.ethiopianreporter.com/119194/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የፀጥታ አካላት ሞት ከሚያስከትል የኃይል ዕርምጃ እንዲቆጠቡ ኢሰመኮ አሳሰበ

የፀጥታ አካላት ሞት ከሚያስከትል የኃይል ዕርምጃ  እንዲቆጠቡ ኢሰመኮ አሳሰበ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የመንግሥት የፀጥታ አካላት በማንኛውም ሕዝባዊና ሃይማኖታዊ ሠልፎች እንዲሁም ሌሎች ስብስባዎች፣ ተመጣጣኝ ካልሆነና ሞት ከሚያስከትል የኃይል ዕርምጃ መውሰድ እንዲቆጠቡ አሳሰበ፡፡ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የመንግሥት የፀጥታ አካላት አላስፈላጊና ተመጣጣኝ.. https://www.ethiopianreporter.com/119195/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

” የፖለቲካ ሥርዓቱ እስካልተረጋጋ ድረስ የኢኮኖሚ ዕድገት ሊኖር አይችልም ” – ዶ/ር ዲማ ነጋዎ

” የፖለቲካ ሥርዓቱ እስካልተረጋጋ ድረስ የኢኮኖሚ ዕድገት ሊኖር አይችልም ” – ዶ/ር ዲማ ነጋዎ ሪፖርተር ጋዜጣ ዛሬ ባሰራጨው ዕትሙ ፤ በ6ኛው አገራዊ ምርጫ በግል ተወዳድረው ያሸነፉት፤ የሕ/ተ/ ም/ቤት አባል እንዲሁም በአሁኑ ወቅት የም/ቤቱ የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ዲማ ነጋዎን ቃለ ምልልስ አድርጓል። በዚህ ቃለምልልስ ፥ ከ120 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ እንዳለ በሚነገርባት ኢትዮጵያ ውስጥ፤ ለዚህ ሕዝብ የሚመጥን ወጥ የሆኑ ጠንካራ አገራዊ  ፓርቲዎች መመሥረት  ለምን አልተቻለም ? ሲሉ ተጠይቀው ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል። ዶ/ር ዲማ ነጋዎ ፦ ” አንደኛው ግለኝነት ነው፡፡ እስካሁን ባለኝ አረዳድ የኢትዮጵያ ሕዝብ በቡድን መሥራት ላይ ክፍተት አለበት፡፡ ለዚህ ማሳያ አንድ ምሳሌ ልጥቀስልህ፡፡ በኢትዮጵያ ስፖርት ውስጥ የቡድን ስፖርትና የግል ስፖርት አለ፡፡ እኛ እንደ አገር የቡድን ስፖርት አሸንፈን አናውቅም፡፡ ነገር ግን በግል በሚደረገው የሩጫ ስፖርት ካየህ ልህቀት አለን፡፡ ወደ ፖለቲካ ስንመጣ ግን መሆን የነበረበት የቡድን ስፖርት ነበር፡፡ በቡድን አብሮ መሥራትና ተቀናጅቶ መንቀሳቀስ እንጂ፣ በቡድን ውስጥ እኔ ያልኩት ብቻ ከሆነ ግን አይሠራም፡፡  ሁሉም የሚያነሳው ጉዳይ ወደ አንድ መጥቶ ነው በጋራ የሚወሰነው። በእኛ ፖለቲካ ውስጥ የምታየው እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን የሚለው ነገር ትልቅ ቦታ አለው፡፡ በፖለቲካ ደግሞ ግለሰቦች በምኞት የሚፈልጓትን ኢትዮጵያ ብቻ የሚቀርፁበት ሁኔታ ይታያል ፤ ነገር ግን የፖለቲካ ሥራ የሚከናወነው አብዛኛው ሕዝብ ምን እንደሚፈልግ ተመሥርቶ መሆን አለበት፡፡ ማንኛውም ኅብረተሰብ ውስጥ ዳርና ዳር የቆሙ ሰዎች አሉ፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዜጎችን ለውጭ ገበያ ዝግጁ የሚያደርጉ 77 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች መለየታቸው ተነገረ

ዜጎችን ለውጭ ገበያ ዝግጁ የሚያደርጉ 77 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች መለየታቸው ተነገረ በአበበ ፍቅር ለውጭ ገበያ ዝግጁ የሚያደርጉ 77 የቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ኮሌጆች ተለይተው ሥልጠና በመስጠት ላይ መሆናቸው ተገለጸ፡፡ በየትኛውም የሥራ ዓይነት የሚሰማሩ ዜጎች ክህሎት መር የሥራ ሥምሪት እንዲያገኙ በማሰብ፣ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ተለይተው  በዓለም የገበያ ፍላጎት ላይ… https://www.ethiopianreporter.com/119063/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢንቨስተሮች አደጋ ሲገጥማቸው ድጋፍ ማድረግ የሚያስችለው መመርያ ተሻረ

ኢንቨስተሮች አደጋ ሲገጥማቸው ድጋፍ ማድረግ የሚያስችለው መመርያ ተሻረ በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ አደጋዎች በኢንቨስተሮች ንብረት ላይ አደጋ ቢከሰት፣ ከመንግሥት ድጋፍ በሚያገኙበት ሁኔታ ላይ ተደንግጎ የነበረውን መመርያ የገንዘብ ሚኒስቴር ሻረው፡፡ በተለያዩ ዘርፎች ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን አፍስሰው እየሠሩ ያሉ ኢንቨስተሮች በንብረቶቻቸው ላይ አደጋ ቢከሰት፣ በርካታ ድጋፎችን… https://www.ethiopianreporter.com/119065/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ተቋማት በቅንጅት ለመሥራት በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት እየሠሩ አለመሆኑ ተገለጸ

ተቋማት በቅንጅት ለመሥራት በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት እየሠሩ አለመሆኑ ተገለጸ ተቋማት በቅንጅት ለመሥራት በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት ኃላፊነታቸውን እየተወጡ አለመሆናቸውን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ አስታወቀ፡፡ ቢሮው ይህንን ያለው ከዘርፉ ተቋማት ጋር በቅንጅት ከመሥራት አንፃር የ2015 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት አፈጸጸምን በተመለከተ፣ ግንቦት 21… https://www.ethiopianreporter.com/119067/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መንግሥት የግብርና ዘርፎች ላይ ታክስ ለመጀመር ዕቅድ እንዳለው ተገለጸ

መንግሥት የግብርና ዘርፎች ላይ ታክስ ለመጀመር ዕቅድ እንዳለው ተገለጸ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰማራበትና ትልቁን የአገሪቱን ኢኮኖሚ ድርሻ የሚይዘው የግብርና ዘርፍ ላይ ግብር ለመጀመር ዕቅድ እንዳለ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ፡፡ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት ‹‹በአገሪቱ በጣም ብዙ የግብርና ምርትና ልውውጥ ይካሄዳል፣ ነገር ግን የግብርና ታክስ… https://www.ethiopianreporter.com/119069/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የተሰማሩ ደላሎችን መቆጣጠር ፈተና እንደሆነበት የአማራ ክልል አስታወቀ

በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የተሰማሩ ደላሎችን መቆጣጠር ፈተና እንደሆነበት የአማራ ክልል አስታወቀ በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የተሰማሩ ዋና ዋና ደላሎችን በቁጥጥር ሥር በማዋል ለሚፈጽሙት ወንጀል ቅጣት እንዲያገኙ ማድረግ ፈተና እንደሆነበት፣ የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ አስታወቀ፡፡ ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ ወደ ውጭ አገር የሚልኩና ድንበር የሚያሻግሩ በሰዎች ንግድ ላይ የተሰማሩ… https://www.ethiopianreporter.com/119071/
Posted in Ethiopian News

የኮስሞ ትሬዲንግ አክሲዮኖች የተሸጡት በማስፈራራትና በማስገደድ መሆኑን በመግለጽ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጠ

የኮስሞ ትሬዲንግ አክሲዮኖች የተሸጡት በማስፈራራትና በማስገደድ መሆኑን በመግለጽ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጠ የአክሲዮኖቹ ሽያጭ ውል እንዲፈርስ ውሳኔ ተሰጥቷል ከሦስት ዓመታት በፊት ታኅሳስ 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ጄጄ ፕሮፐርቲ ማኔጀመንት ኃላፊነቱ የተወሰነ ግል ማኅበርና ወ/ሪት አዜብ ምሕረተ አብ የተባሉ ከሳሾች፣ ኮስሞ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ ግል ማኅበርን 19,900 የአክሲዮን… https://www.ethiopianreporter.com/119074/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት 15 አመራሮችና ሠራተኞች ከሥራ መሰናበታቸው ተገለጸ

የአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አገልግሎት 15 አመራሮችና ሠራተኞች ከሥራ መሰናበታቸው ተገለጸ የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብልሹ ድርጊት ውስጥ ተሳትፈው የተገኙ 15 አመራሮችና ሠራተኞችን ከሥራ ማሰናበቱን አስታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አግልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ገበየሁ ዲቃሳ (ዶ.ር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት አቅርቦት… https://www.ethiopianreporter.com/119076/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መቀሌ በሚገኙ ሦስት የነዳጅ ማደያዎች የድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ መሆን ጀመረ

መቀሌ በሚገኙ ሦስት የነዳጅ ማደያዎች የድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ መሆን ጀመረ ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መልስ በትግራይ ክልል ለመጀመርያ ጊዜ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ የነዳጅ ግብይት ትግበራ በመቀሌ ከተማ በሚገኙ ሦስት የነዳጅ ማደያዎች ላይ ተግባራዊ መሆን እንደጀመረ ታወቀ፡፡ በመላው አገሪቱ ከተጀመረ አንድ ዓመት ሊሞላው የአንድ ወር ዕድሜ ብቻ የቀረው… https://www.ethiopianreporter.com/119081/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ በሽግግር ፍትሕና ተጠያቂነት ላይ ለመነጋገር ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው

የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ በሽግግር ፍትሕና ተጠያቂነት ላይ ለመነጋገር ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር (አምባሳደር)፣ የሽግግር ፍትሕና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚደረጉ ጥረቶች የደረሱበትን ደረጃ በሚመለከት ለመነጋገር ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው፡፡ ከረቡዕ ከዛሬ ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ለሰባት ቀናት በጂቡቲና በኢትዮጵያ ጉብኝት የሚደርጉት… https://www.ethiopianreporter.com/119087/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለውጭ ገበያ ሳይላክ ለቀረ ቡና ላኪዎች ታክስ እስከ ወለዱ እንዲከፍሉ ተወሰነ

ለውጭ ገበያ ሳይላክ ለቀረ ቡና ላኪዎች ታክስ እስከ ወለዱ እንዲከፍሉ ተወሰነ ገቢ ሰብሳቢ ተቋማት ቡና ላኪዎች የሚያቀርቧቸውን ሰነዶች መርምረው ወደ ውጭ ሳይላክ የቀረ ቡና መኖሩን ካረጋገጡ፣ ሊከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ገዥው ወይም ላኪው ከእነ ወለዱ እንዲከፍሉ እንዲያደርጉ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሪፖርተር የተመለከተውና በገንዘብ ሚኒስትር… https://www.ethiopianreporter.com/119090/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አርሶ አደሮች የቲማቲም ማሳቸውን ወደ በጋ ስንዴ እንዲቀይሩ መገደዳቸውን ተናገሩ

አርሶ አደሮች የቲማቲም ማሳቸውን ወደ በጋ ስንዴ እንዲቀይሩ መገደዳቸውን ተናገሩ ‹‹የአመለካከት ችግር ተፈጥሮ ካልሆነ በስተቀር ስንዴ በሌሎች ምርቶች ላይ ተፅዕኖ አላሳደረም›› የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ አርሶ አደሮች፣ የቲማቲምና የአትክልት ማሳቸውን ወደ በጋ መስኖ ስንዴ እንዲቀይሩ መገደዳቸውን ተናገሩ፡፡ ስማቸው እንዳይገለጽ… https://www.ethiopianreporter.com/119093/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

እስረኞችን ለማስለቀቅ በተሰነዘረ ጥቃት አራት ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

በበቆጂ ከተማ እስረኞችን ለማስለቀቅ በተሰነዘረ ጥቃት አራት ሰዎች መገደላቸው ተሰማ   የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በየትኛውም አካባቢ ጥቃት የለም ሲል አስተባብሏል በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በቆጂ ከተማ ማንነታቸው በግልጽ ያልታወቁ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት አራት ስዎችን ሲገድሉ በፖሊስ ጣቢያ የነበሩ የተወሰኑ እስረኞችን ማስለቀቃቸው ተሰማ። ሪፖርተር ያነጋገራቸው የዓይን እማኞች… https://www.ethiopianreporter.com/118877/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በትግራይ ክልል ከመፈናቀልና ከዕርዳታ ጋር በተያያዘ በተለያዩ አካባቢዎች ሰላማዊ ሠልፎች ተደረጉ

በትግራይ ክልል ከመፈናቀልና ከዕርዳታ ጋር በተያያዘ በተለያዩ አካባቢዎች ሰላማዊ ሠልፎች ተደረጉ በዳንኤል ንጉሤ በትግራይ ክልል ላለፉት አራት ወራት ዕርዳታ ተቋርጦብናል ያሉ ተፈናቃዮች፣ ትናንት ማክሰኞ ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም. በተለያዩ አካባቢዎች ሰላማዊ ሠልፎች አደረጉ። በሰላማዊ ሠልፎቹ የተሳተፉት ተፈናቃዮች ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ዕርዳታ በመቋረጡ ሕፃናት፣ እናቶችና አዛውንቶች በሕመምና… https://www.ethiopianreporter.com/118868/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሓት የምርጫ ቦርድ ውሳኔን በመቃወም ቅሬታውን ለአፍሪካ ኅብረት አስገባ

ሕወሓት የምርጫ ቦርድ ውሳኔን በመቃወም ቅሬታውን ለአፍሪካ ኅብረት አስገባ   የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የሕጋዊ ሰውነት ጥያቄ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃወም፣ ቅሬታውን ለአፍሪካ ኅብረት ማስገባቱን ሊቀመንበሩ ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ተናገሩ። የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ሰኞ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም…. https://www.ethiopianreporter.com/118880/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዩኒቨርሲቲዎች በዋጋ ግሽበት ምክንያት ተማሪዎቻቸውን መመገብ በማይችሉበት ደረጃ ላይ መሆናቸው ተነገረ

ዩኒቨርሲቲዎች በዋጋ ግሽበት ምክንያት ተማሪዎቻቸውን መመገብ በማይችሉበት ደረጃ ላይ መሆናቸው ተነገረ በተማሪ 22 ብር ቢመደብም ወጪው ግን 89 ብር መድረሱ ተጠቁሟል ለተማሪ ምገባ የሚመደብላቸው ገንዘብ በዋጋ ግሽበት ምክንያት ዝቅተኛ እየሆነ በመምጣቱ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች ምግብ ማቅረብ ላይ እየተቸገሩ እንደሆነ ተገለጸ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊዎች በትላንትናው ዕለት ግንቦት… https://www.ethiopianreporter.com/118874/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሕዝቡን ኑሮ ማቅለል እንጂ ማክበድ ተገቢ አይደለም!

መንግሥት አገር ሲያስተዳድር ለበርካታ ወጪዎቹ ገንዘብ ስለሚያስፈልጉት አስተማማኝ የገቢ ምንጮች ሊኖሩት ይገባል፡፡ በጀት ሲይዝም ሆነ ወጪዎቹን ሲያቅድ ጠንቃቃ መሆን ይኖርበታል፡፡ ወቅቱ ለመጪው ዓመት በጀት ረቂቅ ማቅረቢያ ስለሆነ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ መነጋገር ይገባል፡፡ መንግሥት ያለፈው ዓመት በጀቱ እንዳልበቃው፣ በርካታ ፕሮጀክቶችን ለመሰረዝ መገደዱን፣ በአንዳንድ ክልሎች ለመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ መክፈል እንዳቃተውና የመሳሰሉ የችግር ወሬዎች በስፋት ተሰምተዋል፡፡ መንግሥት የገንዘብ ችግር አጋጥሞታል ሲባል ጠቃሚ ምክረ ሐሳቦችን ማቅረብ ተገቢ ነው፡፡ መንግሥት በተቻለ መጠን አላስፈላጊ ወጪዎችን መቀነስ አለበት፡፡ ከወረዳ እስከ ፌዴራል መንግሥት ድረስ የሚከናወኑ የቅንጦት ግዥዎችና አንገብጋቢ ያልሆኑ ፕሮጀክቶች መቆም አለባቸው፡፡ በጥናት ላይ የተመሠረቱ አዋጭ የገቢ ምንጮችን ማስፋት ይጠበቅበታል፡፡ በከባድ የኑሮ ውድነት እየተደቆሰ ያለውን ሕዝብ ካለችው ከእጅ ወደ አፍ ገቢ ላይ፣ በተለያዩ መንገዶች ጫና በመፍጠር የተለያዩ የግብር ዓይነቶችን መቆለል ተገቢ አይደለም፡፡ መንግሥት የሕዝቡን ኑሮ ማክበድ አቁሞ ጤናማና ውጤታማ የገቢ ምንጮች ላይ ያተኩር፡፡ እየተለወጠ ካለው የዓለም ሥርዓት ጋር አብሮ መራመድ የግድ ነው፣ መሆንም አለበት፡፡ ከተለያዩ አገሮችም ሆነ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በሚኖር የሁለትዮሽም ሆነ የባለብዙ ግንኙነት፣ የራስን የቤት ሥራ በሚገባ አጠናቆ መነጋገርም ሆነ መደራደር ከመንግሥት ከሚጠበቁ ሥራዎች መካከል ይጠቀሳል፡፡ ለዚህ ደግሞ በተለያዩ መስኮች በተመሰከረላቸው ብቁ ባለሙያዎች መታገዝ አስፈላጊ ነው፡፡ ፖሊሲዎችም ሆኑ ስትራቴጂዎች ወቅቱን የዋጁ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጥቂቶችን ፍላጎት ከማስፈጸም በላይ አገራዊ ጥቅም ሊከበር የሚችለው፣ ከማናቸውም ተደራዳሪ አካላት ጋር በብቃት ጥቅምን ለማስከበር የሚያስችል ክህሎት ሲኖር ነው፡፡ መንግሥት የበጀት ጉድለትን
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሲሚንቶ በዲጂታል መንገድ ለማገበያየት የክፍያ አማራጮች ልየታ ተጀመረ

ሲሚንቶ በዲጂታል መንገድ ለማገበያየት የክፍያ አማራጮች ልየታ ተጀመረ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሲሚንቶ ግብይትን በዲጂታል መንገድ ለማከናወን ከፋብሪካዎች ጋር ውይይቶችንና የክፍያ አማራጮች ልየታ እያደረገ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የአገር ውስጥ ንግድና ሸማቾች ጥበቃ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መስከረም ባህሩ፣ የሲሚንቶ ግብይት… https://www.ethiopianreporter.com/118857/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የማዕድን ነዳጅና ባዮፊዩል ኮርፖሬሽን ዘረፋ እንደተፈጸመበት ተገለጸ

የማዕድን ነዳጅና ባዮፊዩል ኮርፖሬሽን ዘረፋ እንደተፈጸመበት ተገለጸ የኢትዮጵያ ማዕድን፣ ነዳጅና ባዮፊዩል ኮርፖሬሽን ዋና መሥሪያ ቤት ዘረፋ እንደተፈጸመበት የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡ ዘረፋው የተካሄደው ባለፈው ሳምንት እንደሆነ የተናገሩት ምንጮቹ፣ በዋና መሥሪያ ቤቱ ውስጥ የሚገኙ የከበሩ ማዕድናትና የድርጅቱ ንብረቶች እንደተዘረፉ ተናግረዋል፡፡ የኮርፖሬሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት 22… https://www.ethiopianreporter.com/118856/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የቅድመ ምርመራ የተደረገላቸው 133 ሺሕ የቁም እንስሳት ዕርድ ውድቅ ተደረገ

የቅድመ ምርመራ የተደረገላቸው 133 ሺሕ የቁም እንስሳት ዕርድ ውድቅ ተደረገ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ውስጥ በአገር አቀፍ ደረጃ በተደረገው የቅድመ ዕርድ ምርመራ ከ133 ሺሕ በላይ የቁም እንስሳት ተገቢውን ደረጃ ሳያሟሉ እንደተገኙ ታወቀ፡፡ በእንስሳት ልየታና ምዝገባ ሥርዓት ሥር የሚያልፉ ለኤክስፖርት የሚቀርቡ እንስሳቶችን የቅድመና ድኅረ ዕርድ ምርመራ… https://www.ethiopianreporter.com/118860/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢንቨስተሮች በትልልቅ ፕሮጀክቶች ላይ እንዲሳተፉ መንግሥት ቢሮክራሲውን ዘመናዊ ማድረግ እንዳለበት ተገለጸ

ኢንቨስተሮች በትልልቅ ፕሮጀክቶች ላይ እንዲሳተፉ መንግሥት ቢሮክራሲውን ዘመናዊ ማድረግ እንዳለበት ተገለጸ የውጭ ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው መንግሥት ክፍት ባደረጋቸው የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሳተፉ ለማድረግ፣ የመንግሥት ትኩረት ቢሮክራሲውን ዘመናዊ ማድረግ ላይ እንደሆነ ተገለጸ፡፡  በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አባቢ ደምሴ (አምባሳደር) ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ የግሉ ዘርፍ… https://www.ethiopianreporter.com/118862/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የትምህርት ማስረጃቸው እንዲጣራ ከተደረገባቸው 225 ሠራተኞች ውስጥ 40 በመቶዎቹ ሕገወጥ መሆናቸው ተገለጸ

የትምህርት ማስረጃቸው እንዲጣራ ከተደረገባቸው 225 ሠራተኞች ውስጥ 40 በመቶዎቹ ሕገወጥ መሆናቸው ተገለጸ የትምህርት ሚኒስትሩ 4.3 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው አሉ ቀጣሪ መሥሪያ ቤቶች ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት የ225 ተቀጣሪ ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃዎች ትክክለኛነት ሲመረመር፣ 40 በመቶ የሚሆኑት (90 ማስረጃዎች) በሕገወጥ መንገድ የተገኙ መሆናቸው ተገለጸ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ… https://www.ethiopianreporter.com/118865/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝን በቴሌ ብር እንዲከፈል መታቀዱ ተገለጸ

የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝን በቴሌ ብር እንዲከፈል መታቀዱ ተገለጸ በባንኮች በኩል ተከፋይ የሚሆነውን የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ወደ ቴሌ ብር የሞባይል ገንዘብ ሥርዓት ለማሸጋገር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የተቋማቸውን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ… https://www.ethiopianreporter.com/118760/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ ጉዳትና ኪሳራ ማድረሱን መንግሥት ይፋ አደረገ

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ ጉዳትና ኪሳራ ማድረሱን መንግሥት ይፋ አደረገ  ሦስት ሚሊዮን ነዋሪዎች የከፋ ድህነት ውስጥ ናቸው ተብሏል ከአጠቃላይ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት መጎዳታቸው ተገልጿል  በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለይም ማዕከሉን በትግራይ ክልል አድርጎ ለሁለት ዓመታት በተካሄደውና በሌሎች የተወሰኑ አካባቢዎች በነበረው ጦርነት፣ ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ… https://www.ethiopianreporter.com/118763/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በቢሾፍቱ ስለተገደሉ የፖሊስ አባላት ጉዳይ ምርመራ መጀመሩን የከተማው ከንቲባ አስታወቁ

በቢሾፍቱ ስለተገደሉ የፖሊስ አባላት ጉዳይ ምርመራ መጀመሩን የከተማው ከንቲባ አስታወቁ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ በታጣቂዎች ስለተገደሉት አራት የፖሊስ አባላት ጉዳይ ምርመራ መጀመሩን፣ የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ በታጠቁ ኃይሎች ስለተገደሉት የፖሊስ አባላት ምርመራ እየተደረገ መሆኑን፣ የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ ዓለማሁ አሰፋ ተናግረዋል፡፡ በታጣቂዎች… https://www.ethiopianreporter.com/118634/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

‹‹የኢትዮጵያ ሚና ለሱዳን መንግሥት አዎንታዊና ደጋፊ ነው›› የሱዳን የሽግግር መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ልዩ መልዕክተኛ

‹‹የኢትዮጵያ ሚና ለሱዳን መንግሥት አዎንታዊና ደጋፊ ነው›› የሱዳን የሽግግር መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ልዩ መልዕክተኛ   ከተጀመረ አንደኛ ወሩን ላስቆጠረው የሱዳን ጦርነት ‹‹የኢትዮጵያ ሚና ለሱዳን መንግሥት አዎንታዊና ደጋፊ ነው፤›› ሲሉ፣ የሱዳን የሽግግር መንግሥት ምክር ቤት የአፍሪካ ኅብረትና የአፍሪካ ቀንድ አገሮች ልዩ መልዕክተኛ አስታወቁ፡፡ የሱዳን የሽግግር መንግሥት ምክር ቤት የአፍሪካ ኅብረትና የአፍሪካ… https://www.ethiopianreporter.com/118637/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከጆርዳን የመጣ ልዑክ የሕክምና ተቋማትን የሚመርጥበትን ሒደት መንግሥት እንዲመረምረው ተጠየቀ

ከጆርዳን የመጣ ልዑክ የሕክምና ተቋማትን የሚመርጥበትን ሒደት መንግሥት እንዲመረምረው ተጠየቀ መንግሥት የመረጣቸው የሕክምና ተቋማት ተቀባይነት አጠራጥሯል መንግሥት የማያውቀው ክፍያ በዶላር ሊከፈል መሆኑ ተጠቁሟል የቤት ሠራተኞችንና የተለያዩ ሙያ ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ወደ ዓረብ አገሮች መላክ መጀመሩን አስመልክቶ፣ ወደ ጆርዳን የሚላኩ ዜጎች የጤና ምርመራ የሚያደርጉባቸውን የሕክምና ተቋማት ለመምረጥ ወደ… https://www.ethiopianreporter.com/118640/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለፓርላማ በቀረበ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለብልፅግና አባላት ሥልጠና ተሰጠ መባሉ ጥያቄ አስነሳ

ለፓርላማ በቀረበ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለብልፅግና አባላት ሥልጠና ተሰጠ መባሉ ጥያቄ አስነሳ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም. የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ውስጥ፣ ለብልፅግና የክልል ፓርቲ ጽሕፈት ቤት አባላት የአቅም ግንባታ ሥልጠና ድጋፍ መሰጠቱ ተጠቅሶ መቅረቡ በፓርላማ ጥያቄ አስነሳ፡፡  የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ ሚያዝያ 8 ቀን… https://www.ethiopianreporter.com/118642/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአፍሪካ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ አኅጉራዊ ሁነት በአዲስ አበባ ሊዘጋጅ ነው

የአፍሪካ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ አኅጉራዊ ሁነት በአዲስ አበባ ሊዘጋጅ ነው የአፍሪካ ኅብረት 60ኛ ዓመት የምሥረታን በዓል መሠረት በማድረግ ተገማች ባልሆነው ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል? በሚለው ላይ የሚመክር ዓለም አቀፍ ኤክስፖና የምክክር ሁነት መዘጋጀቱን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ ይኼን ያስታወቀው… https://www.ethiopianreporter.com/118644/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢጋድ አባል አገሮች ሐዋላ ላይ የሚሠራ አገራዊ ተቋም እንዲያቋቁሙ ተጠየቀ

የኢጋድ አባል አገሮች ሐዋላ ላይ የሚሠራ አገራዊ ተቋም እንዲያቋቁሙ ተጠየቀ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) አባል አገሮች፣ በሐዋላ ላይ አፅንኦት ሰጥቶ የሚሠራ አገራዊ ተቋም ማቋቋም እንደሚገባቸው ተገለጸ፡፡ የሐዋላ ፖሊሲዎችን (Remittance Policies) በቀጣናው እንዲስማሙ የማድረግ ፕሮጀክት በሚል በተዘጋጀ የማዕከላዊ ባንኮች ስብሰባ ነበር፣ የተቋማቱን ማቋቋም… https://www.ethiopianreporter.com/118649/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሕዝብና ቤት ቆጠራ በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ይካሄዳል ተባለ

የሕዝብና ቤት ቆጠራ በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ይካሄዳል ተባለ የሕዝብና ቤት ቆጠራ፣ እንዲሁም የግብርና መረጃ ቆጠራ በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ እንደሚካሄድ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የ2015 ዓ.ም. የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት… https://www.ethiopianreporter.com/118653/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሙዓለ ንዋይ ገበያ ለማቋቋም አንድ ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ታወቀ

ሙዓለ ንዋይ ገበያ ለማቋቋም አንድ ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ታወቀ መንግሥት 25 በመቶ የግል ኢንቨስተሮች ደግሞ 75 በመቶ ድርሻ ይኖራቸዋል የኢትዮጵያ ‹‹የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ›› ለማቋቋም አንድ ቢሊዮን ብር ገደማ የመነሻ ካፒታል ያስፈልጋል ተባለ፡፡ በ2016 ዓ.ም. ወደ ሥራ የሚገባው የሙዓለ ንዋይ ገበያው ትርፍ ለማስመዝገብ ከሦስት… https://www.ethiopianreporter.com/118656/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሓት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት ተቃኝቶ እንዲስተካከል ጥያቄ አቀረበ

ሕወሓት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት ተቃኝቶ እንዲስተካከል ጥያቄ አቀረበ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ስለ ሕወሓት የሰጠው ውሳኔ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የገለጸው ሕወሓት፣ወሳኔው  በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት ተቃኝቶ እንዲስተካከል ጥያቄ አቀረበ። ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወ.ሓ.ት) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር… https://www.ethiopianreporter.com/118662/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች የሚያደርሱት ጥቃት እንዳልቆመ ታወቀ

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች የሚያደርሱት ጥቃት እንዳልቆመ የጋምቤላ ክልል ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች፣ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ወደ ክልሉ በመግባት የሚያደርሱት ጥቃት እንዳልቆመ፣ የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ለሪፖርተር ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያን ድንበር በመሻገር ጥቃት ያደርሳሉ የተባሉት ታጣቂዎቹ፣ ሰሞኑን ወደ ጋምቤላ ክልል ተሻግረው… https://www.ethiopianreporter.com/118525/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሳይሠሩ በተቋቋሙ ፋብሪካዎች ላይ ቁጥጥር እየተደረገ ነው

የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሳይሠሩ በተቋቋሙ ፋብሪካዎች ላይ ቁጥጥር እየተደረገ ነው ከዓመታት በፊት ሲቋቋሙ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሳይሠሩ የተቋቋሙ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ፋብሪካዎች እየተለዩ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን፣ የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ በአዲስ አበባ የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ ሳይኖር የተቋቋሙ በርካታ ፋብሪካዎች እንደሚገኙ የገለጹት የአዲስ… https://www.ethiopianreporter.com/118522/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በቅርብ ዓመታት ሲሚንቶን ወደ ውጭ ገበያ መላክና መንገድን በኮንክሪት መሥራት ይጀመራል ተባለ

በቅርብ ዓመታት ሲሚንቶን ወደ ውጭ ገበያ መላክና መንገድን በኮንክሪት መሥራት ይጀመራል ተባለ በቅርብ ዓመታት ውስጥ የሲሚንቶ ምርትን ወደ ውጭ ገበያ መላክና መንገድን በሲሚንቶ ኮንክሪት መሥራት ይጀመራል ሲሉ የማዕድን ሚኒስትሩ አስታወቁ፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ማዕድን ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሐሙስ ግንቦት… https://www.ethiopianreporter.com/118527/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሙዚቃ ልዕልቷ ሒሩት በቀለ (1935 – 2015)

የሙዚቃ ልዕልቷ ሒሩት በቀለ (1935 – 2015) ‹‹ኢትዮጵያ…. ሀገሬ መመኪያዬ ……ነሽ ክብሬ በጣም ያኮራኛል ኢትዮጵያዊነቴ የሀገሬ ፍቅር ፀንቶ በስሜቴ….. ኢትዮጵያ ….ሀገራችን ኢትዮጵያ …. እናታችን›› ይህ ዘመነ ዘመናትን እየተሻገረ እንደ ሕዝብ መዝሙር ሲደመጥ፣ ሲዘመር የነበረ፣ ትውልዱ በፍቅረ ሀገር እንዲፀና በማድረግ የበኩሏን ተግባር ከውናለች፡፡ የእሷን ፍኖት በመከተልም የእሷን ዘፈን… https://www.ethiopianreporter.com/118533/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሕግ አስከባሪ አካላት የሚደርሱ የማሰቃየትና ተገቢ ያልሆኑ አያያዞች በገለልተኛ አካል እንዲጣሩ ተጠየቀ

በሕግ አስከባሪ አካላት የሚደርሱ የማሰቃየትና ተገቢ ያልሆኑ አያያዞች በገለልተኛ አካል እንዲጣሩ ተጠየቀ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶችን አያያዝና አፈጻጸም የሚከታተለውና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ስምምነቶች አካላት (United Nations Human Rights-Treaty Bodies) በመባል የሚታወቀው የገለልተኛ ባለሙያዎች ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በሕግ አስከባሪ አካላት የሚፈጸሙ ማሰቃየትና እንግልቶች፣ በገለልተኛ አካላት… https://www.ethiopianreporter.com/118536/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአየር ንብረት ለውጥ ኢትዮጵያን ከአገራዊ ጥቅል ምርቷ እስከ ስድስት በመቶ እንዳሳጣት ተገለጸ

የአየር ንብረት ለውጥ ኢትዮጵያን ከአገራዊ ጥቅል ምርቷ እስከ ስድስት በመቶ እንዳሳጣት ተገለጸ በካርቦን ልቀት ላይ ታክስ ሊጣል እንደታሰበ ተጠቆመ በዓለም ላይ እየከፋ የመጣው የአየር ንብረት ለውጥ በኢትዮጵያም ከማኅበራዊ ቀውስ ባሻገር በኢኮኖሚ ላይ ተፅዕኖ በማሳደር፣ ከአጠቃላይ የአገራዊ ጥቅል ምርቷ (GDP) ከ3.6 በመቶ እስከ 6.1 በመቶ እያሳጣት መሆኑ ተገለጸ፡፡ በዓለም… https://www.ethiopianreporter.com/118538/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

‹‹ጣት እየተቀሳሰርን የዴሞክራሲን አካሄድ እናሳድጋለን ማለት ዘበት ነው›› የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

‹‹ጣት እየተቀሳሰርን የዴሞክራሲን አካሄድ እናሳድጋለን ማለት ዘበት ነው›› የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኢሠፓ የፓርቲ ምዝገባ መከልከሉ ጥያቄ አስነስቷል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ‹‹ጣት እየተቀሳሰርን የዴሞክራሲን አካሄድ እናሳድጋለን ብለን አስበን ከሆነ ዘበት ነው የሚሆነው፤›› ሲሉ፣ ተናገሩ፡፡ ምክትል ሰብሳቢው ይህን የተናገሩት የቦርዱን የዘጠኝ ወራት የዕቅድ… https://www.ethiopianreporter.com/118547/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ቡና በማከማቸት ለውጭ ገበያ ያላቀረቡ ላኪዎች መጋዘን እየታሸገ ነው

ቡና በማከማቸት ለውጭ ገበያ ያላቀረቡ ላኪዎች መጋዘን እየታሸገ ነው የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ገበያ አፈላልገው ኮንትራት ሳይዋዋሉ ቡና ያከማቹ ላኪዎችን መጋዘኖች ማሸግ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ የቡና ላኪዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት እንዳያገኙ ተደርጎ፣ ቡናውን በገቡት ኮንትራት መሠረት ወይም ደግሞ ኮንትራት ከሌላቸው ደግሞ ኮንትራት ላላቸው እንዲሸጡ በማድረግ… https://www.ethiopianreporter.com/118544/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በግማሽ ቢሊዮን ብር ወጪ የተመሠረተው ቴሌቪዥን ጣቢያ ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ ሥርጭት ሊጀምር ነው

በግማሽ ቢሊዮን ብር ወጪ የተመሠረተው ቴሌቪዥን ጣቢያ ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ ሥርጭት ሊጀምር ነው በኢትዮጵያውያን ባለሀብቶችና በሚዲያ ባለሙያዎች በግማሽ ቢሊዮን ብር ወጪ የተመሠረተው ናሽናል ሚዲያ አክሲዮን ማኅበር፣ በከፍተኛ መዋዕለ ንዋይና በላቀ ቴክኖሎጂ ተደራጅቷል የተባለው ዘመናዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ  NBC Ethiopia ከዛሬ ሚያዚያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር… https://www.ethiopianreporter.com/118219/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የአክሱም አውሮፕላን ማረፊያን መልሶ ለመገንባት በመቶ ሚሊዮኖች ወጪ ያስፈልጋል ተባለ

የአክሱም አውሮፕላን ማረፊያን መልሶ ለመገንባት በመቶ ሚሊዮኖች ወጪ ያስፈልጋል ተባለ በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው መሠረተ ልማቶች አንዱ የሆነውና ለሁለት ዓመታት ያለ አገልግሎት የቆየው የአክሱም አውሮፕላን ማረፊያን መልሶ ለመገንባት፣ በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አስታወቀ፡፡ የአውሮፕላን ማረፊያው መንደርደርያ… https://www.ethiopianreporter.com/118222/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መንግሥት ሲቪል ማኅበራት የዘፈቀደ እሥራትን በተመለከተ ያቀረቡትን ምክረ ሐሳቦች እንዲተገብር ተጠየቀ

መንግሥት ሲቪል ማኅበራት የዘፈቀደ እሥራትን በተመለከተ ያቀረቡትን ምክረ ሐሳቦች እንዲተገብር ተጠየቀ   መንግሥት ከሕግ ውጪ የዘፈቀደ እስራትን በተመለከተ፣ በሲቪል ማኅበራት ተወካዮች ተጣርተው የቀረቡ መረጃዎችንና ምክረ ሐሳቦችን በመቀበል ተግባራዊ እንዲያደርግ ጥያቄ ቀረበለት፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥያቄውን ያቀረበው በባህር ዳር፣ በጅግጅጋና በሐዋሳ ከተሞች ያካሄደውን ግልጽ የምርመራ ውይይቶች… https://www.ethiopianreporter.com/118229/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አሁን ባለው አገራዊ ሁኔታ ሕገ መንግሥቱን ለማሻሻል ማሰብ አደጋው የከፋ ሊሆን ይችላል ተባለ

አሁን ባለው አገራዊ ሁኔታ ሕገ መንግሥቱን ለማሻሻል ማሰብ አደጋው የከፋ ሊሆን ይችላል ተባለ በሥራ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አሁን ባለው አገራዊ ሁኔታ ለማሻሻል ወይም ለመቀየር ማሰብ አደጋው የከፋ ስለሚሆን፣ ጠንካራ የአገረ መንግሥት ግንባታና የተሻለ የሰላም ሁኔታ ማስፈን የሚለው ቀዳሚ ሥራ መቅደም አለበት የሚለው ጉዳይ ምሁራንን አነጋገረ፡፡ ‹‹አገራዊና… https://www.ethiopianreporter.com/118233/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዓለም ባንክ ድጋፍ በሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ላይ ሙስናና ብልሹ አሠራሮች እንደሚፈጸሙ ተገለጸ

በዓለም ባንክ ድጋፍ በሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ላይ ሙስናና ብልሹ አሠራሮች እንደሚፈጸሙ ተገለጸ በዓለም ባንክ ድጋፍ በሚከናወኑ ሰባት ፕሮጀክቶች ላይ ሙስናና ብልሹ አሠራሮች የሚፈጸሙ ቢሆንም በሪፖርት ውስጥ እንደማይካተቱ፣ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ይህንን ያስታወቀው ሚያዝያ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ በዓለም ባንክ ዕገዛ. https://www.ethiopianreporter.com/118236/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

