መገናኛ አካባቢ ዘመናዊ የሆነ የብዙሀን ትራንስፖርት ተርሚናል ግንባታ ሊጀመር ነው።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


መገናኛ አካባቢ ዘመናዊ የሆነ የብዙሀን ትራንስፖርት ተርሚናል ግንባታ ሊጀመር ነው
መገናኛ አካባቢ ዘመናዊ የሆነ የብዙሀን ትራንስፖርት ተርሚናል (public transport hub)ግንባታ ሊጀመር ነው።በሰአት እስከ 30 ሺህ ተጠቃሚዎችን የሚያስተናግደው ተርሚናሉ ከቀላል ባቡር አገልግሎትና ከፈጣን አውቶብስ አገልግሎት ጋር የተሳሰረ መሆኑ ተገልጿል። ምክትል ከንቲባው አቶ ታከለ ኡማ በትዊተር ገጻቸው የመገናኛውን ግንባታ የሚያመለክት አራት ቪዲዮዎችን ለቀዋል።
ቪዲዮዎቹን ከታች ያገኙታል።

የብዙሀን ትራንስፖርት ተርሚናሉ የተሽከርካሪ ማቆሚያና የመንገደኞች መተላለፊያ ድልድይ እንዲሁም ባለ ስምንት ወለል ህንፃም ያካተተ ነው ተብሏል።ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የተርሚናሉ ግንባታ በተለይ በአካባቢውን የሚታየውን መጨናነቅ በመቀነስ በኩልና የህዝብ ትራንስፖርትን በማዘመን በኩል የጎላ ድርሻ ይኖረዋል።