በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በደምቢዶሎ የተፈጸመው ግድያ ለሰው ልጅ ሕይወት ያለን ቸልተኝነት ያሳያል – ሂዩማን ራይትስ ዋች


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Boy Publicly Executed in Oromia

Hold Abusive Officials, Security Forces Accountable

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች በደምቢ ዶሎ ከተማ በአደባባይ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ተገድሏል ላለው ወጣት ተጠያቂ የሆኑ የመንግሥት ባለስልጣናት እና የጸጥታ ኃይሎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠየቀ።

 Ethiopian government forces summarily executed a 17-year-old boy in Ethiopia’s Oromia region in broad daylight, Human Rights Watch said today. The public execution of Amanuel Wondimu Kebede underscores the lack of accountability for security force abuses in the country. On May 11, 2021, government forces apprehended and beat Amanuel in Dembi Dollo, a town in the Kellem Wellega zone of western Oromia. A video posted on social media by the town’s administration shows security forces taunting a bloodied Amanuel with a handgun tied around his neck. He was executed in public that day. In the ensuing weeks, the authorities intimidated and arbitrarily arrested other Dembi Dollo residents, including Amanuel’s family members.

የ17 ዓመት ወጣት የነበረው አማኑኤል ወንድሙ ከበደ ግንቦት 3 ቀን 2013 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢ ዶሎ ከተማ ሕዝብ በተሰበሰበበት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መገደሉን የመብት ተሟጋቹ ድርጅት አስታወቋል።

ሂዩማን ራይትስ ዋች እንዳለው የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ታዳጊውን በአደባባይ ከገደሉት በኋላ የታዳጊውን የቤተሰብ አባላት ጨምሮ ሌሎች ነዋሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን በመግለጫው አስታውቋል።

የሂዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር የሆኑት ሌቲሻ ባደር ፥ “ባለስልጣንት ወጣቱን መግደላቸው ለሰው ልጅ ሕይወት ያለውን ቸልተኝነት ያሳያል” ብለዋል።

የአካከባቢው ባለስልጣናትም ወጣቱን በአደባባይ መግደላቸው እና ቪዲዮ መቅረጻቸው ከሕግ በላይ እንደሆኑ እምነት እንዳላቸው ያሳያል ብለዋል።

የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርት : https://www.hrw.org/news/2021/06/10/ethiopia-boy-publicly-executed-oromia