የአልሸባብ ታጣቂዎች የሶማሊያ የወታደር ልብስን ለብሰው በእስር ቤት ጥቃት መፈፀማቸው ተሰማ።

የአልሸባብ ታጣቂዎች የሶማሊያ የወታደር ልብስን ለብሰው በእስር ቤት ጥቃት መፈፀማቸው ተሰማ።

በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በሚገኝ ከፍተኛ ጥበቃ ባለው እስር ቤት ላይ የአሸባሪው አልሸባብ ታጣቂዎች ወታደራዊ ልብስ ለብሰው በመግባት ጥቃት ፈፅመዋል።

የሶማሊያ መንግስት ጥቃቱን የፈፀሙ ሰባቱም የቡድኑ አባላት መገደላቸውን ሲያስታውቅ አልሸባብ በበኩሉ ሁሉም ሙስሊም ታሳሪዎች ከእስር ቤቱ ወጥተዋል ብሏል።

እስር ቤቱ የአልሸባብ ታጣቂዎች ታስረው የነበረበት ነው ሲባል በጥቃቱ ምን ያህል የፀጥታ አካላት እንደሞቱ የተባለ ነገር የለም።

ጥቃቱ ከመፈፀሙ በፊት የደህነንት ሁኔታው ተሻሽሏል በሚል በሞቃዲሾ የሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ተከፍተው እንደነበርም ተገልጿል።

እስር ቤቱ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንታዊ ቤተመንግስት በቅርብ ርቀት ይገኛል ሲባል የሚተዳደረውም በሃገሪቱ የመረጃና ደህንነት አስተዳደር ነው ተብሏል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።