ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ስለወቅታዊው ጉዳይ ይናገራሉ

ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ስለወቅታዊው ጉዳይ ይናገራሉ

”ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አገሪቱን መምራት አለመቻሉን የማይገነዘብ፤ የማንበብ፤ የማዳመጥ አቅምና ችሎታ ያለው ኢትዮጵያዊ፤ ለሚታየው አገራዊ ሽብርና ውድቀት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እኩል ተጠያቂ ነው።”
..
ሻለቃ ዳዊት ወልደ-ጊዮርጊስ
( ዳዊት ወልደጊዮርጊስ የቀድሞ የኢትዮጰያ ውጭ ጉዳይ ም/ሚ/ር፡ የእርዳታ ኮሚሽን ኮሚሽነር፡ የቀድሞው የኤርትራ አስተዳዳሪ፡ የተባበሩት መንግስታት የሩዋንዳ ሚሽን ልኡክና በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ የመካከለኛው ምስራቅናአፍሪካ ተመራማሪ ናቸው )

ኢትዮጵያ እንደ አገር፣ ኢትዮጵያውያን ደግሞ እንደ ህዝብ በቅርብ ጊዜ ታሪካችን አሁን ወዳ’ለንበት የበለጠ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ገብተን አናውቅም። የአገሪቱ ህልውና፣ የህዝባችን አንድነትና ደህንነት ታላቅ ፈተና ላይ ወድቋል። መፃፍና መናገር ያቆምን ወይንም ያልጀመርን ሁሉ ዛሬ ካልተናገርን፣ ዛሬ ካልፃፍን፣ ዛሬ አደባባይ ላይ ወጥተን ካልጮኽን፣ ዛሬ ለአለም መንግስታት አቤቱታችንን ካላቀረብን፣ ማንም እሸናፊ የማይኖርበት – ብዙ ህዝብ የሚያልቅበት፣ የሚፈናቀልበትና የሚሰቃይበት ሁኔታ ውስጥ እንገባለን። አገሪቱን እዚህ ደረጃ ላይ ያደረሷት ፅንፈኞችና የአገር መሪዎች መሆናቸው ግልፅ ቢሆንም፣ በመጀመሪያ ደረጃ ተጠያቂ ሊሆን የሚገባው ግን ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ ነው። እውነት ነው፤ በአሸብራቂና አደንዛዥ ቋንቋ የህዝቡን ያልተቆጠበ ሙሉ ድጋፍ አግኝቶ ነበር። ዛሬ ካስቀመጥነው ማማ ወርዶ ደካማ ወይንም እኩይ እላማ ያለው መሪ ለመሆኑ ያለንበት አስከፊ ሁኔታ በግልፅ ይናገራል።

ጃዋር መሃመድ የሚባል እሸባሪ፣ በአንድ ቀን ብቻ የ67 ሰዎች ህይወት በግፍ እንዲቀጠፍና አገሪቱ በሽብር እንድትጥለቀለቅ አደረገ። በፈጠራ ታሪክ ላይ ተመስርቶ፣ ይህንን ሽብር የፈፀመው – ያስፈፅመው ጃዋር መሃመድ መሆኑ በገሀድ እየታወቀ ይህንን ግልፅ ወንጀል ለማውገዝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እልፈቀደም። እርሱንም ሆነ የድርጅቱን (የOMNን) ስም ጠርቶ ለፍርድ «ይቀርባሉ!» አላለም። ማንንም ስው በህግ ተጠያቂ አላደረገም። ለመሆኑ ምን ዓይነት ጠቅላይ ሚኒስትር ነው ያለን?

ከሰባት ወራት በፊት «A Country on the Brinks/ ኢትዮጵያ፤ አፋፍ ላይ የምትገኝ አገር» በሚል ርዕስ፣ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ፣ እንድ የምርምር ፅሁፍ እቅርቤ ነበር::
ጃዋርን በተመለከተ ከዚህ በታች የሰፈረውን አስተያየት ስጠኹኝ፣
The Jawar Phenomenon
PM Ably seems to have taken a calculated decision to play the ethnic card to perhaps appease the radicals within his party. For certain, his ethnic base is fired up and their expectations are high. His colleague Jawar Mohamed, another fiery demagogue who preaches ethnic and religious extremism has been invited from the USA, Minnesota State, where he was based to operate legally in Ethiopia. Oromo Media Network (OMN) has millions of followers. Despite requests by millions of Ethiopians for the closure of this media out let the PM has never criticized the station let alone order its closure.
Abiy has allowed Jawar Mohamed, the CEO, OMN legally registered in Ethiopia to spread ethnic and religiously motivated hate speech. PM Abiy’s tolerance of Jawar is perplexing. Giving unchecked political power to extremists like Jawar can only further exacerbate the already tense political environment. Some political observers suspect that there is either an explicit or implicit understanding between the PM and Jawar. If that is the case, PM Abiy is allowing Jawar’s extreme voice to influence the youth, particularly in the Oromo region. In any other country Jawar would have ended up in prison and prosecuted for crimes of incitements and possibly for terrorism.
As I wrote in an earlier article, OMN reminds me of Radio Television Libre des Milles Collines (RTLM), the hate radio that was instrumental in the Rwandan Genocide. Its stated aim was �to create harmonious development in Rwandese society� but nothing could have been further from the truth. It was set up and financed by Hutu extremists to prepare the people of Rwanda for genocide by demonizing the Tutsi and encouraging hate and violence. Recognized the danger and asked for international help in shutting down the broadcast. But it was impossible to persuade Western diplomats to take it seriously. They dismissed the station as a joke� General Romeo Dallaire, the Canadian commander of the UN peacekeeping operation in Rwanda at the time of the genocide, said: “Simply jamming [the] broadcasts and replacing them with messages of peace and reconciliation would have had a significant impact on the course of events.” His advice was ignored and the UN and the international community regrets with great humility and embarrassment that, had it acted earlier the genocide would probably have not taken place. There is a red line between freedom of expression and hate speech, oratory and incitement. It is well established in the international legal instruments.
Jawar has been caught on tape telling his crowd threatening Christians. Like the �interhamway�of Rwanda, Jawar has recruited young Oromo�s who call themselves �Querros� to do the dirty work of killing, plundering and creating an atmosphere of fear in the nation. One Ethiopian Mekuria writes on ECDF website:
�The image of Querro youngsters brandishing machetes and other homemade weapons at was a pitiful sight to see. It was reminiscent more of the notorious Boko Haram than the peaceful youngsters with their arms crossed over their heads in protest. That Ethiopians had come to love and appreciate. Querro youngsters are Ethiopian who desire better than being reduced to doing the dirty work of others and getting tarnished in the process. They have camp Jawar to thank for it �
Thousands of Ethiopians have signed a petition to the Minnesota attorney General and US attorney general to �ban OMN media for inciting ethnic violence in Ethiopia and hold its director Jawar Mohamed responsible
Ethiopians are noticeably weary of Prime Minister Abiy Ahmed�s government for failing to control widespread anarchism which seem to emanate from dual power exercised in the country since he became the prime minister of Ethiopia. The �Querro� movement led by Jawar Mohammed is asserting de facto power and disrupting government power in different parts of Ethiopia at will.
ትርጉም:-
የጃዋር ያልተለመደ ሁናቴ
ጠ.ሚ አብይ በተሰላ ውሳኔ፣ በፓርቲያቸው ውስጥ የሚገኙ አፈንጋጮችን ለማባበል የዘውግ ፖለቲካን ካርድ እየተጠቀሙ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት የእርሳቸው የዘውግ መሰረት ተነቃቅቶ፣ የተሰጣቸው ግምት ከፍ ብሏል፡፡ በጋለ ስሜት የዘውግና የሃይማኖት ፅንፈኝነትን የሚያራምደው፣ የእርሳቸው ባልደረባ ጃዋር መሃመድ በህጋዊ መንገድ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲንቀሳቀስ ከአሜሪካ፣ ሚኒሶታ ተጋብዞ መጥቷል፡፡ ኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN) በሚሊዮን የሚገመቱ ተከታዮች አሉት፡፡ ሚሊዮናት ኢትዮጵያውያን ጣቢያው አንዲዘጋ ያቀረቡት ልመና ቢኖርም፣ ጠ.ሚ አብይ አንድም ቀን ጣቢያውን ተችተው አያውቁም፤ ጣቢያው እንደፈለገው እንዲንቀሳቀስ ትተውታል፡፡
አብይ የሚዲያውን ስራ አስፈፃሚ፣ ጃዋር መሃመድና OMNን በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው በዘውግና ሃይማኖት የተቃኘ የጥላቻ ንግግር እንዲያሰራጩ ፈቅደውላቸዋል፡፡ ጠ.ሚ አብይ ጃዋርን መታገሳቸው ግራ ያጋባል፡፡ እንደጃዋር ለመሰሉ ፅንፈኞች ያልተረጋገጠ የፖለቲካ ሃይል መስጠት፣ የፖለቲካውን ምህዳር ውጥረት ይበልጡኑ ከማባባስ በቀር፣ ምንም አይፈይድም፡፡ የተወሰኑ የፖለቲካ ታዛቢዎች እንደሚጠረጥሩት፣ በጠ.ሚውና በጃዋር መካከል፣ ግልፅ የሆነ ወይም ያልሆነ መናበብ አለ፡፡ ነገሩ አንዲህ ከሆነ፣ ጠ.ሚ አብይ የጃዋር ፅንፈኛ አስተሳሰብ ወጣቱን – በተለይ ኦሮሞ ክልል የሚኖረውን – እንዲያነሳሳ ፈቅደዋል ማለት ነው፡፡ በሌላ ሃገር፣ ጃዋር በፈፀመው የማነሳሳት ወንጀል፣ እናም በሽብርተኝነት ተከስሶ፣ ዕድሜውን እስር ቤት ይጨርስ ነበር፡፡
ቀደም ብዬ በፃፍኩት ፅሁፍ፣ OMN የሩዋንዳን የዘር ፍጅት ያጋጋለው የጥላቻ ራዲዮን – Radio Television Libre Milles Collines (RTLM)ን አንደሚያስታውሰኝ ገልጬአለሁ፡፡ የራዲዮ ጣቢያው ዓለም ‹‹የሩዋንዳውያንን ህብራዊ ልማት መፍጠር›› ቢሆንም፣ ዓላማው ግን ከዕውነታው ጋር የተራራቀ ነው፡፡ የተቋቋመውና በገንዘብ የሚደገፈው በሁቱ ፅንፈኞች ሲሆን፣ የሩዋንዳን ህዝብ ጥላቻና ግጭት በመንዛት ለዘር ፍጅት ለማዘጋጀት የታሰበ ነው፡፡ አደጋውን የተረዱ ወገኖች ስርጭቱ እንዲቋረጥ ለዓለም-አቀፍ ማህበረሰብ የእገዛ ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡ ነገር ግን የምዕራብ ዲፕሎማቶችን አሳምኖ፣ ጉዳዩ በአንክሮ አንዲታይ ማስደረግ አልተቻለም፡፡ እንዲያውም ጣቢያውን ከቁብ አልቆጠሩትም፣ ካናዳዊው ጄኔራል ሮሚዮ ዳላየር – በሩዋንዳ የተመድ የሰላም አስከባሪ ሰራዊ አዛዥ – በዘር ፍጅቱ ወቅት – ‹‹ስርጭቱን አስቁመን፣ በሰላምና እርቅ ላይ ያተኮሩ መልዕክቶችን ብናስተላልፍ፣
በሚፈጠሩ ሁኔታዎች ላይ ጉልህ ተፅዕኖ ያሳርፋሉ፡፡›› ብሎ ቢናገሩም፣ ምክራቸው ተቀባይነትን አላገኘም፡፡ ተመድና ዓለም-አቀፉ ማህበረ-ሰብ ቀድመው የዘር ፍጅቱን ለመከላከል እርምጃ ባለመውሰዳቸው፣ ውርደትና እፍረት ጋር ሲፀፅታቸው ይኖራል፡፡ ሃሳብን በነፃነት በመግለፅና በጥላቻ ንግግር፣ በንግግርና በመቀስቀስ መካከል፣ ቀይ መስመር አለ፡፡ በዓለም-አቀፍ የህግ ማዕቀፎች ውስጥ በደንብ ተገልጧል፡፡
ጃዋር ለተከታዮቹ ክርስቲያኖች ስጋት እንደሆኑ ሲናገር ተቀድቷል፡፡ ሩዋንዳ ውስጥ እንደነበረው ‹‹ኢንተርሃምዌይ›› ዓይነት፣ ጃዋር ራሳቸውን ‹‹ቄሮ›› ብለው የሚጠሩ ወጣት ኦሮሞዎችን በመመልመል፣ ግድያን፣ ዘረፋንና በሃገሪቱ የፍርሃት ድባብ ማስፈንን – የመሳሰሉ ቆሻሻ ድርጊቶችን እንዲፈፅሙ አደራጅቷቸዋል፡፡
አንድ መኩሪያ የሚባሉ ኢትዮጵያዊ ECADF ድረ-ገፅ ላይ እንደፃፉት፣
‹‹የቄሮ ወጣቶች ቆንጭራና ሌሎች የቤት ውስጥ መሳሪያዎችን ሲያወዛውዙ የሚያሳዩ ምስሎችን መመልከት፣ እጅግ ይዘገንናል፡፡ እጃቸውን ከጭንቅላታቸው በላይ አጣምረው – በሌሎች ኢትዮጵያውያን ከተወደዱና ከተሞገሱ – ሰላማዊ ሰልፍ ካደረጉ ወጣቶች ይልቅ ጨካኙን – ቦኮ ሃራምን ትዝ ያስብላሉ፡፡ የቄሮ ወጣቶች ኢትዮጵያውያን፣ ነገር ግን የሌሎችን ቆሻሻ ስራ ለመስራትና በዛው ጉዞ መጉደፍ የሚፈልጉ ናቸው፡፡ ዕድሜ ለጃዋር የሚመቻቸውን ሰፈር አግኝተዋል፡፡››
በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ የዘውግ ግጭት የሚቀሰቅሰው OMN ሚዲያ እንዲታገድና ስራ አስፈፃሚው ጃዋር መሃመድ ለሰራው ስራ ተይዞ እንዲጠየቅ›› ፊርማ አሰባስበው ለሚኒሶታ አቃቤ ህግ ፅ/ቤትና ለአሜሪካ አቃቤ ህግ ፅ/ቤት አስገብተዋል፡፡
አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ ጀምሮ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንግስት ከሁለት ሃይል የሚመነጭ የተዛመተ ስርዓት-አልበኝነትን መቆጣጠር ባለመቻሉ፣ ኢትዮጵያውያን በጉልህ ተሰላችተዋል፡፡ በጃዋር መሃመድ የሚመራው የ‹‹ቄሮ›› ንቅናቄ በተጨባጭ የሚታይ ሃይል አሳርፎ፣ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች – በፈቃዱ – የመንግስትን ሃይል እየተፈታተነ ነው፡፡
በዚሁ ፅሁፍ ላይ ነበር የዓለም-አቀፍ መለኪያዎችን ጠቅሼ፣ ኢትዮጵያ እየከሸፈች ያለች ሃገር ( Failed State) መሆኗን ጠቁሜ፣ እስቸኳይ የእርምት እርምጃዎች እንዲወስዱ ያሳሰብኩት። በጊዜው ብዙዎች ተሟግተውኝ ነበር። ዛሬስ ምን ይሉ ይሆን?
በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በማናቸውም የዓለም ክፍል ውስጥ እንደዚህ ያለ ሁኔታ ሲፈጠር፣ በመጀመሪያ ተጠያቂ የሚሆነው መሪው ነው። ሌላውን – በማስረጃ የተደገፈውን ግድፈቱንና ውሸቱን ( በተለይ የውትድርናና የአካዳሚክ ትምህርቱን በተመለከተ) ወደ ጎን ትተን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ እህመድ እገሪቱን መምራት አለመቻሉን የማይገነዘብ የማንበብ፣ የማዳመጥ እቅምና ችሎታ ያለው ኢትዮጵያዊ፤ ለሚታየው አገራዊ ሽብርና ውድቀት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እኩል ተጠያቂ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድፍረት፣ እውቀትና ፍላጎት የለውም። የእርሱ ትኩረት ገፅታውንና ቋንቋውን ማሳመር፣ መስሎ መታየት እንጂ የተናገረውን ወይም ህዝብ የሚፈልገውንና የሚጠብቀውን ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ የሚችል መሪ ሆኖ አልተገኘም። ይህ ወይ ከተፈጥሮ ደካማነት፣ ወይም ደግሞ በፅንፈኞች አላማ ተጠልፎ፣ ተገድዶ ከመሳት ወይም ከአእምሮ መዛባት የመጣ ሊሆን ይችላል። እንደዚህ ያሉ በርካታ መሪዎችን በአፍሪካ አይተናል። «ሁሉን እናውቃለን፣ ለሁሉም መልስ አለን!» ብለው፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያልጨረሱ መሪዎች የፖለቲካ ፍልስፍና መምህር ሆነው ለመታየት በመሞከር አገራቸውን ለውድቀት እንደዳረጉ ብዙ መስክረናል። ሙአመር ጋዳፊ «Direct Democracy» ወይንም «ህዝቡን ከመንግስት ጋር በቀጥታ የሚያገናኝ አዲስ የዴሞክራሲ ስርአት» ብሎ የግሉን ፍልስፍና በመፅሀፍ መልክ አውጥቶ እያንዳንዱ ሊቢያዊ እንደመመሪያ በቃሉ እንዲያጠናው እውጆ ነበር። ( የዚህ መፅሃፍ ሌላኛው ስያሜ «አረንጓዴው መፅሀፍ» የሚል ነው።)
እኔም በአንድ ወቅት ቤንጋዚ የሚገኘው የጋዳፊ ድንኳን ውስጥ ተጠርቼ፣ ስለዚሁ ፍልስፍና የተወሰነ ትምህርት ተቀብያለሁ:: የጋምቢያው መሪ መቶ አለቃ ያህ ያህ ጃሜ፣ «Patriotic Reorientation and Construction» ወይም «አዲሱ የእርበኝነትና የአገር ወዳድነት ስሜት»ን ‘አስተምራለሁ’ ብሎ ተነስቶ፣ ከዚያም አልፎ የአገሪቱ ታላቅ ዶክተር «ነኝ! የኤድስ በሽታን እፈውሳለሁ!» ብሎ፣ በሳምንት እንድ ጊዜ ህዝቡ እያሰለፈ ህክምና ይሰጥ ነበር። ህክምናው የውሸት መሆኑ ቢታወቅም፣ በግልፅ አይነገርም ነበር። ጃሜህ 23 እመት ሙሉ አገሩን ዘርፎ፣ ህዝቡን ጨቁኖ ካበቃ በኋላ ተባርሮ በስደት ወደ ናይጄሪያ ሄደ። የኮንጎው መሪ ጆሴፍ ዲዚሬ ሞቡቱ በፊት ወታደር ነበረ። «Authenticite» በሚል የግል ፍልስፍና የፖለቲካና የባህል አብዮት «አመጣለሁ!» ብሎ ተነሳ። ስሙንም ለወጠ:: «Mobutu Sese Seko Nikki Ngbendu» ብሎ ሰየመ። ትርጉሙም፣ «The all powerful warrior born to win/ ከሁሉም ሃያላን የላቀ፣ ለማሸነፍ ብቻ የተፈጠረ ተዋጊ» የሚል ነው። «የተፈጠርኩት ኮንጎን ለመግዛት ነው።» አለ:: አገሪቱን ለ32 ዓመታት ገዝቶ ዘርፎ፣ አደኽይቶ ለመሰደድ ሲሞክር፣ ሰሜን እፍሪካ ላይ ሞተ::
የደቡብ አፍሪካ መሪዎች የአፓርታይድን ህጋዊነት የሚያፀድቅ ህገ-መንግስትና የፖለቲካ ፍልስፍና አወጡ። የፖለቲካ ፍልስፍናው ጥቁርን ለማግለልና ነጭን የበላይ ለማድረግ ያለመ ስለነበረ፣ ህዝቡ ባደረገው የተራዘመ ትግል ስርአቱ ተገረሰሰ። ኢዲ አሚንም በኡጋንዳ የራሱን ፍልስፍና መስርቶ «አዲሲቱን ኡጋንዳ እፈጥራለሁ!» ብሎ ተነሳ:: አምሳ አለቃ ነበረ፤ ስልጣን በያዘበት ወቅት። ስልጣን ሲይዝ ግን ማዕረጉ « His Excellency President for Life, Field Marshall Ali Haji Doctor Idi Amin Dada, VC MC, Lord of All Beasts of the Earth and Fishes of the Seas and Conqueter of the British Empire in Africa/ የተከበሩ የህይወት ዘመን ፕሬዝደንት፣ ፊልድ ማርሻል አሊ ሃጂ ዶክተር ኤዲ አሚን ዳዳ፣ የድል እና የሰራዊት መስቀል፣ በምድር ላይ የሚገኙ አናብስት እና ባህር ውስጥ ያሉ አሳዎች ጌታ እና አፍሪካ ውስጥ ያሉ የብሪታኒያ ግዛቶች አስመላሽ» ብሎ ራሱን ሰየመ። ከስምንት አመት የጭቆና አገዛዝ በኋላ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተሰድዶ እዚያው አረፈ። መንግስቱ ሀይለማርያምም አገር-ወዳድ ቢሆንም፣ ጨካኝና ኢ-ዲሞክራሲያዊ ርዕዮተ-ዓለም በመከተሉ አገሪቱን ለወያኔ ዳርጎ አመለጠ::
ሌሎቹ መሪዎች እነዚህን የመሳሰሉ በራሳቸው ተክለ-ሰብዕና ላይ ብቻ ያተኩሩ መሪዎችን ገጠመኝ አንብበው ከታሪክና ከምሁራን ከመማር ይልቅ አዲስ የፖለቲካ ፍልስፍና ፈልሳፊ የሚሆኑት ስልጣናቸውን ለማመቻቸትና ከአዋቂዎች በላይ «ነን!» ብለው፣ አምልኮትን ( cult) ለመፍጠር በመፈለግ ነው። ከመሰረታዊ የዴሞክራሲ ጥያቄ ውጪ የራሳቸውን ገፅታና አዋቂነት ለማሳመር፣ ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያራምዱት ይህ የግል የስልጣንና የተመላኪነት ፍላጎት ለአገርም – ለራሳቸውም ሳይበጅ ለአሳፋሪ መንገድ እንደሚዳርጋቸው ታሪክ በጉልህ ያስተምራል።
በአገራችን – በመለስ ዜናዊ ወቅት አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ አሁን ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አገዛዝ «መደመር» ብለው መሪዎች ህዝቡን እያወናበዱት ነው፤ ዴሞክራሲ በተግባርሲተረጎም፣ የአንድን አገር ህዝብ በስብእናው ብቻ እኩል ነፃነትናመብት የሚሰጥ፣ በዘር – በሀይማኖት – በፆታ…ወዘተ..አንዱንከሌላው ለይቶ የማይመለከት የፖለቲካ አስተሳሰብ ነው። ይህ የፖለቲካ አስተሳሰብ በትክክል ከተገበረ፣ ሁሉን ህዝብ አንድያደርጋል። ከክርስቶስ ልደት በፊት፣ ከግሪክ ስልጣኔ ጀምሮ ብዙሊቃውንት የፃፉበት፣ ያስተማሩበት ዛሬ ታላላቅ የሆኑ ዴሞክራቲክ ሀይሎች የደረሱበት ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ያስቻለ የፖለቲካ ፍልስፍናነው።
የዛሬው ወጣት በተስፋና በጉጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይን መደገፉ እንደሞኝነት ተቆጥሮ ሊሆን ይችላል። ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላምና ዲሞክራሲ ለማስፈን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አንደበት በአሸበረቀ እና በማራኪ ቋንቋ የቀረቡት ሃሳቦች ፍቅርና እንድነትን የሚያስተጋቡ ስለነበሩ፣ «እድል እንስጠው!» ብሎ ያልተቆጠበ ድጋፉን ሰጥቷል። ያ ሁሉ ንግግር መና ሆኖ ሲቀር፣ አገሪቱም ወደ ሽብር እየንተራሻተተች ስትሄድ፣ ሌላ አማራጭ ለመፈለግ ይገደዳል።
ዴሞክራሲ አንድ መንገድ ነው ያለው። እንደየአገሩ ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ ሲተገበር ይለያይ እንጂ ሁሉም ዓይነት ዴሞክራሲ በህዝብ አንድነት፣ እኩልነትና ነፃነት ላይ መሰረቱን ጥሎ፣ መሪዎችን በነፃነት የመምረጥ መብት ላይ የተመሰረተ ንድፈ-ሃሳብ ነው። «መደመር፣ መቀነስ!» የሚል የዴሞክራሲ ፍልስፍና የለም።
በዴሞክራሲ አተገባበር ላይ ጥያቄ ቢኖርም፣ አዋቂዎች – ሽማግሌዎች -ተመራማሪዎች – የህዝብ ተወካዮች ይምከሩበት እንጂ የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ቦታ በአጋጣሚ ሰለያዙ ብቻ የፖለቲካና የዴሞክራሲ አስተማሪ ሆኖ መታየት ትንሽነት ነው። ይህ ትኩረት ያጣ አመራር ነው አገሪቱን እዚህ ያደረሳት።
መሪዎች ሁሉን አዋቂ ስለሆኑ እይደለም ለስልጣን የሚመረጡት። እውነተኛ አዋቂዎችን፣ ምሁራንን፣ የአገር ተቆርቆሪዎችን፣ የተለያዩ እስተሳሰብ ያላቸውን ቅን ኢትዮጵያውያንን ሰብስበው የተለያዩ እማራጮች ላይ ተወያይተው ለህዝብ ጥቅም «ይበጃል!» ተብሎ አብዛኛው ወገን የተስማማበት ውሳኔ ላይ መድረስ የሚችሉ ናቸው – ጥሩ «መሪዎች» የሚባሉት። መጥፎ መሪዎች ከእነርሱ አስተሳሰብ ያነሰ እንጂ የላቀ ሊያቀርቡ የማይችሉ፣ በእውቀታቸውም ሆነ በራሳቸው የማይተማመኑ፣ በመሾማቸው ብቻ ተድስተው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለውን ሁሉ ያለአንዳች ትችት የሚቀበሉ አማካሪዎችን የሚሾሙ ናቸው። እነዚህን ይዞ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ወደ ሰባተኛ ንጉስነት እያመራ ያለው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ የኦሮሞ እክራሪዎችን «አይደግፍም!» የሚሉ ብዙዎች አሉ። የኦሮሚያ ክልል ም/ፕሬዚደንት ማለትም የጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ምክትል፣ በአደባባይ አማራን ሙልጭ እድርጎ ሲያወግዝ – ሲዘልፍ ታሪኩን ሲያጎድፍ፣ መሪው ምን አለ? ምንም! ቀደም ብሎ የነበረው የክልሉ ፕሬዝደንት የአዲስ አበባን ዲሞግራፊ ለመለወጥ 500,000 ሺህ የኦሮሞ ተፈናቃዮችን ከሶማሌ ክልል «አምጥቼ በአዲስ አበባ ዙሪያ አስፍሬአለሁ!» ሲል፣ አጠገቡ ተቀምጦ የነበረው መሪው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ምን አለ? ምንም! በቡራዩ፣ በለገጣፎ ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎች ሲጨፈጨፉ፣ ሲገደሉ፣ መሪው ምን አለ? ምንም! ዛሬ የኢትዮጵያ ባንዲራን የያዘ፣ የለጠፈ ሲወገዝ፣ ባንዲራው ከሰውና ከመኪና አልፎ ከቤተ-ክርስትያናት ላይ ሲፋቅ፣ መሪው ምን አለ? ምንም! ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬ ያለው «ሁለት መንግስት ነው። የቄሮና የአቢይ።» ብሎ ጃዋር መሃመድ ሲናገር፣ መሪው ምን አለ? ምንም! አዲስ አበባ የኦሮሚያ «ነች!» ሲባል ከህግ አግባብ ውጪ የተሾመው ታከለ ኡማ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ሲያደርጋት፣ መሪው ምን አለ? ምንም!
ቀን ባለፈ ቁጥር ጠ/ሚኒስትር አቢይ መጨረሻው ከላይ እንደተጠቀሱት መሪዎች መሆኑን ሲገነዘብ፣ ስልጣኑ ላይ ለመቆየት ሲል የበለጡ ስህተቶችን ይሰራል እንጂ ከስህተቱ «ይማራል!» ብሎ ማመኑ በብዙሃኑ ዘንድ አክትሟል። ለዚህም ነው አስቀድመን፣ «ሳይቃጠል በቅጠል» ብለን ስንፅፍ – ስንናገር የከረምነው። አንድ ኢትዮያዊ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰላም የኖቤል ሽልማት ሲያገኝ ደስ ይለናል፤ የመከፋት ስሜት አይሰማንም። ለእውነት ስንናገር ግን ይህ ሰው ሽልማቱ ይገባዋል? የኖቤል ሽልማት ማግኘቱ ስልጣን ላይ ለመቆየት ያለውን ፍላጎት ያጠናክረዋል እንጂ አይቀንሰውም። ዛሬ በአገራችን ውስጥ ሰላም የለም። ከኤርትራ ጋር ያለውም አለመግባባት ህጋዊ ይዘት ባለው ስምምነት አልተቋጨም። ኤርትራም ለጦርነት ያላት ስጋት እልቀነስም። ድንበሩም እንደተዘጋ ነው። ኢትዮጵያ በትግራይ በኩል ባላት ድንበር ላይ ከባድ የስጋት ድባብ እያንዣበበ መሆኑ ይታወቃል። ሰላም ቢፈጠርም እንኳን፣ ( አልተፈጠረም እንጂ) ለሁለቱም መሪዎች እንጂ የኖቤል ሽልማቱ ለአንድ መሪ ብቻ መበርከት አልነበረበትም። ሰላም በሁለት ወገኖች መልካም ፈቃድ የሚመጣ እንጂ በአንድ መሪ ግፊት ብቻ ወይም ፈቃድ የሚገኝ አይደለም።
ሰላምና አንድነት ሊያስገኝ የሚችል መፍትሄ ለመፈለግና ወደ ፊት ለመራመድ ቢያንስ፣ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ እውነታ ላይ መስማማት አለበት። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መምራት አልቻለም። ጃዋርን፣ ኦነግን፣ ኦዴፓን፣ ወያኔን፣ አዴፓን አለማውገዝ ከእውነታ መሸሽ ነው። መፍራት ነው። ዋናው የኢትዮጵያ ችግር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው።
የዛሬ አስር ወር አዲስ አበባ ላይ ባደረግሁት ንግግር፣ «ጠቅላይሚኒስትር አቢይ የኦሮሞ ድርጅት መሪም – የኢትዮጵያም መሪ ሊሆን አይችልም። አንዱን መምረጥ አለበት:: የኦሮሞም – የኢትዮጵያምመሪ ሊሆን አይገባም!» ብዬ ነበር። ደግሜም፣ «ዛሬ የህዝብ ድጋፍ ባለው ወቅት ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ይዞ ደፋር የሽግግር እርምጃዎችን ቢወስድ፣ የኢትዮጵያን አንድነት የሚያስጠብቅ ስላማዊ ሽግግር ሊያስገኝ ይችላል።» ብዬ ነበር። አለበለዚያ ይህች አገር ሌላ ሩዋንዳ «ትሆናለች።» ብዬ፣ እኔን ጨምሮ ሌሎችም ይህንን ሃሳብ አጋርተን ነበር። ዛሬ ወደዚያ እያዘገምን ነው። ሁሉም በእንደዚህ ያለ ለውጥ አይስማማም። ምክንያቱም የተለየ አጀንዳ ያላቸው ይህንን ለውጥ አይፈቅዱም። ይህ ተፈርቶ ግን አገር አይፈርስም። መስዋዕትነቱ አነስተኛ ሆኖ ኢትዮጵያን ማዳን ይቻል ነበር።
ዛሬ የአማራና የኦሮሞ፣ እንዲሁም የትግራይ ጥያቄዎች ላይ አይደለም ውይይታችን ማተኮር ያለበት። ውይይታችን ማተኮር ያለበት፣ «ዛሬ የአገሪቱን ህልውና መጠበቅና የእርስ በእርስ እልቂት ውስጥ እንዳንገባ ምን መደረግ አለበት?» የሚለው ላይ ነው:: ዛሬ ቤተ-ክርስትያናት እየተቃጠሉ ምእመናንና የቤተ-ክርስትያን አገልጋዮች እየተገደሉ፤ መንግስት ግን ይህንን ግፍ ሊያስቆም አልቻለም። የአገራችን ሁኔታ ከዘር ፖለቲካ አልፎ የሀይማኖት ይዘት ማሳየቱ እጅግ አሳሳቢ ነው። መንግስት በጠቅላይ ሚኒስትሩና በኢህአዴግ ስር፣ አገሪቱ ውስጥ ሰላም ለማስፈንና ወደ ዴሞክራሲ ስርእት ለመሸጋገር እይቻልም።
ጠ/ሚር አቢይ ስልጣን ላይ እንደወጣና ከዚያም በኋላ ለመስረታዊ ለውጥ ረቂቅ ፍኖተ- ካርታ ደጋግመን እቅርበን ነበር። አሾፈብን እንጂ ለውይይትም መንገድ አልከፈተልንም። ዛሬ የደረስንበት ደረጃ ደግሞ በዚያ ፍኖተ-ካርታ እንድንሄድ አያስችለንም። ሁኔታው ተለውጧል። መጀመሪያ ቀርቦ የነበረው ሀሳብ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይን የሽግግሩ ማዕከል ያደረገ ነበረ።
አሁን ማድረግ የሚበጀው ምርጫውን ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘም ነው። በዚህ ሁኔታ ምርጫ «ይደረግ!» ማለት ህዝብን ማፋጀት ከመሆኑም በላይ ሁኔታውን ሊያስለውጥ የሚችል ምንም ውጤት አይኖረውም።
የሚቀጥለው እርምጃ ከኢህአዴግ ሌላ አሸጋጋሪ ሊሆን የሚችል፤ ከሶስቱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶችና ክልሎች ( ኦሮሞ፣ ትግራይና አማራ) ውጭ የሆነ ጠ/ሚኒስትር እንዲመረጥ ማድረግ ነው። የዚህም አሸጋጋሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መመዘኛ የኢትዮጵያን እንድነት ከዘር ምንነት የሚያስቀድም፣ ቆራጥና ደፋር ውሳኔዎች በመስጠት አሁን ያለውን የፀጥታ መታወክ በውይይትና በሀይል ለመፍታት የተዘጋጀ፣ ገለልተኛ የሆነ፣ በችሎታና በአገር-ወዳድነት ሚዛን ከተመረጠ ካቢኔ ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን ወደሰላምና ዴሞክራሲ ሊያሸጋግር የሚችል መሆን አለበት። የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አንዱ እጩ ሊሆን ይችላል። ሌላው ምርጫ ደግሞ የአሁኒቱን ፕሬዝደንት አምባሳደር ሳህለ ወርቅ ዘውዴን ማቅረብይቻላል።
የሽግግር መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር ከተወሰነ በኋላ፣ ኢህአዴግ የማንም የፖለቲካ ድርጅቶች አባል ባልሆኑ፣ የአገር ሽማግሌዎች፣የሀይማኖት አባቶች፣ ምሁራን፣ ወጣቶች፣ እክቲቪስቶች፣ ከሁሉም ብሄረሰብ አባላት የተውጣጡ የሰላምና እንድነት ጠበቃዎች የሚገኙበት ብሄራዊ የሽግግር ጉባኤ አቋቁሞ ራሱን ያፈርሳል።
የኢህአዴግ ፓርላማ አባሎች እውነት እገር ወዳድ ከሆኑ ለራሳቸው ጥቅምና ስልጣን ካልቆሙ፣ ኢትዮጵያን የሚያስቀድሙ ከሆነ፣ ይህንን ደፋር እርምጃ መውሰድ ይጠበቅባቸዋል። ይህንን በማድረግ ላለፈው ጥፋታቸው ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይክሳሉ። ልዩና አጣዳፊ ጉባኤ ጠርተው ሳይዘገዩ በሚቀርቡላቸው አማራጮች ላይ እንዲወያዩ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥሪ ያስተላልፍላቸው!
የዚህ የሽግግር ጉባኤ ሚና አዲስ ህገ-መንግስት ማርቀቅ፣ አዲስ ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ ማቋቋምና የእውነት፣ የፍትህ፣ የካሳና የእርቅ ኮሚሽን ማቋቋም፣ ሁሉም በእኩልነትና በነፃነት የሚኖርባትን – ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችል ፍኖተ-ካርታ መንደፍና ለህዝብ ማቅረብ ይሆናል:: ዝርዝሩን ከዚህ በፊት በንግግርም – በፅሁፍም እስቀምጬዋለሁ።
