በየካ ኮተቤ የኮቮድ ህሙማን ማዕከል የኮቪድ ፅኑ ህሙማን መካከል በአማካይ ከአስሩ ስምንቱ ህይወታቸው እያለፈ መሆኑ ተገለፀ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በየካ ኮተቤ የኮቮድ ህሙማን ማዕከል ከሚገኙ የፅኑ ህሙማን መካከል በአማካይ ከአስሩ ስምንቱ ህይወታቸው እያለፈ መሆኑ ማዕከሉ ገለፀ። በኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ የተያዙ ወጣቶችም እየሞቱ እንደሚገኝም ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ሳንባና የፅኑ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም ዶክተር ዳዊት ከበደ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ ከቀን ወደ ቀን በቫይረሱ ምክንያት ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ታማሚዎች ቁጥር ተበራክቷል፤ የሚሞቱ ሰዎችም በዝተዋል። በዚህም በአሁኑ ወቅት ከፅኑ ህሙማን ባለፈ በቫይረሱ የተያዙ ወጣቶችም ህይወት እያለፈ ነው።

እንደ ዶክተር ዳዊት ገለፃ፤ ከዕለት ወደ ዕለት የኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ህሙማን ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ነው። ይሄም ወደ ፅኑ ህሙማን የሚገቡ ሰዎችን ቁጥር እንዲጨምር ያደረገ ሲሆን፤ ምንም አይነት ተጓዳኝ ህመም የሌሉባቸው እድሜያቸው በሃያና ሰላሳዎቹ የሚገኙ ወጣቶችም ፅኑ ህሙማን ክፍል ይገኛሉ፤ ህይወታቸውም እያለፈ ነው።

https://www.press.et/Ama/?p=41934