ማጀቴ፣ ገምዛ፣ ሸዋሮቢት…!
“…እዚያው ውዬ አሁን ገና መምጣቴ ነው። ማጀቴና ጉምዛ ትናንት እንደነገርኳችሁ ነው። ግርማ የሺጥላ (ነአ) እና የሰሜን ሸዋ ካቢኔ ሰሞኑን ተሰብስበው ይፋት የሚባል አናስተዳድርም፣ ሁልጊዜ ረብሻ ከሚነሣ ልዩ ዞን የሚለው ቀርቶ ምሥራቅ ኦሮሚያ በሉት ተባብለው ወስነው ነበር አሉ። ከዚያ እነ አቢይ ግርማን ገድለው በዚያ ሰበብ ሰሜን ሸዋን ለመጠቅለል ነበር ሃሳባቸው። መጀመሪያ ሰሞኑን የዐማራ ገበሬ እህል መሰብሰብ ሲጀምር ኦነጎቹ መተናኮስ ጀመሩ። መከላከያ ግባ ሲባል ወገቤን፣ አልታዘዝኩም ማለት ጀመረ። ፋኖዎቹ የገባውን ኦነግ ወቅተው ከመሩት።
“…ትናንት በዕለተ ቅዱስ ጊዮርጊስ መከላከያው ከኦነግ ሸኔ ጋር ተቀናጅቶ ወደ ማጀቴ ሄደ። እነ አርበኛ ደራሲ አሰግድ እለቱ ሊቀሰማእታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ነውና ቅዳሴ አስቀድሰን ሳንጨርስ ወደ ውጊያው አንገባም ብለው በእምነት ጸኑ። ቅዳሴው አልቆ፣ ተአምረ ማርያም ሰምተው፣ ተባርከው ወደ ውጊያው ገቡ። ከዚያ በኋላ የሆነውን መከላከያ ተብዬው ይናገር። ቁስለኞች ሳይቀሩ ከሚሴ ውሰዱን እስኪሉ ድረስ ተጨረገዱ።
“…የትናንቱ የማጀቴው እንዲህ አልፎ ትናንት ማታ ዙጢ እና ሸዋሮቢት የኦሮሞ ወታደሮቹ ትንኮሳ ጀመሩ። ወታደሩ ግን አልዋጋም አለ። አዛዦቹ በከዘራ እየመቱ ጭምር ግቡ አሏቸው። ወታደሩ እምቢኝ አለ። የሆነው የመከላከያ አዛዥ በስናይፐር ተሸኘ። መሸ ነጋ፣ ዛሬም ሆነ። መከላከያ ውጊያ ጀመረ። ነገር ግን መብረቅ የቀላቀለ ዝናብ ከየት መጣ ሳይባል አወረደው። ለጥቂት ጊዜ በረደ። አሁን ሸዋሮቢት በዙ 23 ጭምር ገጥመዋል። እንዴት ነው ስላቸው። አብሽሩ ጥሩ እየሄደ ነው እያሉኝ ነው።
“…የጎንደሩም የአምባ ጊዮርጊሱ አይወራም። እንዲያው ዝም፣ ጭጭ ነው። በርታ ነፃ አውጪዬ። በርታልኝ አምበሳዬ። ድሉ የአንተ ነው።
•ገና ገና የሸዋል ገና…!