ዓመታት ባለፉ ቁጥር ሁኔታዎች እየተባባሱ፣ እየተወሳሰቡ፣ የህዝቡ ምርጫ እየጠበበ ሄዶ ወደ የእርስ በእርስ እልቂት እናመራለን። ያለፈው አመት ከዛሬው የተሻለ ለለውጥ ምቹ ነበር። ድፍረት እና የአመራር ጥበብ የጎደለው ጠቅላይ ሚኒስቴር እድሉን እልተጠቀመበትም። ሌላ አመት ደግሞ ከቆየን ኢትዮጵያን ፈፅመን ልናጣት እንችላለን።
ጠንካራ፣ ወሳኝ፣ አገር-ወዳድ አዳማጭ ጠቅላይ ሚኒስትር ለሃገሪቱ አስፈላጊ ነው። የሽግግር ጉባኤው ስራውን በሚስራበት ወቅት እዲሱ ጠ/ሚኒስትር አገሪቱ ውስጥ መረጋጋት እንዲኖር የፌደራል ሀይሉን ተጠቅሞ እርምጃዎችን በመውስድ፣ ፀጥታ ማስከበር ዋናው ሀላፊነቱ ይሆናል። ፀጥታን በተመለከተ፣ የክልሎችን ስልጣን መገደብና የፌደራል ሃይሉ በዲሲፕሊን እና በስርዓት የክልሎችን ፀጥታ የሚያስተባብር፣ የሚያጠናክር ሆኖ እንዲሰራ ማዋቀርና መስማማት ብዙ ጥረት ይጠይቃል።
ሁለት መንግስት ሊኖር ስለማይችል የጃዋር መሃመድን እንቅስቃሴ በሀይል ሳይሆን ግለሰቡን ህግ ፊት በማቅረብ እንቅስቃሴውን መግታት፣ አዲስ አበባ የአገሪቱ ዋና ከተማ እንጂ የማንም መናገሻ እንዳልሆነች በፍጥነት ማወጅ ግድ ይላል፤ አዲስ እበባ ላይ ሰላም ከሌለ፣ ማእከላዊ መንግስት ሊሰራም-ሊኖርም እይችልምና:: እነዚህ ሁለት ቁልፍ ጉዳዮች ለሽግግር ወሳኝ ቅድመ-ሁኔታዎች ናቸው። የአዲስ አበባና የጃዋር ጉዳዮች ሳይፈቱ የሽግግር ስራዎችሊጀመሩ አይችሉም። ሲፅፉት ቀላል ነው። ነገር ግን እነዚህን ሁሉ ለመተገበር ብዙ መስዋእትነት የሚያስጠይቅ ጊዜ ውስጥ እንደምናልፍ ጥርጥር የለውም። የዘርና የሀይማኖት ፅንፈኞች ወደ እዚህ ውስብስብ ሁኔታ ውስጥ አገሪቷን ከትተዋታል። ባለው ሁኔታ ከቀጠልን፣ የባሰ እንጂ የተሻለ ጊዜ እንደማይመጣ ግምቴ ነው።
ኢህአዴግ ይህንን ለማስፈፀም ለመከላከያ ሀይሉ ሙሉ ስልጣንሲሰጥ፣ ይህ ስልጣን መስመር ዘልሎ በህዝብ ላይ ጦርነት የታወጀ እንዳያስመስል የሲቪክ ድርጅቶች አብረውት እንዲስሩ፣ ስህተቶችና ግድፈቶችን እንዲጠቁሙና እንዲታረሙ ማድረግም ያስፈልጋል::
ፀጥታውን የማረጋጋቱ ሁኔታ እየተከናወነ ኢህአዴግ የህዝብ ተጠሪዎች ጉባኤ ስብስቦ፣ ( የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያልጨመረ) ከዚህ በፊት ባቀረብኩት ዝርዝር ሀሳብ መሰረት ስለሽግግሩ ሂደት ነፃ የሆነ ውይይት መጀመርና አቅጣጫ መንደፍ፣ በዚህም ወቅት የዓለም-አቀፉን ማህበረ-ሰብ፣ በተለይ የእፍሪካ አንድነት ድርጅት ተመልካቾችን እንዲልክ መጠየቅም አስፈላጊ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ማወቅ ያለበት፣ ይህ አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ የተከፈተው ሽብርና ጉድለት ካለምንም ጥርጥር የውጭ ሃገራት እጅ አለበት። ገንዘብ በገፍ እየገባ ነው። ሰዎችን ህብረተስቡ ውስጥ አስርገው ህዝቡን እያነሳሱ ነው። ይህ ግልፅ ነው። ጃዋርን ብቻ ነጥለን ብንመለከት፣ የውጭ ድጋፍ እንዳለው ወይንም የውጭ መንግስታትና ድርጅቶች ጉዳይ አስፈፃሚ ለመሆኑ ተግባሩ ይገልፃል። ለምንድነው ከዓመት በፊት ገቢውና ድርጅቱ «ይመርመር!» ስንል፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ «እምቢ!» ያለው? ለምንድን ነው እዚህ ሀገር ውስጥ ሁለት መንግስት ነው «ያለው!» («የቄሮና የአቢይ» ብሎ) በይፋ ሲናገር፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝም ያለው? «እኔና ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሁም ለማ መገርሳ ተመካክረን ነው የምንስራው!» ብሎ በይፋ ሲናገር፣ ማስተባበያ ያልተስጠው? ይህ ሁሉ የሚያሳየው ከጃዋር ጀርባ፣ የአቢይ መንግስት ሊገታው የማይችል ሀይል «አለ!» ብሎ ስለሚያምን ነው።
ይህች አገር የሁሉም ካልሆነች የማንም አትሆንም። የኦሮሞ ፅንፈኞች ጊዜና ሀይል ከእኛ ጋር ሰለሆነ ሁሉንም «እንውስድ!» የሚል የስግብግብነት፣ የጀብደኝነት፣ የጠባብነትና የጭካኔ ተግባራቸውን ካላቆሙና አማራን «አዋርደን፣ ገፍተን፣ አሳንሰን እንገዛለን!» የሚለውን እስተሳሰባቸውን በፍጥነት እንዲያቀዘቅዙ ካልተመከሩ፣ የአማራውን ብሄረሰብ ቁጣና መልስ ማንም ምንም ሊመክተው አይችልም፤ እነርሱንም ጨምሮ። የአማራውን አመራር ለማዳከም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ማእከልነት የተሸረበውን ሴራና የተፈፀሙትንም ግድያዎች አስመልክቶ፣ «ማን? እንዴት? ለምን?» የሚሉትን ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመመለስ እስከ አሁን አልፈቀደም። አማራው በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የኖረው፣ የሞተው፣ የታገለው፣ ለኢትዮጵያ ክብር – ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድነትና ነፃነት ነው። ይህንን የአማራ ህዝብ የቆመለትንና የሞተለትን የሺህ አመታት ተጋድሎ ማንም ሊያጎድፈው አይችልም። ዛሬም እንደበፊቱ ለክብሩ፣ ለህልውናው፣ ለኢትዮጵያ እንድነት ከአጋር ብሄረስቦች ጋር ሆኖ ይዋደቃል።
አማራ እንደኦሮሞ ፅንፈኞች ሳይሆን ከአማራነቱ በፊት ኢትዮጵያን የሚያስቀድም ኩሩ ህዝብ ነው። ለኢትዮጵያ ህልውና ለመታገል ግን የራሱ ህልውና መጠበቅ አለበት። ስለዚህም አማራ ተደራጅቶ በተጠንቀቅ ላይ እንዲገኝ ማድረግ ቀዳሚ ተግባር ነው። በታሪክ እንዳየነው ሁሉ ከሌሎች ብሄረስቦች ጋር ሆኖ የኢትዮጵያን አንድነት ያስከብራል። ሁሉም በእኩልነት በአንድ ጠረጴዛ (በኢትዮጵያ ) ዙሪያ ተሰባስቦ የአገሪቱን የወደፊት ዕጣ ይወስናል። አንዱ ከሌላው ያነስ ወይም የበለጠ ሆኖ የማይታይባትን ኢትዮጵያ መመስረት የሚቻለው አንዱ ከአንዱ የበለጠ ሀይል እንደሌለው መረዳት የሚያስችለው የሀይል ሚዛን ሲፈጠር ነው። አማራና የኦሮሞ
ፅንፈኞች ግፍ: ጭካኔና አገር የመበተን ድርጊታቸው ያስቆጣው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ተደራጅቶ የሀይል ሚዛን ለመፍጠር ሲችል ብቻ ነው – ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላምና አንድነት ሊፈጠር የሚችለው።
ስወለድም፣ ሳድግም፣ ስማርም በመንግስት ታላላቅ ሀላፊነት ቦታዎችን ይዤ ስሰራም፣ የራሴንም – የሌላውንም ማንነት ጠይቄ አላውቅም። ጄኔራል ጃገማ ኬሎ፣ ጄኔራል አበበ ገመዳ፣ ጄኔራል ደምሴ ቡልቱ፣ ጄኔራል መርእድ ንጉሴ፤ ታላቅ ሰብእና፣ ታላቅ ችሎታ ያላቸው፤ ግዙፍ፣ የማከብራቸው አለቆቼ ነበሩ። ከጄኔራል መርእድ ንጉሴ ጋር በጣም በቅርበት ሰርቻለሁ። ኦሮሞ መሆናቸውን ያወቅሁት በቅርቡ የመፅሀፋቸው የምረቃ ስነ-ስርአት ሲከናወን ከተመለከትኩ በኋላ ነው። የአለቆቼንም – የወዳጆቼንም – የሰራተኞቼንም ማንነት ጠይቄ አላውቅም። አንጠያየቅም:: አስፈላጊም አልነበረም። ኦሮሞ ብዙ ታላላቅ መሪዎች አሉት – በታሪካችን ዑደት ውስጥ እንዳስተዋልነው። አዲስ ታሪክ መፍጠር እስፈላጊ አይደለም። ብ/ጄኔራል ታደሰ ብሩ የሸፈቱ ሰሞን በመጀመሪያ ሄደው ያነጋገሯቸው እንጭኔ ላይ የሚገኙ የእድገት በህብረት ዘማቾችን ነው። እኔ የእድገት በህብረት አዝማች ስለነበርኩኝ፣ ዘማቾቹን ለማረጋጋት ወደ ቦታው ሄጄ ነበር። ለዘማቾቹ የነገሯቸው የመሬት አዋጁን በመቃወም፣ አዲስ ትግል መጀመራቸውንና ዘማቾችም ይህንን እዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ ተማሪዎችን እንዳያስተምሩ ነው። በደርግ ጊዜ የወጣው የመሬት አዋጅ የተረቀቀው በአዋቂ ኦሮሞዎች – ሀይሌ ፊዳ፣ ዘገየ እስፋው፣ ዶክተር ዲማ ነገዎ በመሳሰሉት ነው። የመሬት አዋጁም በአብዛኛው ወይንም ሙሉ በሙሉ የኦሮሞን ህዝብ እንዲጠቅም ተደርጎ የታወጀ ነው። በንጉሱ ጊዜ የህግ ትምህርት ቤት ተማሪ እያለሁ፣ የእኔ የጥናት ፅሁፍ ይህንን የመሰለ አዋጅ እስፈላጊነቱን የሚመረምር ነበር። ሀይሌ ፊዳና ድርጅቱ – መኢሶን የጄኔራል ታደስ ብሩን አቋም እውግዟል:: ከዚህ የመሬት አዋጅ በኋላ፣ የኦሮሞ ህዝብ ከሌላውህዝብ የተለየ ጭቆናና ግፍ አልተፈፅመበትም።
የኦሮሞ ብሔርተኞች የሀሰት ትርክት ፋብሪካ ዛሬ ላይ ጄኔራል ታደስ ብሩን የኦሮሞ ነፃነት ታጋይ እርብኛ እድርጎ የውሸት ታሪክ ፈብርኮባቸዋል። በነገራችን ላይ ከጄኔራል ታደስ ብሩ ጋር አብረው የሸፈቱት መኮንኖች በቅርብ የማውቃቸው ናቸው። እርሳቸውን ተከትለው የሄዱበት የግል ምክንያቶችንም ጭምር አሳምሬ አውቃአለሁ:: የዋቆ ጉቱም ጉዳይ እንደዚሁ ነው:: እርሱን ይዋጋ የነበረው በጄኔራል ጃገማ ኬሎ የሚመራው የአራተኛ ክፍለ-ጦር ሰራዊት ነበር። ይህ ስው ምን እንደነበር፣ ለምን እንደሽፈተ ለማወቅ፣ የኔን ቃል ሳይሆን የጄኔራል ጃገማ ኬሎን መፅሀፍ ማንበብ በቂ ነው። ዛሬ የኦሮሞን ታላቅነት ለማጋነን በኦሮሞ ብሄርተኞች በኩል፣ ታላቅ የሃሰት ትርክት ፋብሪካ ተቋቁሟል። የማይፋቀው ሃቅ ግን የሃሰት ትርክት ፋብሪካ የማይተካው ዕውነተኛው ታሪካችን በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በመላው አለም የታሪክ ቤተ መፅሃፍት ውስጥ በቀላሉ መገኘቱ ነው።
አርማችን የኢትዮጵያ ባንዲራ፣ ምህላችን ለኢትዮጵያ አንድነት ነበር። ዛሬ ጊዜና እንጭጭ አስተሳሰቦች ዝቅ ብዬ እንዳስብ አስገደዱኝ እንጂ ይህንን ሳላይ፣ « ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ!» እያሉ ባንዲራችንን እያውለበለቡ ከተሰዉት ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ ሲዳማ፣ ጉራጌ፣ ጋምቤላና ኮንሶ…አልቆቼና ወዳጆቼ ጋር አብሬ ሞቼ ብሆን፣ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር። እግዜር እድሜ ሰጥቶ ይህንን ጊዜ እሳየኝ!…ስለዚህ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር ለመሄድ ይህንን ሀሳብ አቅርቤአለሁ!
ዛሬ ወቅቱ «ምን መደረግ አለበት?» የሚል ጥያቄ ስላቀረበልን፣ እኔ በፊናዬ ይህንን ወርውሬአለሁ። ሀሳቤን በሌላ ሀሳብ ሞግቱ! አማራጭ ሃሳቦችን ለውይይት አቅርቡ!
ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