" /> የኮሮና ቫይረስ በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑን ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተናግረዋል። | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የኮሮና ቫይረስ በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑን ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተናግረዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ቫይረሱ በሁሉም አገራት ሊባል በሚችል ደረጃ በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑን ተናግረዋል።
ዶ/ር ቴድሮስ ከደቂቃዎች በፊት በጄኔቫ በሰጡት መግለጫ “በኮሮናቫይረስ የተያዘው የመጀመሪያው ሰው ሪፖርት ከተደረገ በኋላ፤ የመጀመሪያዎቹ 100 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ለመያዝ 67 ቀናትን ወስዷል” ብለዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊው ጨምረውም፡ “ቀጣዮቹ 100ሺህ ሰዎች የተያዙት በ11 ቀናት ውስጥ ሲሆን፤ ሦስተኛ 100ሺህ ሰዎች የተያዙት ግን በ4 ቀናት ውስጥ ነው” በማለት የቫይረሱን ስርጭት ፍጥነት አመላክተዋል።
ዶ/ር ቴድሮስ ኮሮና ቫይረስን በፍጥነት ለመከላከል የቡድን 20 አባል አገራት መሪዎች በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ እንደሚያቀርቡም አስታውቀዋል።
ምንጭ፡- ቢቢሲ

የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV