በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰሩ ማናቸውም መገናኛ ብዙሃን ከትግራይ ክልል ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጻረሩ ስያሜዎችን እንዳይጠቀሙ ማሳሰቢያ ተሰጠ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ባወጣው መግለጫ በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም የመገናኛ ብዙሃን ሕወሓትን የትግራይ ክልል መንግስት እንዲሁም በድርጅቱ የሚመራውን ኃይል የትግራይ መከላከያ ኃይል በሚል ስያሜ እንዳይጠቀሙ አሳስቧል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን  ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እድሪስ፣ “ሕወሓትን የክልል መንግስት ማለት እና በክልል ደረጃ የመከላከያ ኃይል የሚል ስያሜ መጠቀ…