60 የሰቆቃና የለቅሶ ቀናቶች ! …. 2 ወራት ያልተፈታው እገታ !


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


60 የሰቆቃና የለቅሶ ቀናቶች ! …. 2 ወራት ያልተፈታው እገታ !

እያወራን ያለነው ስለ ዜጎች ደሕንነትና ስለ ሰብዓዊ መብት እንጂ ስለ ፖለቲካ አይደለም። ተማሪዎቹ የት ናቸው የሁሉም ጥያቄ ነው።

የደምቢዶሎ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ከታገቱ ሁለት ወር ሞላቸው። ከወላጆች ለቅሶና ከተማሪዎች ሰቆቃ እንግልት እንዲሁም ከመግለጫና ከተስፋ በስተቀር ምንም የታየ አዲስ መፍትሔ የለም።

የመንግስት ግዴለሽነት በሕዝብ ጫና ከላላ በኋላም ከፕሮፓጋንዳ ውጪ ምንም ተግባራዊ ፍንጭ የተጨበጠ ውጤት አልታየም። እያወራን ያለነው ስለ ዜጎች ደሕንነትና ስለ ሰብዓዊ መብት እንጂ ስለ ፖለቲካ አይደለም።

የታገቱ ተማሪዎችን የማፈላለጉ ስራ ከቄለም ወለጋ ባለፈ እስከ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ድረስ በመዝለቅ በመፈለግ ላይ መሆኑን ሰራዊቱ ምን አልባት የጠፉትን ልጆች ወደ ድንበር እና ወደ ጎረቤት አገሮች የማሸሽ አዝማማያ ሊኖር ይችላል በሚል ጥርጣሬ አሰሳ እያከናወነ እንደሚገኝ መከላከያ ሰራዊቱን ጠቅሶ አዲስ ማለዳ አስነብቦናል።

ይህ የሚያሳየው መንግስት ምንም መረጃ እንዳሌለው ወይንም ሆን ተብሎ የሚድበሰበስ መረጃ በመንግስት መዋቅር ውስጥ እንዳለ አመላካች ነው።

ከደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ጠፍተዋል የተባሉትን የተማሪዎች ዝርዝር በመውሰድ ተማሪዎቹ እስከ አሁን ያሉበት ባለመታወቁ እና የተማሪዎች ቤተሰብም መጥፋታቸውን በማመልከቱ ፍለጋው ተጠናክሮ መቀጠሉ ተሰምቷል። ባለፉት ሁለት ወራት መንግስት ምንም አይነት ስራ አለመስራቱን በግልፅ እያየን ነው። ተማሪዎቹ የት ናቸው የሁሉም ጥያቄ ነው። #MinilikSalsawi