በዋሽንግተን ዲ.ሲ. በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ሲካሄድ የነበረው ውይይት ሳይቋጭ ተጠናቋል::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ኢትዮጵያ ሱዳን እና ግብጽ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ሲያደርጉት የነበረውን ድርድርና የረቂቅ የስምምነት ሰነድ ዝግጅት ሳይቋጭ ተጠናቋል

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ እንደገለጹት “የካቲት 4 እና 5/2021ዓም በዋሽንግተን ዲ.ሲ. በኢትዮጵያ በሱዳን እና በግብጽ መካከል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል እና አለቃቀቅን በተመለከተ ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ለማዘጀት ሲካሄድ የነበረው ውይይት በዚህኛውም ዙር ሳይቋጭ ማምሻውን ተጠናቋል::”

የኢትዮጵያ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ በዚህ ሳምንት የሶስቱ አገራት የህግ ባለሙያዎች የደረሱበትን ረቂቅ ስምምነት ዝግጅት በኢትዮጵያ በኩል ለመገምገም ወደ ስፍራው ማቅናታቸው የሚታወስ ነው፡፡