በትዳር ውስጥ ሆነው ነገር ግን ተለያይተው መኖር የሚባል ነገር በምዕራቡ ዓለም እየተስፋፋ ነው። ለዚህ ምርጫቸው ደግሞ ጥንዶቹ ብዙ ምክንያቶችን ያቀርባሉ። አንደኛው ምክንያት ‘ትዳርንም ላጤነትንም አንድ ላይ ለማስኬድ’ ነው ይላሉ። በሌላ በኩል የበለጠ ነጻነት ይሰጣልም የሚሉ አሉ። ጃፓን ውስጥ እንዲህ አይነቱ ሃሳብ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ ነው። ለመሆኑ በእንዲህ አይነት የትዳር ዘይቤ ው…