አዲስ አበባ ተሸከርካሪዎች የመጫን አቅማቸውን እንዲቀንሱ የሚያስገድድ መመሪያ ተዘጋጀ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ የህዝብ ትራስፖርት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎች የመጫን አቅማቸውን እንዲቀንሱ የሚያስገድድ መመሪያ መዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል።

አዲሱ መመሪያ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ቢሮው አስታውቋል፡፡

የቢሮው ኃላፊ ኢ/ር ስጦታው አከለ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አዲሱን መመሪያ በተመለከተ ተከታዮቹን መረጃ ሰጥተዋል ፦

– በአዲሱ መመሪያ መሰረት ተሽከርካሪዎች የሚቀንሱበት መጠን ይለያያ አንጂ ሁሉም አይነት የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች የተሳፋሪ ቁጥር ይቀንሳሉ።

– በኢዲሱ መመሪያ መሰረት ታክሲዎች በወንበር ሙሉና እና ከኋላ 3 ሰውና ሃይገሮች (ቅጥቅጦች) በወንበር ልክና ተራርቀው የሚቆሙ 5 ሰዎች እንዲጭኑ ታዟል።

– ባሶች ከዚህ በፊት ከሚጭኑት በ50 በመቶ ቀንሰው እንዲጭኑ።

– የተሽካርካሪዎች የመጫን አቅም ዝቅ ቢልም በታሪፍ ላይ የተለየ ጭማሪ አይኖርም።

– የመመሪያውን ተፈጻሚነት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣንና የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ቢሮ ይቆጣጠራሉ።

– ይህን መመሪያ ተላልፈው በሚገኙ አሽከርካሪዎች ላይ ከ500 እስከ 5ሺ የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