በቤንሻንጉል ምርጫ ለማካሄድ የጸጥታ ሁኔታውን አስመልክቶ ምርጫ ቦርድ መረጃ ልሰበስብ ነው ሲል ክልሉ ከታጣቂዎች ጋር እርቀ ሰላም ላይ ነኝ ብሏል

ምርጫ ቦርድ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች ምርጫ ለማካሄድ ይቻል እንደሆነ ለመወሰን ስለ ክልሉ ጸጥታ ሁኔታ መረጃ ሊሰበስብ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። ቦርዱ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ባቀረቧቸው ቅሬታዎች ላይ በተደረገው ምርመራ ዙሪያ በዚህ ስምንት በሚጠራው ስብሰባ ይመክራል። ከ22ቱ በክልሉ ከሚገኙት 22 የምርጫ ክልሎች ውስጥ፣ በ17ቱ ምርጫ ክልሎች ባለፈው ሰኔ ምርጫ አልተካሄደባቸውም።
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመንግሥት እጃቸውን የሰጡ ከ1 ሺህ በላይ ታጣቂዎች ባሕላዊ የእርቅ ስነ ሥርዓት እንዳካሄዱ የክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። የአማጺው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ አባላት የሆኑት ታጣቂዎቹ በክልሉ መተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ናቸው ተብሏል። የክልሉ መንግሥት ቀደም ሲል ከታጣቂዎቹ ጋር የባሕላዊ እርቅ ሂደት ለማካሄድ ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል።