አሜሪካ ሶማሊያ ላይ የአየር ጥቃት መፈፀሟን አስታውቃለች።


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070

የጦር አውሮፕላንአሜሪካ በሰሜን ሶማሊያ ጋልካዮ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በአልሻባብ ታጣቂዎች ላይ የአየር ጥቃት መፈፀሟን አስታውቃለች።

የአየር ጥቃቱ የደረሰው በትናንትናው ዕለት ሲሆን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ስልጣን ከተቆጣጠሩ በኋላም የመጀመሪያው እንደሆነ ተገልጿል።

አሜሪካ በአልሻባብ ጥቃት ለደረሰበት የሶማሊያ ጦር ድጋፍ ስትሰጥ መቆየቷን የመከላከያ ኃይሉ ቃለ አቀባይ ሲንዲ ኪንግ ተናግረዋል።

በዚህ አየር ጥቃት ያደረሰው የጉዳት ምዘና እየተከናወነ ቢሆንም የመጀመሪያ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ግንም ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት አለመድረሱን ቃለ አቀባይዋ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮን) ጥቃቶችን ገድበዋል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው ወቅት በሶማሊያ የአየር ጥቃቶች እንዲጨምሩ አድርገዋል።

ሆኖም ከስልጣን ሊለቁ ባሉበት ወቅት በሶማሊያ ተሰማርተው የነበሩት 700 ልዩ ኃይሎች እንዲወጡ አዘዋል።

አል-ሸባብ አብዛኛውን ደቡባዊ እና ማዕከላዊ ሶማሊያን የሚቆጣጠር ሲሆን በተመድ በሚደገፈው መንግሥትም ላይ አዘውትሮ ጥቃቶችን ይፈፅማል።