‹‹የሚጠና የፖሊሲ ጉዳይ የለንም›› የሚሉ የመንግሥት ተቋማት መኖራቸው ተገለጸ

‹‹የሚጠና የፖሊሲ ጉዳይ የለንም›› የሚሉ የመንግሥት ተቋማት መኖራቸው ተገለጸ ትምህርት ሚኒስቴር አንደኛው መሆኑ ተጠቁሟል የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት መንግሥታዊ ተቋማት እንዲጠኑላቸው የሚፈልጉትን የፖሊሲ ጉዳይ እንዲያሳውቁት በሰርኩላር ቢጠይቅም፣ አንዳንዶቹ ‹‹የሚጠና ጉዳይ የለንም›› የሚል ምላሽ እንደሚሰጡ አስታወቀ፡፡ ኢንስቲትዩቱ እያንዳንዱ መንግሥታዊ ተቋም ለምርምር የሚበቁና የሚነሱ ጉዳዮችን፣ እንዲሁም በግልጽ መረጃ… https://www.ethiopianreporter.com/118239/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኢትዮጵያ ያለው የሲቪክና የሚዲያ ምኅዳር አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ያለው የሲቪክና የሚዲያ ምኅዳር አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ 30ኛው የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ዛሬ እየተከበረ ነው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት፣ የሲቪክና የሚዲያ ምኅዳር ውስጥ እየተፈጠሩ ያሉ ክስተቶች አሳሳቢ እየሆኑ መምጣታቸውን የተመድ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጽሕፈት ቤተ ገለጸ፡፡ ባለፉት ሁለት ቀናት በኢትዮጵያ ጉብኝት… https://www.ethiopianreporter.com/118245/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሱዳን ቀውስ በጎረቤት አገሮች ሊፈጥር የሚችለው ተፅዕኖ

የሱዳን ቀውስ በጎረቤት አገሮች ሊፈጥር የሚችለው ተፅዕኖ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን እ.ኤ.አ. ፌብሩዋሪ 1957 ነበር በሱዳን መዲና ካርቱም የተመሠረተው፡፡ ሱዳን ያኔ ከጎረቤቶቿ ኢትዮጵያና ግብፅ ጋር ሆና ነበር ለመላው የአፍሪካ አኅጉር መዝናኛ…
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያ ካርቱም የሚገኙ ዲፕሎማቶቿን ወደ ገዳሪፍ አዛወረች

ኢትዮጵያ ካርቱም የሚገኙ ዲፕሎማቶቿን ወደ ገዳሪፍ አዛወረች ሃምሳ አገሮች ዜጎቻቸውን በኢትዮጵያ በኩል ለማስወጣት ጠይቀዋል ከተጀመረ ሁለት ሳምንታት ያለፈው የሱዳን ጦርነት፣ በፀጥታ ሥጋትና በመሠረታዊ አገልግሎቶች መቋረጥ ምክንያት፣ ኢትዮጵያ ካርቱም የሚገኙ ዲፕሎማቶቿን ወደ ገዳሪፍ… https://www.ethiopianreporter.com/118099/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

መንግሥት የሦስት ዓመታት የልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ በበጀት ዓመቱ ለማፅደቅ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ

መንግሥት የሦስት ዓመታት የልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ በበጀት ዓመቱ ለማፅደቅ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ አገራዊ የስፓሻል ልማት ማዕቀፍ ረቂቅ ሰነድ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል ከ2016 እስከ 2018 የበጀት ዓመት ተግባራዊ የሚደረገውና በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ በሚባል ደረጃ የተዘጋጀው፣ የልማትና የመንግሥት ኢንቨስትመንት ዕቅድ፣… https://www.ethiopianreporter.com/118098/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በደቡብ ለተከሰተው ድርቅ መንግሥት ስድስት ጊዜ እርዳታ ተጠይቆ አለመስጠቱ በምርመራ ተረጋገጠ

በደቡብ ለተከሰተው ድርቅ የፌደራል መንግሥት ስድስት ጊዜ በደብዳቤ ተጠይቆ ምላሽ አለመስጠቱ በምርመራ ተረጋገጠ ሲሳይ ሳህሉ – April 30, 2023 የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በደቡብ ኦሞ ዞን በተከሰተው ድርቅና ጎርፍ አደጋ ምክንያት፣ የፌዴራል መንግሥቱ ለችግሩ ምላሽ እንዲሰጥ የክልሉ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ስድስት ጊዜ በደብዳቤ እንዲሁም በስልክ ዕርዳታ ቢጠይቁም፣ ምንም ዓይነት… https://www.ethiopianreporter.com/118116/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ለኮምቦልቻ ወደብ የተያዘ በጀት ለጂማ አለመዛወሩን አስተባበለ

ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ለኮምቦልቻ ወደብ የተያዘ በጀት ለጂማ አለመዛወሩን አስተባበለ ኤልያስ ተገኝ – April 30, 2023 የመቀሌ ደረቅ ወደብና ተርሚናልን ለማስጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት፣ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ አዲስ ደረቅ ወደብ ለመገንባት የያዘውን በጀት ወደ ጂማ የደረቅ ወደብ ግንባታ አዘዋውሯል በሚል የሚናፈሳው መረጃ… https://www.ethiopianreporter.com/118119/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢሰማኮ በሰላማዊ ሠልፍ ለመንግሥት ጥያቄ እንደሚያቀርብ አስታወቀ

ኢሰማኮ በሰላማዊ ሠልፍ ለመንግሥት ጥያቄ እንደሚያቀርብ አስታወቀ   በኑሮ ውድነት ምክንያት በሠራተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጫና መፍትሔ እንዲያገኝና ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ምጣኔ እንዲሻሻል፣ በሰላማዊ ሠልፍ ጥያቄ ለመንግሥት እንደሚያቀርብ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) አስታወቀ፡፡ ‹‹ለሠራተኛው መሠረታዊ ጥያቄዎች አፋጣኝ መፍትሔ›› በሚል መሪ ቃል የዘንድሮውን… https://www.ethiopianreporter.com/118128/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በውጭ ምንዛሪ ሥርዓቱ ላይ ‹‹መሠረታዊ ቅኝት›› እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ

በውጭ ምንዛሪ ሥርዓቱ ላይ ‹‹መሠረታዊ ቅኝት›› እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ   የትግራይ ክልል ተሳታፊዎች የተገኙበት የኢንቨስመንት ፎረም ተካሄደ ለማክሮ ኢኮኖሚ ዕድገትና ለውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ‹‹ጠቃሚ ጉዳይ›› በመሆኑ፣ የውጭ ምንዛሪ ሥርዓቱ ‹‹መሠረታዊ ቅኝት›› እየተደረገበት መሆኑ ተገለጸ፡፡ በምንዛሪ ሥርዓቱ ላይ መሠረታዊ ቅኝት እየተደረገ መሆኑን የገለጹት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ… https://www.ethiopianreporter.com/118131/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ በትምህርታቸው ላይ ጫና እንደፈጠረባቸው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ

የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ በትምህርታቸው ላይ ጫና እንደፈጠረባቸው የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ በአበበ ፍቅር ከሁለት ሳምንታት በላይ ያስቆጠረው የኢንተርኔት (የበይነ መረብ) አገልግሎት መቋረጥ በትምህርታቸው ላይ ጨና እየፈጠረባቸው መሆኑን፣ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተናገሩ፡፡ የተለያዩ መረጃዎችን በብዛት የሚያገኙት ከኢንተርኔት መሆኑን የተናገሩት ተማሪዎቹ፣ አሁን ግን አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ከመምህራን የሚሰጣቸውን… https://www.ethiopianreporter.com/117993/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ወደ ውጭ ከተላከ እንጀራ 28 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱ ታወቀ

ወደ ውጭ ከተላከ እንጀራ 28 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ ሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች በአገር ውስጥ ምርቶች ተተክተዋል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ወደ ውጭ ከተላከ እንጀራ 28 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2008 ዓ.ም. አሻሽሎ ባወጠው የአሠራርና የአባላት ሥነ ምግባር መሠረት፣… https://www.ethiopianreporter.com/118008/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ለቀጣይ ዓመት የበጀት ዝግጅት የዕቅድ ምክክር ተጀመረ

ለቀጣይ ዓመት የበጀት ዝግጅት የዕቅድ ምክክር ተጀመረ እያለቀ ላለው በጀት ዓመት ተጨማሪ በጀት አልተጠየቀም የዴሞክራሲ ተቋማት የበጀት ዕቅዳቸውን ለፓርላማው እያቀረቡ ነው ለመጪው 2016 በጀት ዓመት የበጀት ዕቅድ ዝግጅት፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ጋር የበጀት ስሚ መርሐ ግብር ማካሄድ ጀመረ፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ከተለያዩ… https://www.ethiopianreporter.com/118004/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የመከላከያ የትጥቅ ግዥ ሚስጥራዊነት ላይ የፓርላማ አባላት ጥያቄ አነሱ

የመከላከያ የትጥቅ ግዥ ሚስጥራዊነት ላይ የፓርላማ አባላት ጥያቄ አነሱ በአምስት ዓመታት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ ማሻሻያ የተደረገበትን የመከላከያ አዋጅ ለማፅደቅ ትናንት ማክሰኞ ሚያዝያ 17 ቀን 2015 ዓ.ም. የተሰባሰቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በአዋጁ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ክርክር አንስተዋል፡፡ ነባሩ አዋጅ ‹‹መከላከያ ”የፌዴራል መንግሥት የግዥ… https://www.ethiopianreporter.com/118011/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በደቡብ ክልል የሠሩበትን የትርፍ ሰዓት ክፍያ የጠየቁ የጤና ባለሙያዎች ዛቻ እየደረሰብን ነው አሉ

በደቡብ ክልል የሠሩበትን የትርፍ ሰዓት ክፍያ የጠየቁ የጤና ባለሙያዎች ዛቻ እየደረሰብን ነው አሉ ለአሥር ወራት በትርፍ ሰዓት የሠሩበትን ክፍያ ባለማግኘታቸው ምክንያት የሚመለከተው አካል እንዲከፍላቸው የጠየቁ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጣቢያ የሚገኙ ከ38 በላይ የጤና ባለሙያዎች፣ ‹‹ደመወዝ በመጠየቃችን እስርና ዛቻ እየተፈጸመብን… https://www.ethiopianreporter.com/118017/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የብረት አጥር ዝርፊያን ለመግታት ኮንክሪት ለማድረግ መገደዱን አስታወቀ

የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የብረት አጥር ዝርፊያን ለመግታት ኮንክሪት ለማድረግ መገደዱን አስታወቀ ብረቱን ወደ ኮንክሪት ለመቀየር ከፍተኛ ወጪ ይጠይቃል የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በአዲሱ አዳማ ፈጣን መንገድ ዳርና ዳር የተተከለውን የብረት አጥር ዝርፊያ ለማስቀረት፣ የተተከሉትን የብረት አጥሮች በኮንክሪትና በተቀቀሉ እንጨቶች ለመቀየር መገደዱን አስታወቀ፡፡ በመንገዶቹ ዙሪያ የተተከሉትን ብረቶች ሊሰረቁ በማይችሉ… https://www.ethiopianreporter.com/118014/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አበዳሪ አገሮች የኢትዮጵያን የዕዳ ሽግሽግ ሒደት በአፋጣኝ እንዲያገባድዱ የአውሮፓ ኅብረት ጠየቀ

አበዳሪ አገሮች የኢትዮጵያን የዕዳ ሽግሽግ ሒደት በአፋጣኝ እንዲያገባድዱ የአውሮፓ ኅብረት ጠየቀ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙን እንዲደግፉ ጠይቋል ኢትዮጵያ አበዳሪ አገሮችን በተደጋጋሚ ስትጠይቅ ለቆየችው የዕዳ ይሸጋሽግልኝ ጥያቄ፣ አበዳሪ አገሮች አፋጣኝ ምላሽ የመስጠት ሒደቱን እንዲያገባድዱ የአውሮፓ ኅብረት ጥሪ አቀረበ፡፡ አበዳሪ አገሮቹ በጋራ ባቋቋሙት የጋራ ማዕቀፍ (Common… https://www.ethiopianreporter.com/118023/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዲጂታል የክፍያ ዘዴ የተጀመረው የነዳጅ ግብይት ለነዳጅ እጥረት መፈጠር ምክንያት እንዳይሆን ተሠግቷል

በዲጂታል የክፍያ ዘዴ የተጀመረው የነዳጅ ግብይት ለነዳጅ እጥረት መፈጠር ምክንያት እንዳይሆን ተሠግቷል የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል የክፍያ ዘዴ ለማስፈጸም ከትናንት በስቲያ ጀምሮ መተግበር የጀመረው አሠራር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ማደያዎችን እያጨናነቀና ለነዳጅ እጥረት መንስዔ እንደሆነ ተገለጸ፡፡ መንግሥት በአስገዳጅነት እንዲተገበር ያደረገው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ፣ በታክሲዎች ላይ ተፈጻሚ… https://www.ethiopianreporter.com/118028/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የዋጋ ግሽበት ምጣኔ መስፋት አባባሽ ምክንያቶችና የሚቀርበው አመክንዮ

የዋጋ ግሽበት ምጣኔ መስፋት አባባሽ ምክንያቶችና የሚቀርበው አመክንዮ የዋጋ ግሽበት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ባደጉ አገሮች ጭምር ፈተና መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ኢትዮጵያም እ.ኤ.አ. በ2023 በዓለም ደረጃ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ከተመዘገበባቸው አሥር… https://www.ethiopianreporter.com/117770/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎችን የሚያቋቁመው ረቂቅ አዋጅ በርካታ አደረጃጀቶችን ይዞ መምጣቱ ጥያቄ አስነሳ

ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎችን የሚያቋቁመው ረቂቅ አዋጅ በርካታ አደረጃጀቶችን ይዞ መምጣቱ ጥያቄ አስነሳ የቦርድ አባላት ስብጥር ከመንግሥት አካላት የፀዳ እንዲሆን ተጠይቋል የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎችን ለማደራጀት በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ፣ በትምህርት ተቋማቱ ይዋቀራሉ ተብለው የታሰቡት አደረጃጀቶች መብዛት፣ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሥራ መጠላለፍና መደራረብ ይፈጥራል የሚል ሥጋት እንዳለባቸው ምሁራን ገለጹ፡፡ በቅርቡ የራስ ገዝ… https://www.ethiopianreporter.com/117742/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በዜጎችና በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እንዲቆም ተጠየቀ

በዜጎችና በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እንዲቆም ተጠየቀ ሁለት የግብረ ሰናይ ድርጅት ሠራተኞች መገደላቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል የኢትዮጲያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት፣ ከሰሞኑ የክልል ልዩ ኃይል አባላትን በአዲስ መልክ ለማደራጀት በተጀመረው ሥራ በዜጎች፣ በሲቪል ማኅበረሰብ ተቋማትና ሠራተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት እንዲቆም ጠየቀ፡፡ ምክር.. https://www.ethiopianreporter.com/117720/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር ለምርታማነት ማነቆ እንደሆነበት የአማራ ክልል አስታወቀ

የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር ለምርታማነት ማነቆ እንደሆነበት የአማራ ክልል አስታወቀ በአማራ ክልል የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር እንደገጠማቸውና ለሥራቸው እንቅፋት እንደሆነባቸው፣ የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ፡፡ ‹‹ኢንዱስሪዎች የሚገጥማቸው የኃይል አቅርቦት ችግር፣ የማምረት አቅማችንን ከማሳደግ አኳያ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጥሯል፤›› ሲሉ የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት… https://www.ethiopianreporter.com/117723/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከተሽከርካሪዎች መብዛት ጋር በተያያዘ የሕግ ጥሰቶች እየተበራከቱ መሆኑን ትራፊክ ማኔጅመንት ገለጸ

ከተሽከርካሪዎች መብዛት ጋር በተያያዘ የሕግ ጥሰቶች እየተበራከቱ መሆኑን ትራፊክ ማኔጅመንት ገለጸ በየዕለቱ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ የትራፊክ ሕግ ጥሰቶች እየተበራከቱ መምጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ለሪፖርተር ገለጸ፡፡ የተሽከርካሪዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ የትራፊክ ሕግ የሚጥሱና ዕርምጃ የሚወሰድባቸው አሽከርካሪዎች ቁጥር እየጨመረ… https://www.ethiopianreporter.com/117727/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የፌዴራል ግዥዎች በኤሌክትሮኒክስ እንዲካሄዱ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ተላከ

የፌዴራል ግዥዎች በኤሌክትሮኒክስ እንዲካሄዱ የሚያስገድድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ተላከ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ19ኛው መደበኛ ስብሰባው ተወያይቶ ለፓርላማው እንዲፀድቅ የላከው የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ፣ የፌዴራል ግዥዎች ከ2016 ዓ.ም. ጀምሮ በኤሌክትሮኒክስ እንዲያካሂዱ የሚደነግግ መሆኑ ተነገረ፡፡ ረቂቅ አዋጁ ከዚህ ቀደም የነበሩ በግዥና በንብረት አስተዳደር ሥርዓት… https://www.ethiopianreporter.com/117730/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

‹‹ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ጉባዔ በጎ ውሳኔዎችን ትጠብቃለች›› ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

‹‹ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ጉባዔ በጎ ውሳኔዎችን ትጠብቃለች›› ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመጭው ግንቦት ወር መጀመሪያ ሳምንት በብራስልስ ከሚጀምረው የአውሮፓ ኅብረት ካውንስል ጉባዔ፣ ኢትዮጵያ በጎ የሚባሉ ውሳኔዎችን እንደምትጠብቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መለስ ዓለም (አምባሳደር) በሳምንታዊ መግለጫቸው እንዳሉት፣ የኢትዮጵያና የአውሮፓ ኅብረት ግንኙነት. https://www.ethiopianreporter.com/117725/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በምሥራቅ ኢትዮጵያ በኮንትሮባንድ የሚወጣውን ጫት ለመከላከል ፈቃደኝነት እንደሌለ ተነገረ

በምሥራቅ ኢትዮጵያ በኮንትሮባንድ የሚወጣውን ጫት ለመከላከል ፈቃደኝነት እንደሌለ ተነገረ በምሥራቅ ኢትዮጵያ በሶማሌ ክልልና አካባቢው በኮንትሮባንድ የሚወጣውን ጫት ለመከላከል ተባባሪ እንዳልሆኑ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የጉምሩክ ሕግ ተገዥነት ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሙሉቀን በየነ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በምሥራቅ ኢትዮጵያና አካባቢዋ ‹‹ጫት ለአገር ውስጥ ፍጆታ… https://www.ethiopianreporter.com/117733/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የለመዱትን ያስጣለ የኑሮ ውድነት

በአበበ ፍቅር ‹‹አንተ ደህና እንድትውል ቤተሰብህ ደህና ይዋል›› የሚባለው አባባል የአንዱ ሰላም መሆን ለሌላው ሰላም ውሎ ማደር ወጥቶ መግባት ወሳኝ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት ለብዙዎች አሳሳቢ ጉዳይ እየሆነ መጥቷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው አስቸጋሪና ፈታኝ መሆን አብዛኛውን የኅብረተሰብ ክፍል ጓዳ ነክቷል፡፡ የአንደኛው አበሳ ጠባሳው ሳይሽር ሌላው እየተተካ በአንዱ ሲሉት በሌላው እያመረቀዘ መምጣት በኢትዮጵያ ሰላም እንዲናፈቅ አድርጓል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታየ ያለው የሰላም መደፍረስና ግርግር ተስፋቸውን ያጨለመባቸው ነዋሪዎች ደግሞ እንደባህል፣ እምነታቸውና ወጋቸው የሚያከብሩትን በዓል እንኳን በደስታ እንዳያከብሩ እንቅፋት ሆኗል፡፡ አቅሙ እንኳን ቢኖር ሥነ ልቦናዊ ጫናው ደስታቸውን ስለመንጠቁ አስተያየት የሰጡን ነግረውናል፡፡ ‹‹በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ›› እንደሚባለው በየቀኑ በፍጥነት እየጨመረና እያደገ ያለው የኑሮ ውድነትም በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰዎችን ከመብላት ወዳለመብላት፣ ከዘመድ አዝማድ ከመጠያየቅ ወዳለመጠያየቅ፣ በዓላትን እንደልማዳቸው ከማክበር ወዳለማክበር፣ ከየጎረቤት ከመቋደስ ወዳለመቋደስ እያሸጋገራቸውም ነው፡፡ ኑሮው ከሚችሉት በላይ እየሆነባቸው እንደመጣና በዚሁ ከቀጠለ ለመኖርና በልቶ ለማደር በእጅጉ እንደሚቸገሩ ስጋታቸውን ያጋሩንም አሉ፡፡ ከዕለት ኑሮ በተለየ መልኩ በጉጉት የሚጠብቁት፣ ከመቼውም በተለየ በጋራ የሚበሉበት፣ የሚጠጡበትና አዳዲስ የሚለብሱበት በዓል ሲመጣ አብሮት የሚመጣው ወጪ ፍርኃትና ጭንቀት እንደሆነባቸው የሚገልጹም አሉ፡፡ ወ/ሮ መሠረት ብርቁ፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ መንገድ ዳር ሸራ ወጥረው ሻይና ቡና በመሸጥ ሁለት ልጆቻቸውን ያሳድጋሉ፡፡ ለልጆቻቸው አቅማቸው የፈቀደውን እያደረ ቢሆንም፣ የኑሮ ውድነቱ እንደፈተናቸው ይናገራሉ፡፡ በተለይ በዓላት
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የማዕድን አምራቾች የሮያልቲ ክፍያን ዝቅ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ

የማዕድን አምራቾች የሮያልቲ ክፍያን ዝቅ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ  ፀደቀ ከፍተኛ ደረጃ የከበረ ማዕድን አምራቾች ይከፍሉ የነበረውን የሮያልቲ ክፍያ መጠን፣ ከሰባት ወደ አምስት በመቶ ዝቅ እንዲል የሚያደርገውን የማዕድን ሀብት ልማት ረቂቅ አዋጅ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አፀደቀ፡፡ የማዕድን ማምረት ሥራ ባለፈቃዶች ከማዕድን ማምረቻ ሥፍራ ከሚያወጡት የማዕድናት… https://www.ethiopianreporter.com/117751/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያ የገባችበት የውጭ ዕዳ ጫና አጣብቂኝና የአበዳሪ አገሮች ፖለቲካዊ ፍልሚያ

የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማልፓስ በአሜሪካ መካሄድ የጀመረውን የዓለም ባንክና የአይኤምኤፍ የጋራ ጉባዔ መጀመር አስመልክቶ፣ ባለፈው ሳምንት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ታዳጊ የአፍሪካ አገሮች ያለባቸውን ከፍተኛ የውጭ ዕዳ ማቅለያና የመክፈያ ጊዜን በመልሶ ማዋቀር ለማራዘም ያቀረቡት የዕዳ መልሶ ማዋቀር ጥያቄ መዘግየት እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል። በተለይ ኢትዮጵያ፣ ጋናና ዛምቢያ የገጠማቸው የዕዳ ጫና ቀውስ እየሰፋ በመሄዱ፣ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ዕዳቸውን ለማቅለልና የመክፈያ ጊዜው እንዲራዘም ያቀረቡት ጥያቄ ላይ በአስቸኳይ መወሰን ያስፈልጋል ብለዋል። ‹‹ሁሉም አበዳሪ ወገኖች ቃላትን ወደ ተግባር የሚቀይሩበት ጊዜው አሁን ነው፤›› ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል። ይሁን እንጂ የአገሮቹን በተለይም የኢትዮጵያን የውጭ ዕዳ መልሶ በማዋቀር የዕፎይታ ጊዜ ለመስጠት አስቸጋሪ የሆነው አገሮቹ (ኢትዮጵያን ጨምሮ) ከቻይና መንግሥት የወሰዱት ብድርና የብድር ስምምነቱ ሚስጥራዊ መሆን፣ ሌሎች አበዳሪ አገሮች የቀረበላቸውን የዕዳ መልሶ የማዋቀር ጥያቄ ለመመለስ መቸገር ነው፡፡ አሜሪካ በዓለም የገንዘብ ድርጅት ላይ ያላትን ተፅዕኖ በመጠቀምና የቡድን 20 አገሮችን በማስተባበር፣ ታዳጊ አገሮች ከቻይና ያገኙት የውጭ ብድር ግልጽ ካልሆነ የዕዳ ጫናውን የማቃለል ተግባር እንዳይፈጸም ጫና እያደረገች ነው። ለዝርዝር ዘገባው ሊንኩን ይጫኑ ። https://www.ethiopianreporter.com/117779/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሁሉም ክልሎች የታየው የጤፍ ዋጋ ጭማሪ የመጋቢት ወር የዋጋ ግሽበትን ማሻቀቡ ተነገረ

በሁሉም ክልሎች የታየው የጤፍ ዋጋ ጭማሪ የመጋቢት ወር የዋጋ ግሽበትን ማሻቀቡ ተነገረ በመጋቢት ወር በአገሪቱ ሁሉም ክልሎች የታየው የጤፍ ዋጋ ጭማሪ ወርኃዊ የምግብ ዋጋ ግሽበትን እንዲያሻቅብ ማድረጉን፣ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ፡፡ በተጠናቀቀው ወር ከሰብል እህሎች በተለይም የጤፍ፣ እንዲሁም የአትክልና ፍራፍሬና የጥራጥሬ ምርቶች ዋጋ ጭማሪ እንዳሳየ የተገለጸ ሲሆን፣… https://www.ethiopianreporter.com/117629/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ስኳር ኮርፖሬሽንንና ሳዑዲ ስታርን ሊከስ መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ስኳር ኮርፖሬሽንንና ሳዑዲ ስታርን ሊከስ መሆኑን አስታወቀ ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ የስድስት ግድቦችን ውኃ ተጠቅመው ክፍያ ባልፈጸሙ በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽንና በሳዑዲ ስታር እርሻ ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል የማኅበር ላይ ክስ ሊመሠርት መሆኑን፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡ ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ዓመታት… https://www.ethiopianreporter.com/117632/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የቁም እንስሳት ግብይትን ጨምሮ ሦስት ፖሊሲዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ ሊደረጉ ነው

የቁም እንስሳት ግብይትን ጨምሮ ሦስት ፖሊሲዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ ሊደረጉ ነው በኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ያልነበሩ ብሔራዊ የንግድ፣ የጥራትና የቁም እንሰሳት ዓብይት ሦስት ፖሊሲዎች በዚህ ዓመት ፀድቀው ተግባራዊ ዝግጅት መጠናቀቁን፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ከሦስቱ ፖሊሲዎች በተጨማሪም ብሔራዊ የውጭ ንግድ ፕሮሞሽን ስትራቴጂ በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘጋጅቶ… https://www.ethiopianreporter.com/117635/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዩኒቨርሲቲዎች በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ መፈቀዱ ለትምህርት ተደራሽነትና ጥራት እንቅፋት እንዳይሆን ተሰግቷል

ዩኒቨርሲቲዎች በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ መፈቀዱ ለትምህርት ተደራሽነትና ጥራት እንቅፋት እንዳይሆን ተሰግቷል   በሦስት ዓመታት ውስጥ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ይሆናሉ ተብሏል የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎችን ለማደራጀት እንዲረዳ ተዘጋጅቶ ለውይይት በቀረበው ረቂቅ አዋጅ፣ ዩኒቨርሲቲዎቹ በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ መደንገጉ፣ ተቋማቱ ከትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ይልቅ ወደ ገንዘብ ማካበት እንዳይሄዱ ሥጋት እንዳላቸው… https://www.ethiopianreporter.com/117638/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ማረጋገጫና ፈቃድ ሳይኖረው ግንባታ ማከናወኑ በኦዲት ተረጋገጠ

ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ማረጋገጫና ፈቃድ ሳይኖረው ግንባታ ማከናወኑ በኦዲት ተረጋገጠ ‹‹የግንባታ ፈቃድ ማውጣት እንዳለብን አሁን ነው ያወቅነው›› ፍቅሬ ደሳለኝ (ፕሮፌሰር)፣ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ‹‹እኔ ከፕሮፌሰር እንደዚህ ያለ መልስ አልጠብቅም›› ወ/ሮ አራሬ ሞሲሳ፣ የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ የግንባታ ማረጋገጫና ፈቃድ ሳይኖረው https://www.ethiopianreporter.com/117641/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አይኤምኤፍና ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የሁለትዮሽ የምንዛሪ ገበያ እንዳይኖር ሊመክሩ ነው

አይኤምኤፍና ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የሁለትዮሽ የምንዛሪ ገበያ እንዳይኖር ሊመክሩ ነው ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይኤምኤፍና ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ያለውን የሁለትዮሽ የውጭ ምንዛሪ ገበያ እንዳይቀጥል ለማድረግ የሚያስችል መፍትሔ ለማግኘት በዚህ ሳምንት ስብሰባ ሊቀመጡ መሆናቸውን ገለጹ፡፡ ስብሰባው በዚሁ ሳምንት መካሄድ በጀመረው የሁለቱ ተቋማት ዓመታዊ የስፕሪንግ ጉባዔ (Spring… https://www.ethiopianreporter.com/117651/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በደብረብርሃን ከተማ ሁሉም ነገር ዝግ ከመሆኑም በተጨማሪ መግባትም ሆነ መውጣት እንዳልተቻለ ነዋሪዎች ተናገሩ

በደብረብርሃን ከተማ ሁሉም ነገር ዝግ ከመሆኑም በተጨማሪ መግባትም ሆነ መውጣት እንዳልተቻለ ነዋሪዎች ተናገሩ በከተማው ውስጥና ዙሪያው የተኩስ ልውውጥ መኖሩም ተጠቁሟል ወደ ደሴ መውጫ እስከ ጣርማ በር ተሽከርካሪዎች ከነጭነታቸው መቆማቸው ታውቋል የክልል ልዩ ኃይሎችን እንደገና ማደራጀት ወይም ወደ መከላከያ፣ ፖሊስ፣ ፌዴራል ፖሊስ ለማካተት ወይም ወደ ሲቪል ለመመለስ ከተጀመረው እንቅስቃሴ ጋር… ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ 
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ገዥው ብልፅግና ፓርቲና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በወቅታዊው የአማራ ክልል ውጥረት ምክንያት ተፋጠዋል፡፡

የክልል ልዩ ኃይሎችን በአገር መከላከያ፣ በፌዴራል ፖሊስና በክልል ፖሊስ መዋቅሮች እንዲደራጁ ውሳኔ ከተላለፈ በኋላ፣ በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ተቃውሞ፣ ገዥው ብልፅግናና አብን የቃላት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል፡፡ ስድስተኛ ቀኑን የያዘውና በአማራ ክልል በርካታ ከተሞች በቀጠለው ተቃውሞ የክልሉ ነዋሪዎች ውሳኔው ጊዜውን ያልጠበቀ፣ የክልሉን የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያላስገባ ከመሆኑም በላይ፣ የክልል ልዩ ኃይል መፍረስ ውሳኔ በክልላቸው ቀድሞ መጀመሩ ቁጣ እንደቀሰቀሰባቸው በፖለቲከኞች ዘንድ በተደጋጋሚ ተወስቷል፡፡ አብን መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የገዥው ብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የክልል ልዩ ኃይሎችን በሚመለከት ያሳለፈው ውሳኔ፣ በሁሉም ክልሎች ልዩ ኃይሎች ላይ በእኩል ደረጃ ተፈጻሚ የማይሆንና የውሳኔው ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ማስፈታት መሆኑን ስለመገምገሙ አስታውቆ ነበር፡፡ ፓርቲው ከበቂ የሽግግር ጊዜ በኋላ የክልል ልዩ ኃይሎችን አደረጃጀት ማስተካከል እንደሚገባ የሚያምን መሆኑን ገልጾ፣ ጉዳዩን ከሕጋዊነት፣ ከወቅታዊና አገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎች አንፃር በመመርመር ገዥው ፓርቲ ያሳለፈው ውሳኔ ወቅቱን ያልጠበቀ እንደሆነ በመግለጫው አስታውቋል፡፡ አብን ክስተቱ ከተፈጠረ ወዲህ በተከታታይ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ ባደረጋቸው መግለጫዎች፣ ሕወሓት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በተካሄደው የሰላም ስምምነት መሠረት ትጥቅ ባልፈታበት ልዩ ኃይልን ያለ በቂ ዝግጅት፣ ውይይት፣ የጋራ መግባባትና መተማመን ሳይደረስ በድንገትና ያለ በቂ የፀጥታ ዋስትና ለማፍረስ መንግሥት ያሳለፈው ውሳኔና ውሳኔውን ለማስፈጸም እየሄደበት ያለው መንገድ ኃላፊነት የጎደለው ነው ብሏል፡፡ በተመሳሳይ ገዥው ፓርቲና የፌዴራሉ መንግሥት ስህተቱን ከማረምና መፍትሔ ከማፈላለግ ይልቅ፣ በጥፋት ላይ ጥፋት እየጨመረ ችግሩን እያወሳሰበና
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ቡና ላኪዎች በዓለም ገበያ መቀዛቀዝ ሳቢያ የገቡትን ውል እያፈረሱ በመሆኑ በገቢ ላይ ቅናሽ አምጥቷል ተባለ

ቡና ላኪዎች በዓለም ገበያ መቀዛቀዝ ሳቢያ የገቡትን ውል እያፈረሱ በመሆኑ በገቢ ላይ ቅናሽ አምጥቷል ተባለ ባለፉት ወራት 394 የሚሆኑ የግብይት ውሎች አልተፈጸሙም የ2014 የበጀት ዓመት ለኢትዮጵያ የቡና ምርት ኤክስፖርት አፈጻጸም ልዩ የሚባል ዓመት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ዓምና ኢትዮጵያ ወደተለያዩ የዓለም አገሮች ከላከችው ቡና 1.4 ቢሊዮን ዶላር አግኝታለች። ይህ… https://www.ethiopianreporter.com/117568/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የፋይናንስና የፀጥታ ችግር የኅብረት ሥራ ማኅበራትን የውጭ ግብይት ድርሻ ዝቅ ማድረጋቸው ተገለጸ

የፋይናንስና የፀጥታ ችግር የኅብረት ሥራ ማኅበራትን የውጭ ግብይት ድርሻ ዝቅ ማድረጋቸው ተገለጸ በምርት መሰብሰቢያ ወቅት በቂ የፋይናንስ ድጋፍ አለመገኘትን ጨምሮ የኤክስፖርት ምርት በሚመረትባቸው አካባቢዎች ያጋጠመው የፀጥታ ችግር፣ የኅብረት ሥራ ማኅበራት የውጭ ግብይት ድርሻ አፈጻጸምን ዝቅ ማድረጋቸው ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ የኅብረት ሥራ ኮሚሽን የስምንት ወራት ዕቅድ… https://www.ethiopianreporter.com/117505/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ማሽነሪዎችን ከካተርፒላር የሚቀበለው ብቸኛው ቀርጫንሸ ግሩፕ 2.5 ቢሊዮን ገቢ ለማግኘት ማቀዱን ገለጸ

ማሽነሪዎችን ከካተርፒላር የሚቀበለው ብቸኛው ቀርጫንሸ ግሩፕ 2.5 ቢሊዮን ገቢ ለማግኘት ማቀዱን ገለጸ የማሽነሪ ዕቃዎችን ከካተርፒላር ለመቀበል ሙሉ ዕውቅና አግኝቻለሁ ያለው ቀርጫንሸ ቡና ላኪ ቡድን በአንድ ዓመት ውስጥ 2.5 ቢሊዮን ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ፡፡ ቀርጫንሸ ቡና ላኪ ቡድን ዓርብ መጋቢት 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው… https://www.ethiopianreporter.com/117509/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት ለመስጠት የዲጂታል ትምህርት ስትራቴጂ እየተነደፈ መሆኑ ተገለጸ

በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት ለመስጠት የዲጂታል ትምህርት ስትራቴጂ እየተነደፈ መሆኑ ተገለጸ በአበበ ፍቅር ትምህርትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ተደራሽ ለማድረግ የዲጂታል ትምህርት ስትራቴጂ እየተነደፈ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ህዋዌ ቴክኖሎጂ መጋቢት 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና በአይሲቲ ልማት ላይ በሐያት ሪጀንስ ሆቴል ባዘጋጀው የውይይት መድረክ፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂ የመማር… https://www.ethiopianreporter.com/117506/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሻይ ቅጠል ከሚያመርቱ ሦስት ድርጅቶች የሁለቱ ፈቃድ እንዲነጠቅ ተጠየቀ

ሻይ ቅጠል ከሚያመርቱ ሦስት ድርጅቶች የሁለቱ ፈቃድ እንዲነጠቅ ተጠየቀ የቡናና ሻይ ባለሥልጣን ሻይ ቅጠል አምርተው ኤክስፖርት ያላደረጉ ሁለት ድርጅቶች የንግድና የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንዲነጠቅ፣ የሚመለከታቸውን የመንግሥት ተቋማት በደብዳቤ መጠየቁን አስታወቀ፡፡ ሻይ ቅጠል ለማምረት ውል ፈጽመው ከሚሠሩ አርሶ አደሮች ውጪ፣ አምራች ድርጅቶች ሦስት ብቻ መሆናቸውን፣ ከእነሱም… https://www.ethiopianreporter.com/117512/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከስደት ተመላሾች እንዲቆዩበት ቤታቸውን ያከራዩ ክፍያ እየተፈጸመላቸው ባለመሆኑ ቅሬት አሰሙ

ከስደት ተመላሾች እንዲቆዩበት ቤታቸውን ያከራዩ ክፍያ እየተፈጸመላቸው ባለመሆኑ ቅሬት አሰሙ ‹‹የጎርፍና የድርቅ ጉዳይ እያለ ለዚህ ምላሽ የለኝም›› የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሕዝብ ግንኙነት ከዓረብ አገሮች ከስደት ለተመለሱ መጠለያ ለብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ቤታቸውን ያከራዩ ግለሰቦች፣ ክፍያ እየተፈጸመላቸው አለመሆኑንና በቤቶቻቸው ላይ ውድመት ቢደርስም… https://www.ethiopianreporter.com/117516/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በባሌ ዞን የዩራኒየምና የቶሪየም ማዕድናት ክምችት ያደረሰው ጉዳት ካለ ተጨማሪ ጥናት ያስፈልጋል ተባለ

በባሌ ዞን የዩራኒየምና የቶሪየም ማዕድናት ክምችት ያደረሰው ጉዳት ካለ ተጨማሪ ጥናት ያስፈልጋል ተባለ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን መዳወላቡ ወረዳ ዋሬ ቀበሌና በአጎራባች ስድስት ቀበሌዎች አለ የተባለው የዩራኒየምና የቶሪየም ማዕድናት ክምችት በሰውና በእንስሳት ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ቢነገርም፣ እስካሁን የከፋ አደጋ አለማስከተሉን በመግለጽ ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለሥልጣን… https://www.ethiopianreporter.com/117519/
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያን ያካተተ 12 የአፍሪካ ከተሞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመሠረታዊ አቅርቦቶች ጥናት ሊደረግ ነው

ኢትዮጵያን ያካተተ 12 የአፍሪካ ከተሞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የመሠረታዊ አቅርቦቶች ጥናት ሊደረግ ነው ኢትዮጵያን ጨምሮ 12 የአፍሪካ ከተማዎች ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለ የመሠረታዊ አቅርቦቶች ጥናት ሊደረግ መሆኑ ተነገረ፡፡ የአፍሪካ ከተሞች የምርምር ጥምረት ‹‹African Cities Research Consortium (ACRC)›› በኩል ተግባራዊ የሚደረገው ፕሮጀክት፣ ሦስት አንኳር ዋና ላይ ያተኮረ መሆኑን ‹‹ፎረም ፎር… https://www.ethiopianreporter.com/117528/
Posted in Amharic News, Ethiopian News