የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር ኤርትራ ላይ የሚረጨው መርዝ ቀጥሏል አሉ

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በአገራቸውና መንግሥቷ ላይ ጫና ለማሳደር በውጭ ኃይሎች መርዝ የመርጨት የተለመደ ስልት ቀጥሏል አሉ ሚኒስትሩ በካውንስል ኦን ፎሬይን ሪሌሽን ላይ ሰኞ ጥር 2 በሚሼል ጋቪን የታተመውን መጣጥፍ ጠቅሰው በቲውትር ገጻቸው ትችታቸውን ሰንዝረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ጦርነት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚነሳው ይኸኛው ሐቲት አቀራረቡን ብቻ በአዲስ ስልት አድርጎ በቅርቡ በፎሬይን ፖሊሲ የበይነመረብ መጽሔት ላይ ከወጣው መጣጥፍ ጋር የሚመሳሰል መሆኑን አንስተዋል፡፡
የሐተታው አጠቃላይ ስዕል የውጭ ኃይሎች [አሜሪካ መራሹ ኃይል] በአፍሪካ ቀንድ መጫወት ወይም መቆመር የሚሹበትን እቅድ የሚያንፀባርቅ ስለመሆኑንም ነው የጠቆሙት፡፡
በካውንስል ኦን ፎሬይን ሪሌሽን ላይ የወጣው ጽሑፍ የውጭ ጫና ማበርታትን ያለሙና ከእውነት የራቁ የፈጠራ ክሶችን በኢትዮጵያ መንግሥትና ኤርትራ ላይ ጭኗል፡፡