ዶ/ር ቴድሮስ ህወሓትን ለመደገፍና የጦር መሳሪያ እንዲያገኝ ለማድረግ ያልፈነቀሉት ድናጋይ የለም – ጄነራል ብርሃኑ ጁላ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ኢታማጆር ሹሙ ቴድሮስ አድሃኖምን ሕወሓትን ደግፈዋል ሲሉ ከሰሱ – ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ቆመው እነዚህን ሰዎች ያወግዛሉ ብለን አንጠብቅም። እነሱን ለመደገፍ ሁሉንም ነገር ሲያደርጉ ነበር፤ ጎረቤት አገራት ጦርነቱን እንዲያወግዙ ሲቀሰቅሱ ነበር – ኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ

Ethiopian army accuses WHO chief Tedros Ghebreyesus of backing dissident Tigray region – where he is originally from – and helping their fighters get weapons

ሦስተኛ ሳምንቱን በያዘው በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊትና በትግራይ ክልል ኃይሎች መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውና በሺዎች የሚቆጠሩ መሰደዳቸው እየተነገረ ነው።

https://i.dailymail.co.uk/1s/2020/11/19/09/35859078-0-image-a-7_1605777572322.jpgዶ/ር ቴድሮስ የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ከመሆናቸው በፊት በህወሓት በሚመራው መንግሥት ወቅት የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል።

ቢቢሲ ዋና ዳይሬክተሩ ላይ የቀረበውን ክስ አስመልክቶ ምላሽ እንዲሰጡ ጥያቄ ቢያቀርብም እስካሁን ምላሽ አልሰጡም።

የአገሪቱ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ጀነራል ብርሃኑ ጁላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳሉት ህወሓትን ለመደገፍና የጦር መሳሪያ እንዲያገኝ ለማድረግ ዶ/ር ቴድሮስ “ያልፈነቀሉት ድናጋይ የለም”።

“ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ቆመው እነዚህን ሰዎች ያወግዛሉ ብለን አንጠብቅም። እነሱን ለመደገፍ ሁሉንም ነገር ሲያደርጉ ነበር፤ ጎረቤት አገራት ጦርነቱን እንዲያወግዙ ሲቀሰቅሱ ነበር” ብለዋል ጀነራል ብርሃኑ።

“የጦር መሳሪያ እንዲያገኙ ሲሰራላቸው ነበር” ብለዋል።

ከሦስት ዓመት በፊት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊ ሆነው የተመረጡት ዶ/ር ቴድሮስ፤ የኮሮናቫይረስን ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ በዓለም ዙሪያ ዕውቅናን አግኝተዋል።

በፌደራል መንግሥቱና የትግራይ ክልልን በሚመራው ህወሓት መካከል ለወራት የቆየው አለመግባባትና መካሰስ ባለፈው ዓመት ማብቂያ ላይ በትግራይ ክልል በተናጠል የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ መባባሱ ይታወሳል።

በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ በትግራይ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ በክልሉ ኃይሎች ጥቃት መፈጸሙን በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ማዘዛቸውን ተከትሎ ፍጥጫው ወደ ግጭት አምርቶ ሁለት ሳምንት አልፎታል።