" /> ሙሉ ኃይላችንን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19)ን ጫና ለመቋቋም እናውለው! – (ኢዜማ) | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

ሙሉ ኃይላችንን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19)ን ጫና ለመቋቋም እናውለው! – (ኢዜማ)

ሙሉ ኃይላችንን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19)ን ጫና ለመቋቋም እናውለው!

የኮሮና ቫይረስ ወረረሽኝን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ (PDF )

የዓለም የጤና ድርጅት (WHO) የኮሮና ቫይረስን (Coronavirus Disease2019 “COVID-19”) በመጋቢት 2 ቀን 2012 ዓ.ም ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ መሆኑን አውጇል፡፡ እስከ መጋቢት 14 ቀን 2012 ድረስ በሽታው 195 አገሮችን ያዳረሰ ሲሆን፤ ከ378 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፤ ከ16500 በላይ ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል። ምንም እንኳን በሽታው መድሃኒትም ሆነ ክትባት ገና ያተገኘለት ቢሆንም በሕክምና እርዳታና ክትትል ከበሽታው አገግመው ወደ ቤታቸው የተመለሱ ሰዎች ቁጥር ከ102 ሺህ በላይ ነው። ይህም ሰዎች ተገቢ የሕክምና ዕርዳታ እስካገኙ ድረስና በቂ የቅድመ ጥንቃቄ ዕርምጃዎችን ከወሰዱ የበሽታውን ስርጭት መግታት እንደሚቻል አመላካች ነው። በሽታው በአገራችን መከሰቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ተቋም መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም ባወጡት የጋራ መግለጫ ያሳወቁ ሲሆን እስካሁን አስራ አንድ ሰዎች (ሶስት ጃፓናውያን፣ አንድ እንግሊዛዊ፣ አንድ አውስትራሊያዊ እና 4 ኢትዮጵያውያን) በበሽታው መያዛቸው ታውቋል፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያ የቫይረሱ ወረርሺኝ በማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና የኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ የተለያዩ አደጋዎችን ደቅኗል፡፡

 


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV