" /> የዶ/ር ካትሪን ሐምሊን ቀብር ሥነሥርዓት ተፈጸመ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የዶ/ር ካትሪን ሐምሊን ቀብር ሥነሥርዓት ተፈጸመ

የኢትዮጵያ የፌስቱላ ሆስፒታል መሥራች የዶ/ር ካትሪን ሐምሊን የቀብር ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስትያን ተፈፅሟል።ዶክተር ካትሪን ሐምሊን ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት በመኖሪያ ቤታቸው የአስከሬን ሽኝት ከተደረገ በኋላ የቀብር ስነስርዓቱ ተከናውኗል፡፡
ከመሃንዲስ አባትና ሃሳብ አፍላቂ እናት የተወለዱት ዶክተር ካትሪን ሐምሊን ለቤተሰባቸው ሁለተኛ ልጅ ናቸው፡፡ ዶክተር ካትሪን ሐምሊን በፊስቱላ ህመም ተጠቂ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ላበረከቱት እጅግ ከፍተኛ የሆነ የበጎ አድራጎት የኢትዮጵያ የክብር ዜግነት እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተበርክቶላቸዋል።
ዶክተር ካትሪን ሀምሊን ፌስቱላ ኢትዮጵያ የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት በማቋቋም ከ60 ዓመታት በላይ ለ60 ሺህ ያህል ሴቶች የፌስቱላ ህክምናን ከሰጡ በኋላ በ96 ዓመታቸው መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።

የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV