ግብፅ ኢትዮጵያ ግድቧን መሙላት እንዳትጀምር የሚያሳስብ ለፀጥታው ምክር ቤት የላከችው ደብዳቤ የግብፅን ሀፍረተቢስ አካሄድ የሚያሳይ ነው – ጄሲ ጃክሰን

Elias Meseret — አሜሪካዊው የመብቶች ተሟጋች ጄሲ ጃክሰን ግብፅ ሰሞኑን ለተ.መ.ድ የፀጥታው ምክር ቤት ያስገባችው ደብዳቤ ላይ ጥቁር የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ኮሚቴ (Congressional Black Caucus) ተቃውሞ እንዲያሰሙ ጥሪ አቅርቧል! ዛሬ ማምሻውን የደረሰኝ ይህ በጄሲ ጃክሰን የተፃፈ ደብዳቤ እንደሚለው ግብፅ የአሜሪካ መንግስትን፣ የአለም ባንክን እንዲሁም ተ.መ.ድን በመጠቀም የቅኝ ግዛት ውል በ11 የአፍሪካ ሀገራት ላይ ለመጫን እየሞከረች ነው።”አሜሪካ አረብ ሊግ እና ግብፅ ከወጠኑት የቅኝ ግዛት ውልን በጥቁር አፍሪካውያን ላይ ከመጫን እቅድ ራሱን ሊነጥል ይገባል” የሚለው ደብዳቤው ለጥቁር የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ኮሚቴ መሪ ካረን ባስ የተፃፈ ነው።

“ግብፅ ለፀጥታው ምክር ቤት የላከችው ደብዳቤ ላይ ከጠቀሰችው ጉዳይ አንዱ ኢትዮጵያ ግድቧን መሙላት እንዳትጀምር የሚያሳስብ ነው። ይህ የግብፅን ሀፍረተቢስ አካሄድ የሚያሳይ ነው”— ጄሲ ጃክሰን

“ግብፅ የአስዋን ግድብን ስትሰራ የኢትዮጵያን አስተያየት አልጠየቀችም ነበር። ኢትዮጵያ እና ግብፅ በተለያዩ ህጎች ይዳኛሉ ካልተባለ በቀር ግብፅ በፊት ያላደረገችውን ኢትዮጵያ አሁን አድርጊ ልትባል አይገባም”— ጄሲ ጃክሰን

Image

 

Image

Image

Imageመረጃ ቲቪን በተሻለ ጥራት እና ፍጥነት እንድናቀርብ እገዛችሁን እንሻለን።
መረጃ ቲቪን ለማገዝ ይህን ሊንክ በመጫን አባል ይህኑ - JOIN Mereja TV