የትኛውም መንግሥት ወይም ኩባንያ ያለ ሶማሌ ሕዝብ ይሁንታ የኦጋዴን አካባቢን የተፈጥሮ ጋዝ ጥቅም ላይ የማዋል መብት የለውም

አብዲራህማን መሃዲ የሚመሩት የኦብነግ አንጃ፣ ኦጋዴን ውስጥ መንግሥት የጀመረውን የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ላይ የሶማሌ ሕዝብን ያሳተፈ ግልጽ ሂደት እስኪዘረጋ ድረስ እንዲቋረጥ ጠይቋል።

አንጃው፣ የትኛውም መንግሥት ወይም ኩባንያ ያለ ሶማሌ ሕዝብ ይሁንታ የኦጋዴን አካባቢን የተፈጥሮ ጋዝ ጥቅም ላይ የማዋል መብት የለውም ብሏል።

መንግሥት ፕሮጀክቱን የጀመረው፣ የማኅበረሰብ ምክክርና የአካባቢ ደኅንነት ጥበቃና የማኅበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ ሳይደረግ እና ሕጋዊ የሃብት ክፍፍል ስምምነት ላይ ሳይደረስ መሆኑን በመጥቀስም አንጃው ተችቷል።

መከላከያ ሠራዊት በጸጥታ ሽፋን ከፕሮጀክቱ ዙሪያ በርካታ ነዋሪዎችን አፈናቅሏል በማለት የከሰሰው አንጃው፣ ተመድ፣ አፍሪካ ኅብረትና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ጉዳዩን እንዲመረምሩም ጥሪ አድርጓል።