በአማራ ክልል ላይ አብይ አሕመድ ባወጀው ጦርነት የሚሳተፉ የሕወሓት የጦርና የደሕንነት አበጋዞች ታወቁ

ትህነግ በሰሞኑ ጦርነት ተሳትፏል። ለማሳያ ያህል ከተዋጊው ባሻገር ለፌደራል መንግስት መረጃ እያቀረቡ ያሉ የህወሓት ሰዎችን እንሆ!

በቀጥታ ከሰራዊቱ የተላከው ከስር ቀርቧል!

1ኛ ኮ/ል ተወልደ አጠቃላይ የሕወሐትን የመረጃ ዘርፍ እየመራ ያለ ነው። ይህ ሰው በድርድሩ ወቅት ተደራዳሪ የነበር ሲሆን በአሁኑ ወቅት የአማራን ጉዳይ እያጠናቀረ ለፌደራል መንግስቱ ያቀርባል።

2ኛ ተከስተ የተባለ የህወሓት አባል ብሔራዊ መረጃ ሁመራ ተመድቦ የነበረ ነው። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ሲከበብ የሀምሌ አምስት ኦፕሬሽን ከመሩት መካከል ነው። ወልቃይት ጠገዴ ሰፍረው የሚኖሩ ትግሬዎችን መልምሎ የደህንነት ስራ ያሰራ ነበር። አሁን አማራ ላይ መረጃ አሰባሳቢ ሆኖ ከፌደራል መንግስቱ ጋር እየሰራ ነው።

3ኛ ሲሳይ የተባለ በጌታቸው አሰፋ መዝገብ ተከስሶ የነበረ ሲሆን በጎንደር መተማ የህወሓትን ደህንነት ስራ ሲያከናውን የነበረ ነው። በአሁኑ ወቅትም ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ሳምረ የተባለውን ቡድን እያስገባ ይገኛል። ከፌደራል መንግስቱ ጋር እየሰራ ነው።

4ኛ ገበረ ዮሐንስ የውጭ መረጃ ዳሬክተር የነበረ የህወሓት አባል ነው። በህወሓት የድሮው የጫካ ትግል ጎንደር እና ሁመራ በስለላ የነበረ ሰው ነው። በአሁኑ ወቅት የአማራውን ጉዳይ እየተከታተለ ከፌደራል መንግስቱ ጋር ይሰራል።

5ኛ ሜ/ር ጀነራል ገብሬ ዲላ የፌደራሊስት ሐይሎች በሚል በሐገር ደረጃ አዲስ ኃይል በማደራጀት እየመራ ያለ ሲሆን አማራን ይቃወማሉ የሚላቸውን አማራ ክልል የሚኖሩ አካላት እያገኘ ኃይል እያደራጀ ነው። በዚህ ዘመቻ ተሳታፊ ነው።

ይህ በመረጃ ብቻ ከፌደራል መንግስቱ ጋር እየሰሩ የሚገኙትን ለምሳሌ ያህል ለማሳየት ነው። በጦርነቱ ወቅት ከመከላከያ ሰራዊቱ የተቀነሱት የህወሓት አባላት በአማራ ክልል ተሰማርተዋል። ባለፈው ጦርነት የተሳተፉት በርካታ የህወሓት ሐይሎች ተሳታፊ ናቸው። በዝርዝር እንመጣበታለን።

ባለፈው ጦርነት ሂሳብ እናወራርዳለን ብለው የዘመቱበት አልበቃ ብሏቸው አሁንም ከመከላከያ ጋር ሆነው በርካታ ወንጀሎችን እየፈፀሙ ነው። ወጣቶችን እየረሸኑ ነው።