ብልጽግና ፓርቲ የህዝብ ፍላጎት የወለደው ነው – የሲዳማ ዋና አስተዳዳሪ

የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፤
– ብልጽግና ፓርቲ የህዝብ ፍላጎት የወለደው መሆኑን ገለጹ
– በሲዳማ ክልል የፓርቲው ቅርንጫፍ እንደሚከፈት አስታወቁ

(ኢ.ፕ.ድ)
የብልጽግና ፓርቲ እየተበራከቱ የመጡ የህዝብ ፍላጎቶችን መመለስ በሚያስፈልግበት ወቅት የተወለደ ፓርቲ መሆኑን የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ገለጹ፡፡ የሲዳማ የክልልነት ሂደት ሲጠናቀቅም በክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት እንደሚከፈት አስታውቀዋል፡፡

ዋና አስተዳዳሪው አቶ ደስታ ሌዳሞ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ባለፉት ሶስት ዓመታት በርካታ የህዝብ ፍላጎቶች ታይተዋል፤ ጥያቄዎችም ተነስተዋል፡፡ ይህን ሊመልስ የሚችል ቁመና ያለው ፓርቲ አስፈላጊ እንደመሆኑም የብልጽግና ፓርቲ ወቅቱ የፈጠረው ፓርቲ መሆኑ እሙን ነው፡፡

የብልጽግና ፓርቲን በመመስረት ሂደትም የሲዳማ ተወላጅ የደኢህዴን አባላት ተሳታፊና የውሳኔው አካል እንደመሆናቸው የሲዳማ የክልልነት ሂደት ሲጠናቀቅ በፓርቲው ሕገ ደንብ መሰረት የፓርቲው ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በክልሉ ይኖራል፡፡

ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/Ama/?p=23460


► መረጃ ፎረም - JOIN US