Blog Archives

አትሌት መሰረት ደፋር 500 ሰዎችን የሚያስተናግድ ሕንጻ ለለይቶ ማቆያነት እንዲውል ፈቀደች።

አትሌት መሰረት ደፋር 500 ሰዎችን የሚያስተናግድ ሕንጻ ለለይቶ ማቆያነት እንዲውል ፈቀደች። አትሌት መሰረት ደፋር መገናኛ አካባቢ እያስገነባች ያለውን ባለ 12 ወለል ሕንጻ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ለለይቶ ማቆያነት እንዲያገለግል ማስረከቧን ኢዜአ ዘግቧል። ሕንጻው በሳምንት ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚደረግ ታውቋል። ወርርሽኙን ለመቋቋም ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም አትሌቷ በዚሁ ጊዜ ተናግራለች።  
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ምርጫ ቦርድ የቅንጅት መስራች አባላት ስም ዝርዝርን እንዲያጣራ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጥያቄ አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ( ቅንጅት) መስራች አባላት ስም ዝርዝርን እንዲያጣራ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጥያቄ አቀረበ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀድሞ አዋጅ ተመዝግበው የሚገኙ የፓለቲካ ፓርቲዎች በአዲሱ ህግ ላይ ተቀመጡትን መስፈርቶች እንዲያሟሉ መጠየቁ ይታወሳል፡፡ በዚህም መሰረት ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ በአዲሱ አዋጅ በተደነገገው መሰረት 7,214 ( ሰባት ሺህ ሁለት መቶ አስራ አራት) ተጨማሪ መስራች የፓርቲ አባላትን አስፈርሞ እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ እነዲያቀርብ ተገልጾለት ነበር፡፡ ፓርቲው ጥር 26 ቀን 2012 ዓ.ም ከ8 ክልሎች የተሰበሰበ የመስራች አባላት ፊርማ የያዘ ሰነድ ለቦርዱ አቀርቧል፡፡ በመሆኑም የቀረበው ሰነድ ላይ የሚከተሉትን ቦርዱ አስተውሏል፡፡ -ቦርዱ ከእያንዳንዱ ገጽ ላይ በተወሰደ እና ወካይ ሊሆን የሚችል ናሙና ባደረገው ማጣራት፣ ጥሪ ካደረገባላቸው 50 ፈራሚዎች መካከል፣ አንዱ ብቻ ፈርሞ ሲገኝ 49ኙ ግን በተለያየ ምክንያት ፊርማቸውን አለማኖራቸውን አረጋግጧል።( አብዛኛው የተሳሳተ ስልክ ነው፣ አልፈረምኩም የሚሉ ምላሾችና የማይሰራ መስመር ሆነው ተገኝተዋል) -የፓርቲው ማመልከቻ ላይ የፓርቲው ሊቀመንበር ቢፈርሙም፣ የተሰበሰበው ፊርማ ቃለ መሃላ ላይ የፈረመው ሌላ ግለሰብ መሆኑን፣ ሃላፊነቱም አለመገለጹን -የአያት ስም ያላስመዘገቡ፣ ስለአባልነታቸው በፊርማቸው ያላረጋገጡ፣ እድሜ፣ ጾታ፣ የምዝገባ ቀናቸው የማይታወቅ ፈራሚ ስሞችም በጉልህ ተገኝተዋል፡፡ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና አዋጁን ለማስፈጸም የወጣው አዋጅ መሰረት በአባልነት ያልተመዘገበን ሰው የተመዘገበ በማስመሰል የሌለን ሰው እንዳለ ማስመሰል ሃሰተኛ ስምና ፊርማ ማዘጋጀት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ በአዋጁ መሰረት ቦርዱ ሊወስድ ከሚችላቸው ምዝገባን ከመከልከልና ከማገድ በተጨማሪ አግባብ ባለው የወንጀል
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

በአወዳይ በመንግሥት እና በተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች መካከል ግጭት ተከሰተ

በአወዳይ ከተማ በመንግሥት እና በተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች መካከል ግጭት መከሰቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። BBC Amharic : ዛሬ ጠዋት የጠቅላይ ሚንስርት ዐብይ መንግሥት እና ፓርቲን ለመደገፍ የከተማዋ ነዋሪዎች አደባባይ የወጡ ሲሆን፤ በተቃራኒው ደግሞ የጠቅላይ ሚንስትሩን መንግሥት በመቃወም መፈክር እየሰሙ የወጡ ሰዎች እንደነበሩ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ የፖሊስ ባልደረባ ለቢቢሲ እንደተናገረው “ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን ለመደገፍ ሰዎች ሰልፍ ወጡ። ከዛ ለምን ለድጋፍ ወጣችሁ የሚሉ ሌሎች ሰዎችም መውጣት ጀመሩ። ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚያወግዝ መፈክር በማሰማት ድንጋይ መወርወር ጀመሩ” በማለት የግጭቱን አጀማመር ያስረዳል። በደንጋይ ተመተው እና በዱላ ተደብድበው ጉዳት የደረሰባቸው ብዙ ሰዎች መኖራቸውን የፖሊስ አባሉ ተናግረዋል። ይህ የፖሊስ ባልደረባ እንደሚለው ከሆነ፤ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተከሰተውን ግጭት ለመበትን ፖሊስ በርካታ ጥይት ወደ ሰማይ መተኮሱን ተናግረው፤ በፖሊስ ኃይል በተተኮሰ ጥይት ጉዳት የደረሰበት ሰው ስለመኖሩ የማውቀው የለም ብለዋል። ሌላው የከተማዋ ነዋሪ “ባለፉት ቀናት የአከባቢው የመንግሥት ባለስልጣናት ‘ለጠቅላይ ሚንስትሩ ድጋፋችሁን ለመግለጽ ሰልፍ ውጡ’ እያሉ ነዋሪዎችን ሲያስጨንቁ ነበር” ይላል። ይህ የአወዳይ ከተማ ነዋሪ እንደሚለው ከሆነ ዛሬ ጠዋት ላይ ሰዎች ለድጋፍ ሲወጡ እነሱን የሚቃወሙ ሌሎች ሰዎችም አደባባይ መውጣት ጀመሩ። “በዚህ መካከል ከየት መጡ ሳይባል በርካታ የጸጥታ ኃይል አባላት ከተማዋን ወረው ግርግር ተፈጠረ ከዚያም ወደ ግጭት ተገባ” በማለት ይናገራል። ይህ የከተማዋ ነዋሪ እንደሚለው ከሆነ ድጋፍ ለመስጠት አደባባይ ወጡ የተባሉት ሰዎች ወደው እና ፍቅደው ሳይሆን በደረሰባቸው ጫና ነው ይላል። ቢቢሲ
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

የመጨረሻ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የታላቁ የኅዳሴ ግድብ ድርድር ሊካሔድ ነው

DW : የኢትዮጵያ፣ የግብፅ እና የሱዳን ምኒስትሮች፣ ጠበቆች እና ባለሙያዎች “የመጨረሻ” ይሆናል ተብሎ ለሚጠበቀው የታላቁ የኅዳሴ ግድብ ድርድር ዋሽንግተን ዲሲ ገቡ። የሶስቱ አገሮች ልዑካን ከዚህ ቀደም ባደረጉት ድርድር ባስቀመጡት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ጥር 19 እና 20 ቀን 2012 ዓ.ም. በአሜሪካ ይወያያሉ። የኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ ስለ ግድቡ ውኃ አሞላል እና የወደ ፊት የሥራ ክንውን በሱዳን ዋና ከተማ ኻርቱም ባለፈው ሳምንት የተዘጋጀ የሥምምነት ረቂቅ እንደሚገመገም በትዊተር ገፃቸው ገልጸዋል። ምኒስትሩ እንዳሉት በኻርቱም የተዘጋጀው የሥምምነት ረቂቅ ከዚህ ቀደም ድርድር በተደረገባቸው ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ ነው። ግድቡ ውኃ የሚሞላባቸው ምዕራፎች፤ በግድቡ የሚከማቸው የውኃ መጠን፤ ድርቅ እና የድርቅ አስተዳደር፤ የሶስቱ አገሮች የመረጃ ልውውጥ እና የትብብር ጉዳዮች ቴክኒካዊው ድርድር ያካተታቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ስለሺ በቀለ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ምኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ፤ የውኃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ እንዲሁም የምኅንድስና እና የሕግ ባለሙያዎች ያካተተው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በትናንትናው ዕለት ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ማቅናቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ገልጿል። በግብፅ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ሳሜሕ ሽኩሪ የሚመራው የልዑካን ቡድን ወደ አሜሪካ ማምራቱን መስሪያ ቤታቸው ትናንት ገልጾ ነበር።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ሀበሻና ሚኒሊክ የጃዋር ገበያ ናቸው። (ታዬ ደንደኣ)

የፖለቲካ ጨዋታ – Taye Dendea Aredo Tapha Siyaasaa… 3 Qoreen abbaa dhaabe waraana! Mammaaksa Oromooti! Gidiraan maree booda abbuma galaafata jechuufi! Kaleessa gumaa baasuuf akka qabsooftu ifaan himatte! Ummata nagayaa fi jaalalaan waliin jiraataa ture jidduutti sabummaa fi amantiin shakkii dhalchite! Abidda hamaa lafa nagayaatti qabsiifte! Gaafa abiddichi laboobu ammoo qaama biraa komatuutti kaate! Yakka ofii raawwatte nama biraatti maxxansuu duraan baratte! Garuu amma yeroon dhugaa dhiyaatte! እሾህ የሚወጋው የተከለውን ሰው ነው። የኦሮሞ ተረት ነው። ተንኮል መልሶ ባለተንኮሉን ነው የሚጎዳው ለማለት ነው። ትላንት ደም ለመመለስ እንደምትታገል ተናገርህ ነበር። ትናንት በአንድነት እና በፍቅር የሚኖርን ህዝብ እምነት እና ብሄር ከፋፍለህ እንዲጠራጠር አደረግክ። እሳቱ ሲነሳ ደግሞ ሌላ ሰው ተጠያቂ አደረግክ። ራስህ የሰራኸውን ወንጀል ለሌላ ሰው ማላከክ ትናንት የለመድከው ነው። አሁን የእውነት ጊዜ ተቃርባለች። Bara dheeraaf diraamadhaan Oromoo harkaa horii funaante! Amma garuu yeroon sun tarte. Diraamaa tolchanii deggarsa Oromoo shamatuun hafte. Namuu ajandaa kee barate! “Habashaa fi Minilik” gabayaa keeti! Gaafa deggarsi Oromoo sirraa laafe ganama kaatee “Habashaa fi Minilik” jettee arrabsoo gadhiisuun kaampii gamaa dallansiifta! Durriyyees bittee of arrabsiifta! Gaafa dubbiin oo’ite horii funaansa seenta! Akkasiin miira sabaa kakaasaa fayyaalessa elmatta! Icitiin gaafa dhiyoo Ameerikaatti raawwate reefu bahe. Arrabsoo fi mormii akka feetu ofii himatte! Mee maaliif daandii nagayaa dhiiftee “Karaa Habashaan
Posted in Ethiopian Drama, Ethiopian News

የብልጽግና ጽንሰ-ሀሳብ ቁሳዊ፣ መንፈሳዊና ስርዓታዊ በማለት በሶስት ይከፈላል – ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

ኢዜአ  – የብልጽግና ዋነኛ ማጠንጠኛ ኃብት ወይም ጥሪት ማፍራት ነው የሚሉት አያሌዎች ናቸው። በምሁራን አስተያየት ግን ይህ እውነት አይደለም። ኃብት ማፍራት የብልፅግና መገለጫ ከሆኑት መሰረቶች መካከል አንዱ እንጂ ብቸኛው የብልፅግና ማመልከቻ እንዳልሆነ ነው ምሁራኑ የሚያብራሩት። በምሁራኑ አተያይ አንድ አገር ወይም ማህበረሰብ አደገ ወይም በለጸገ የሚባለው ማህበራዊ፣ ምጣኔ ኃብታዊና ፖለቲካን ጨምሮ አጠቃላይ ሁኔታዎቹ ላይ የላቀ እድገት በማስመዝገብ በዜጎች ሁለንተናዊ ህይወት ላይ እርካታ ሲፈጠር ነው። ይህንን ተከትሎም ለአጠቃላይ ሰብአዊነትና የሰው ልጅ ደህንነት የሚቆረቆር በስነ-ልቦና የዳበረ አእምሮ መፈጠሩ ሲረጋገጥ ማህበረሰቡ በልፅጓል ወይም በብልፅግና ጎዳና ላይ ነው ሊባል ይችላል ይላሉ ምሁራኑ። ”ብልጽግና የዜጎች ሥጋዊ፣ የስምና የነጻነት ፍላጎቶችን በቀጣይነት ማሟላት እንዲችሉ አቅማቸውን ማሳደግ ነው” የሚለው ይህ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፃ ሀሳቡን የበለጠ ያዳብረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዲግሪ የፍልስፍና ተማሪው ዮናስ ዘውዴም ብልፅግና ዘርፈ ብዙና ሁለንተናዊ እድገት መሆኑን ይገልፃሉ። ወደ ብልጽግና ለመጓዝ የሚከናወኑት ተግባራት ሁሉን አቀፍና እርስ በእርሳቸው በእጅጉ የተቆራኙ ናቸው ይላሉ። ይሁንና ቅደም ተከተልም ሊኖራቸው ይገባል ባይ ናቸው አቶ ዮናስ። ‘በኛ አገር ምንድነው ያጣነው ምግብ፣ መጠለያ፣ ነጻነት ወይስ እኩልነት’ የሚለው መነሻ በትክክል ሲመለስ የብልፅግና ጎዳናን ያዝን ሊባል ይችላል ይላሉ አቶ ዮናስ። በተለያዩ መፅሃፎቻቸውና በሚያስተጋቡት መንፈሳዊና ማህበራዊ ትንተናቸው የሚታወቁት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በበኩላቸው የብልጽግና ጽንሰ-ሀሳብ “ቁሳዊ፣ መንፈሳዊና ስርዓታዊ” በማለት በሶስት ይከፍሉታል። ቁሳዊ ብልጽግና አንድ ሰው በህይወት ሲኖር ለመኖር አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ሲሟሉለት የሚያገኘው ሲሆን
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

የኢራንና አሜሪካንን ፍጥጫ ተከትሎ የነዳጅና ወርቅ ዋጋ ጨምሯል ተባለ

BBC Amharic : ኢራን፤ ኢራቅ ውስጥ የሚገኝ የአሜሪካ ወታደሮች መጠለያን በሚሳዔል ካጠቃች በኋላ የነዳጅ ዋጋ መናሩ ታውቋል። የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ1.4 በመቶ ጨምሮ በእስያ ገበያ አንድ በርሜል በ69.21 ዶላር [2220 ብር ገደማ] እየተሸጠ ይገኛል። የወርቅ ዋጋም ቢሆን ከሚሳዔል ጥቃቱ በኋላ መናር መጀመሩ ታውቋል። መካከለኛው ምስራቅ ሊያጋጥም ይችላል ተብሎ ከተሰጋው ቀውስ ጋር በተያያዘ፣ የዓለም አቀፍ ገበያዎች የአክሲዮን ዋጋ በተቃራኒው እየቀነሱ መምጣታቸው ተነግሯል። የኢራን መንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ ጥቃቱ አሜሪካ ጄኔራል ቃሲም ሶሌይማንን በመግደሏ ለሱ ምላሽ ይሆን ዘንድ ነው ብሏል። አርብ ዕለት በአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት የተገደሉት ሱሌይማኒ ቀብር በትላንትናው ዕለት ከተፈፀመ ከሰዓታት በኋላ ነው ኢራን ሚሳዔሏን ወደ አሜሪካውያን መንደር የላከችው። የሰውዬው ሞት በኢራንና ዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን ውጥረት አጡዞት ነገሮች ወደሌላ አቅጣጫ እንዳያመሩ ስጋት ጭሯል። በዓለማችን እጅግ በርካታ ነዳጅ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ የውቅያኖስ ውስጥ ነዳጅ ማሳለጫ በሁለቱ ሃገራት ውጥንቅጥ ችግር እንዳያጋጥመውም ተሰግቷል። ሳዑዲ አራቢያ፣ ኢራቅ፣ ዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስ እና ኩዌትን የመሳሰሉ ነዳጅ አውጭና ሻጭ ሃገራት በኢራንና አሜሪካ ግርግር ምክንያት ምጣኔ ሃብታቸው እንዳይጎዳም ስጋት አለ። ኢራንም ቢሆን ለነዳጅ ሽያጯ የምትጠቀመው መስመር የሆርሙዝ ማሳለጫን ነው። የዓለማች ግዙፍ የተጣራ ነዳጅ አምራች የሆነችው ካታርም ብትሆን የሆርሙዝ ማሳለጫን በመጠቀም ነው ነዳጇን የምትቸበችበው። ከሚሳዔል ጥቃቱ በኋላ የአሜሪካ አየር ትራንስፖርት ባለሥልጣን አውሮፕላኖች በኢራን፣ ኢራቅና በአካባቢው የአየር ክልል እንዳይበሩ አስጠንቅቋል። ዕገዳው ኦማን እና ሳዑዲ አራቢያንንም የሚያካትት ነው። አሁን ከተባባሰው የኢራንና
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

የ600 ብር ፓስፖርት ለማግኘት እስከ 50 ሺህ ብር ጉቦ እንደሚጠየቁ ተገልጋዮች ተናገሩ

አዲስ ፓስፖርት ለማግኘት እንዲሁም ለማደስ የሚወስደው ረጅም ጊዜ ለሙስና በር መክፈቱ ታወቀ፡፡ ተገልጋዮች አገልግሎቱን ለማግኘት እስከ 50ሺ ብር ጉቦ እየተጠየቁ ነው፡፡ The long wait for renewing passports has opened room for brokers, dealers and government employees to take bribes in order to speed up the process of getting a passport. People are being asked to pay up to 50,000 birr as a bribe for a new passport. Normally a passport costs 600 birr. No photo description available. Read Full story : https://www.capitalethiopia.com/featured/passport-slowdown-means-more-corruption/
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ከ3ኛ ፎቅ ተማሪ ተወርውሮ መገደሉን ተከትሉ ላልተወሰነ ጊዜ ተዘጋ

ለድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ ዩኒቨርሲቲያችን ሰኞ ታህሳስ 20/2012 ዓ/ም ሊጀመር የነበረው ትምህርት ባጋጠመን ወቅታዊ ችግር ምክንያት በዩኒቨርሲቲያችን ትምህርት ማስቀጠል የሚያስችል ሁኔታ አለመኖሩን ተረድቷል:: ስለሆነም የመማር ማስተማር ሂደቱ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ የዩኒቨርሲቲ ሴኔት ወስኗል:: ስለሆነም ዩኒቨርሲቲው ከታህሳስ 20/2012 ዓ/ም በኋላ ምንም አይነት አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን እየገለጽን የተማሪዎችን የመልሶ መቀበያ ጊዜ ወደ ፊት በሚዲያ የሚገልጽ መሆኑን ወስኗል:: Image ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ አመት ተማሪ ከ3ኛ ፎቅ ህንፃው ተወርውሮ በመሞቱ እስከሚቀጥለው ድረስ ተጨማሪ ማስተማሪያ የመማር ማስተማር ሂደቱን አቁሟል ፡፡ ይሁኔ አለማየሁ የ3 ኛ ዓመት የባንክ ተማሪ ነበር።በሁለት ወራት ውስጥ በተመሳሳይ ከፎቅ ተወርውሮ ተማሪ ውስጥ ሲገደል 2ኛ ጊዜ ነው ፡፡ Image Image የሟች ተማሪ አስከሬን በነገው እለት ወደ ወለጋ ጉሊሶ የሚላክ መሆኑ ታውቋል ። ተማሪ ይሁኔ ከሞተ በኋላ በዩንቨርስቲው ውስጥና ውጪ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። በርካታ ተማሪዎች ዩንቨርስቲውን ለቀው የወጡ ሲሆን ከፊሎቹ ቀደም ብለው የገብርኤልን አመታዊ ንግስ ለማንገስ ወደ ቁልቢ ተጉዘዋል። #Ethiopia:#DireDawa Univ suspended teaching-learning process until further notice after a 3rd year student was thrown off a 3rd floor of a building to his death. Yihune Alemayehu was a 3rd year Banking student. It's the 2nd time a student is killed in the same univ in two months. pic.twitter.com/7O4nD67zUS — Addis Standard (@addisstandard) December 28, 2019  
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በዓለም ተፅዕኖ ከፈጠሩ 50 ግለሰቦች አንዱ ሆኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በዓለም ተፅዕኖ ከፈጠሩ 50 ግለሰቦች አንዱ ሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ፋይናንሺያል ታይምስ ጋዜጣ ከፈረንጆቹ 2010-2019 በነበሩት 10 ዓመታት በዓለም ላይ ለውጥ በማምጣት ከተጠቀሱት 50 ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ዝርዝር ተካትተዋል። 1ኛ) በፖለቲካው መስክ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ቱኒዚያዊው ሞሃመድ ቡአዚዝ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜሪከል የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሳዑዲው አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሃመድ ቢን ሳልማን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቻይናው መሪ ዢ ዥንፒንግ እና ሌሎችም ተካትተዋል። 2ኛ) በምጣኔ ሀብት፣ በቢዝነስና በቴክኖሎጂ፦ የአማዞን ኩባንያ ባለቤት ጄፍ ቤዞስ የአፕል ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቲም ኩክ ቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ የአውሮፓ ማዕከላዊ ባንክ ፕሬዚዳንት ክርስቲን ላጋርድ ቻይናዊው ስራ ፈጣሪ ባለሃብት ጃክ ማ የፌስቡክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማርክ ዙከርበርግ እና ሌሎችም ተካትተዋል። 3ኛ) በባህል፣ በሚዲያ፣ በስፖርት እና በሳይንስ ዘርፍ፦ ሊዮኔል ሜሲ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ አሜሪካዊቷ ሙዚቀኛ ቴይለር ስዊፍት የሜዳ ቴኒስ ንግስቷ ሴሬና ዊሊያምስ እና ሌሎችም ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ተካትተዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ምንም የተጀመረ የውህደት ንግግር የለም:: ዘገባው መሰረተ ቢስና የሐሰት ነው – አቶ ናትናኤል ፈለቀ የኢዜማ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

– ብልፅግና ፓርቲና ኢዜማ በጋራ ጥምር መንግስት ለመመስረት ቅድመ መግባባት ላይ ደረሱ – ዘገባው መሰረተ ቢስና የሐሰት ነው – አቶ ናትናኤል ፈለቀ በብልፅግናና በኢዜማ ከፍተኛ አመራሮች መሃል የተደረሰው ሚስጥራዊ ንግግር ውህደት ሳይሆን ከምርጫው በኋላ አንዳቸው መንግስት መመስረት የሚያስችል መቀመጫ ባያገኙ በጋራ ጥምር መንግስት ለመመስረት ቅድመ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ነው። የኢዜማ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ናትናኤል ፈለቀ ዘገባው መሰረተ ቢስና የሐሰት ነው ሲል አስተባብለዋል። ኃላፊው እንደገለጹት ዘገባውን አስመልክተው ይመለከተዋል ላሉት ግለሰብ ሪፖርት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። መረጃውን ያደረሱን ምንጮች እንዳሉት ጠሚ አብይና ፕ/ር ብርሃኑ ይህን የተስማሙት የብልፅግና የፖለቲካ ፕሮግራም ከየትኞቹም ብሄር ተኮር ፓርቲዎች በተሻለ ከኢዜማ ፕሮግራም ጋር መቀራረብ ስለሚታይበት በመንግስት ምስረታ ሂደት ላይ እንቅፋት የሚሆኑ ጉዳዮች አይኖሩም በሚል እሳቤ ነው።እነዚህ ሚስጥራዊ ውይይቶች መደረጋቸውን የሁለቱ ፓርቲዎች በርካታ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ጭምር አያውቁም። ከ ምርጫ 97 በኋላ ቅንጀት አዲስ አበባን አለመረከቡ ስህተት እንደነበር ጠ/ሚ አብይ ለረጅም ጊዜ ፊት ለፊት ከሚቀርቡት ሰዎች ጋር ይሞግት እንደነበር አንድ ምንጭ  ነግረዋል። አሁንም ብልፅግናና ኢዜማ አዲስ አበባን ጠቅልለው ለማሸነፍ የምርጫ ግብግብ ውስጥ የሚገቡ ቢሆንም ጠ/ሚ አብይ ግን ኢዜማ በርካታ መቀመጫዎችን ቢያሸንፍም ስጋት ይሆናል ብሎ ስለማያስብ ስውር ድጋፍ እያደረገላቸው ይገኛል። ምንጮች እንዳሉት ። የኢዜማ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ናትናኤል ፈለቀ ዘገባው መሰረተ ቢስና የሐሰት ነው ሲል አስተባብለዋል። ኃላፊው እንደገለጹት ዘገባውን አስመልክተው ይመለከተዋል ላሉት ግለሰብ ሪፖርት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። በትዊተር ገፃቸውም
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

የለማ መገርሳ የጠለፋ ፖለቲካ አይሳካም – ስዩም ተሾመ

ኦቦ ለማ መገርሳ የመደመር ፍልስፍናን ሆነ በፓርቲዎች መዋሃድ እንደማይስማሙ ገልፀዋል። የኦዴፓ ምክር ቤት ውህደቱን በሚያፀድቅበት ግዜ በአካል መገኘታቸውን ጭምር ገልፀዋል። በእርግጥ በውህደቱ ሂደት ላይ ይህን ያህል የጎላ ተፅዕኖ አሊያም ግድፈት ይኖራል የሚል እምነት የለኝም። በዚህ ረገድ የሰፋ ክፍተት ቢኖር ኖሮ እንደ ድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር ችግሩን ለመፍታት ጥረት ማድረግ አሊያም ደግሞ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን አቋም በይፋ መግለፅ ነበረባቸው። በተመሣሣይ በመደመር ፍልስፍና አለማመን መብታቸው ነው። በኦዴፓ ከፍተኛ አመራሮች መካከል የሃሳብ ልዩነት መኖሩን እንደ ልዩ ክስተት ሊወሰድ አይገባም። ይሁን እንጂ ነገሮች በሂደት አልፈው ጫፍ ላይ ከደረሱ በኋላ “ከመጀመሪያው ጀምሮ አልደግፍም፥ አልስማማም ነበር” ማለት በአጭር ቃል አይነፋም። አሁን ላይ የተቃውሞ ድምፅ ማሰማት ውህደቱን ለማደናቀፍ ካልሆነ በስተቀር መሠረታዊ የሆነ የአቋም ልዩነት መኖሩን አያሳይም። መሠረታዊ የሆነ የአቋም ልዩነት ከነበረ ደግሞ መጀመሪያውኑ አልስማማም ብሎ የራስን መንገድ መከተል ይሻል ነበር። በአለቀ ሰዓት እንዲህ ያለ ነገር ውስጥ መግባት ያው የተለመደ የመጠላለፍ ፖለቲካ ነው። ይሄ ደግሞ ወያኔና ጃዋርን ከማስደሰት በቀር የሚያመጣው ለውጥ ያለ አይመስለኝም። ይሄም ቢሆን የአንድ ሰሞን የጨበራ ተስካር ነው። ዋናው ነገር ውህደቱ እውን ይሆናል። የኢትዮጵያም ሰላምና አንድነት ይረጋገጣል። ሀገርና ህዝብን ዋስትና አስይዞ የፖለቲካ ቁማር መጫወት አብቅቷል።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

የ9ኙ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽነሮች በሀዋሳ ከተማ የጋራ ዉይይት አደረጉ፡፡

“በታላቅ ጽናት ህዝባችንን ከማንኛዉም የወንጀል ጥቃት እንከላከላለን!”በሚል መሪ መልዕክት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሺን፣የ9ኙ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽነሮች በሀዋሳ ከተማ የጋራ ዉይይት አደረጉ፡፡ “በታላቅ ጽናት ህዝባችንን ከማንኛዉም የወንጀል ጥቃት እንከላከላለን!”በሚል መሪ መልዕክት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሺን፣የ9ኙ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽነሮች በሀዋሳ ከተማ የጋራ ዉይይት አደረጉ፡፡   የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻዉ ጣሰዉ የዉይይት መድረኩን በይፋ በከፈቱበት ወቅት በ2011ዓ.ም በወንጀል መከላከልም ሆነ በምርመራ መስክ የተመዘገቡት ድሎች እንዳሉ ሁሉ መታረም የሚገባቸዉ የተለያዩ ችግሮች እንዳጋጠሙ አንስተዋል፡፡ በ2012 ዓ.ም በየአካባቢ ያሉ የጸጥታ ችግሮችን ነቅሶ በማዉጣት እና ሁሉ አቀፍ የማረሚያ መንገዶችን መተግበር እንደሚገባም ኮሚሽነር ጀነራሉ አሳስበዋል፡፡ የፖሊስ ኮሚሽነሮቹ በህገ-ወጥ የሰዎች ዝዉዉር እና በጦር መሳሪያ ዝዉዉር፣በአደንዛዥ ዕፅ ቁጥጥር፣በገንዘብ እና በኮንትሮባንድ ዝዉዉር ዙሪያ በ2012 ሩብ ዓመት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትንም ገምግመዋል፡፡ በወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ከማዋል አንጻር፣የፖሊስ አባላት የአመለካከት፣የክህሎት እና የአቅም ግምባታ ጋር ተያይዞ በተሰሩ ስራዎች ላይም ሰፊ ዉይይት አድርገዋል፡፡ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ተኮላ አይፎክሩ በቀጣይ የሀገሪቷን የህግ የበላይነት ፣የህዝቡን ሰላም እና ደህንነት በተጠናከረ መልኩ ለማረጋገጥ እንዲሁም ለልማት ምቹ የሆነ አካባቢ ለመፍጠር በትጋት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ የወንጀል ተጠርጣሪዎችን አድኖ በቁጥጥር ስር ለማዋል በፌደራል ፖሊስ የወጣዉ ኦፕሬሽናል እቅድ ተከትሎ የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣የደቡብ እና የሱማሌ ክልል ፖሊስ የተሻለ ዉጠት ያስመዘገቡ መሆናቸዉ ተነግሯል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

በኦሮሚያ ክልል ስራ አጥ ወጣቶች ለእኩይ አላማ አራማጆች መጠቀሚያ ሆነዋል ተባለ።

ሥራ አጥነት የጸጥታ ችግሩን እንዳባባሰው ተገለፀ (ኢ.ፕ.ድ) በምዕራብ ኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ባለመስፋፋቱ በብዛት ወጣቱ ተምሮ ሥራ አጥ መሆኑንና ሂደቱም በእኩይ ተግባር ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ዓላማ እንዲከተሉ ማድረጉን የምዕራብ ወለጋ ዞን አስታወቀ። የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ኤሊያስ ኡመታ በተለይ ከጋዜጣው ሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ በቅርቡ የተወሰደውን መረጃ ዋቢ በማድረግ በምዕራብ ወለጋ ብቻ የመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ያላቸው ወጣቶች ቁጥር ከስድስት ሺህ በላይ ደርሷል። በዚህ የተነሳ አንዳንድ ወጣቶች በእኩይ ተግባር ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ዓላማ መከተላቸውን እና የጸጥታ ችግሩ እንዲባባስ ማድረጉን ያነሱት የዞኑ አስተዳዳሪ ችግሩን ለመቅረፍ ከሰላም ማስከበር ጎን ለጎን የስራ እድሎች የሚሰፉበት አቅጣጫ ተይዞ እየተሰራ ነው ብለዋል። ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/Ama/?p=21155
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ያልተለወጠው የፖለቲካ ባህል በኢትዮጵያ – ውይይት

DW : የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሁኔታ በትኩረት ከሚከታተሉ አንዳንዶች የመክበብ ፖለቲካ ሲሉት፣ አንዳንዶች ሕዝቡ ለውጥ ብሎ የመጣውን ሁሉ እያመነ በተስፋ የሚመለከት፣ መንግሥት ሥልጣን ላይ ትኩረት አድርጎ የሕዝብን አደራ ችላ የሚልበት አካሄድ እንዳለው ይናገራሉ። https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/FEE703AA_2_dwdownload.mp3 ለአንዳንዶች ደግሞ ትግሉ በማን እና በማን መካከል ነው የሚለውን ለመግለፅ የማይቻል ውል አልባ ነው። ሁሉንም የሚያስማማው ግን አሁንም የሀገሪቱ የፖለቲካ ባህል ባለበት የሚረግጥ፤ ጫፍ እና ጫፍ ተቆሞ መጓተት፤ መቧደን የበዛበት አይነት መሆኑ ነው። ከ50 ዓመታት በላይ ለተጨቆነው ሕዝብ ለውጥ ለማምጣት የተደረጉ ትግሎች ምንም አላስገኙም ማለት አይቻልም። ሆኖም ግን መሠረታዊው እና ሁሉም የሚመኙት፤ እኩልነት እና ፍትህ የሰፈነበት አስተዳደር የመመሥረቱ ነገር ግን አሁንም ከፍላጎት አልፎ እውን የመሆኑ ጉዳይ ረዥም መጓዝን እንደሚጠይቅ እየታየ ነው። የሃሳብ ልዩነት ዛሬም እንደ1960 እና 70ዎቹ ያፋጥጣጥ፣ ያፈራርጃል። ውሎ አድሮ ሊመጣ የሚችለውን በመስጋት አብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል የመለኮት ኃይልን ጣልቃ ገብነት የሚመኝበት እውነት በገሀድ ይታያል። በዚህ መሃል ኅብረተሰቡ ለውጥ የተሻለ ነገር ለማየት ይመኛል። ያልተለወጠው የፖለቲካ ባህል በኢትዮጵያ የዚህ ሳምንት የእንወያይ ርዕሰ ጉዳይ ነው DW
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

“ህወሓትን የሚተካ የፖለቲካ ኃይል የለም” – አቦይ ስብሃት ነጋ

BBC Amharic : አቶ ስብሃት ነጋ በትጥቅ ትግሉ ወቅት ከተራ ታጋይ እስከ ከፍተኛ የህወሓት አመራር የደረሱ ግለሰብ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ፤ ‘በክብር’ ከተሰናበቱት ባለሥልጣናት መካከል አንዱ ናቸው።በትጥቅ ትግሉ ወቅት ስለነበራቸው ሚና እንዲሁም ስለወቅታዊ የኢትዮጵያ የፖለቲካዊ ሁኔታ ከቢቢሲ ትግርኛ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ቢቢሲ፡ ህወሓት ከተመሠረተበት ግዜ አንስቶ በክብር እስከተሰናበቱበት ድረስ አመራር ላይ ነበሩ። ከልምድዎ እጅግ የሚኮሩበት ወይም እንዲህ ባደርግ ኑሮ ብለው በግል ወይም እንደ ድርጅት የሚቆጩበት ነገር አለ? አቦይ ስብሃት፡ እንደ ድርጅት ድክመት አልነበረብንም አልልም፤ ብዙ ድክመቶች ነበሩብን። በግልም ስህተቶችን አልፈፀምንም አልልም። እኔም በግሌ አንዳንድ ስህተቶችን ፈጽሜያለሁ፤ ሆኖም በቅጽበት ይታረም ነበር። የሓኽፈን ውጊያ የኔ ስህተት ነበር ውጊያው ድል አልነበረም። ግን በፍጥነት ተምረን በፍጥነት ነበር የምናርመው። ከድክመት እንማር ነበር፤ በድልም የመርካት ሁኔታ እንዳይኖር እንማርበት ነበር። በድል መስከር አይገባም። የኢትዮጵያ መጻኢ ታሪክ ተጽፏል፤ ፕሮግራም ላይ ሰፍሯል። ከዚሁ በመነሳት ነው ‘ትግሉ ረጅምና መራራ ነው፤ ድል ግን አይቀሬ ነው’ ነው የተባለው። ቢቢሲ፡ ሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ሥርዓቱ በሙስና በስብሷል ይሉ ነበር። እርስዎና ቤተሰብዎ ግን በሙስና ትታማላችሁ ምን አስተያየት አለዎት? አቦይ ስብሃት፡ ሙስና ቀስ እያለ የሚመጣ ችግር ነው። ሙስና አለ በሚለው ላይ ‘መጠኑ ትንሽ ነው፤ አይደለም መጠነ ሰፊ ነው’ የሚል ክርክር ነበር። ይብዛም ይነስም ምልክቱ ሲታይ ቶሎ መታረም ነበረበት። ኋላ ላይ እያደገ መጥቶ ሙስናን መጸየፍ እየደከመ መጣ። ሙስና የሥርዓታችን ዋነኛው ጠላት ነው
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የ2019 የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡

VIDEO ዘንድሮ ለዘርፉ ከቀረቡ እጩዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና የ16 ዓመቷ ስዊድናዊት የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋች ግሪታ ተንበርግ በሰፊው ያሸንፋሉ የሚል ግምት ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከ20 ዓመት በፊት ደም አፋሳሽ የነበረውንና በርካታ ሰዎች ያለቁበትን የኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት መቋጫ እንዲያገኝ አድርገው ሰላም በማውረዳቸውና ምስራቅ አፍሪካ የትብብር ቀጠና እንዲሆን ያደረጉት ድፕሎማሲያዊ ጥረት የኖቤል ሽልማቱን እንዲያሸንፉ ጉልህ ሚና ተጫውቷል ተብሏል፡፡ በተለይም ወደ ደም መፋሰስ እየገባች የነበረችው የሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች ተደራድረው የስልጣን ክፍፍል በማድረግ ወደ ሰላም መመለሳቸውም ትልቅ ዋጋ የሚያሰጥ ስኬት ተደርጎም ተወስዷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአንድ ቀን 350 ሚሊዮን ችግኝ ማስተከላቸውና በእርሳቸው አመራር የካቢኔያቸውን ግማሹ በሴቶች እንዲያዝ ማድረጋቸውም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲቸራቸው ያደረገ መሆኑን የፖለቲካ ጠበብቶች ግምታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በተለያዩ መስኮች ጉልህ ተግባራቶችን ያከናወኑ ግለሰቦችን ተቋማት በየዓመቱ የሚሸለሙበት የኖቤል ሽልማት በአለማችን ከሚሰጡ ሽልማቶች መካከል ቀዳሚው ነው፡፡የኖቤል የሰላም ሽልማት እስካሁን ለ133 ግለሰቦችና ተቋማቶች ተሰጥቷል፡፡ እ.ኤ.አ 1938 ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ለኖቤል ሽልማት መታጨታቸው የቢቢሲ መረጃ ያሳያል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኖቤል ሽልማትን በማሸነፋቸው 9 መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም 9 ሚሊዮን የስዊድን ክሮነር ይበረከትላቸዋል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ኢትዮጵያን ወደ ገበያ-መር ኢኮኖሚ ማስገባት የተሻለ እና አስፈላጊ ነው ተባለ

DW : መቀመጫዉን በእንግሊዝ ሀገር ያደረገዉ «ኮንትሮል ሪስክ» የተባለዉ የምጣኔ ሀብት አማካሪ ድርጅት  በጎርጎሮሳዊዉ መስከረም 23 ቀን 2019 የተወሰኑ የአፍሪቃ ሀገራትን  የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት በተመለከተ ዓመታዊ  ዘገባ አዉጥቷል። ድርጅቱ ባወጣዉ የ2019 የአፍሪካ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ስጋትና ዉጤታማነት ጠቋሚ መረጃ በኢትዮጵያ፣ በአንጎላና በደቡብ አፍሪቃ የተደረጉ የማሻሻያና የለዉጥ አጀንዳዎች  በሀገራቱ የምጣኔ ሀብትና የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ላይ ያሳደሩትን ተፅዕኖዎች መርምሯል። https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/7A2D6512_2_dwdownload.mp3 ዘገባዉ በአፍሪቃ ሀገራት መካከል ያለዉን አፈፃጸም  ከአህጉሪቱ ነባራዊ ሁኔታ አንጻር በመለየትም  ለመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ተስፋ ሰጪ የሆኑ የገበያ ዕድሎችንና አደጋዎችን በንፅፅር አቅርቧል። በዚህ መሰረት ባለሀብቶች መዋዕለ ንዋያቸዉን በኢትዮጵያ ቢያፈሱ በዋናነት ከህዝብ ብዛቷ አንጻር በከፍተኛ ደረጃ ዉጤታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ አመልክቷል። በዚያዉ ልክም በሀገሪቱ ዉጤታማ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰትን ሊገድቡ የሚችሉ ስጋቶች መኖራቸዉን ገልጿል። ለሀገራት ከተሰጠዉ አስር ነጥብ ኢትዮጵያ በመዋዕለ ንዋይ ፍሰት አዋጭነቷ አንፃር ስምንት ነጥብ የተሰጣት ሲሆን የስጋት ደረጃዋም በዚያዉ መጠን ከፍተኛ መሆኑ ነዉ በዘገባው የተመለከተዉ። Äthiopien Währung Birr (DW/Eshete Bekele Tekle) ምንም እንኳ የስጋት መጠኑ ካለፈዉ 2018 ጋር ሲነፃጸር በዜሮ ነጥብ አራት መቀነስ ቢታይበትም ከፍተኛ ስጋት ይታይባቸዋል ከሚባሉ ሃገራት ማለትም፦ ዲሞክራቲክ ኮንጎን እና ደቡብ ሱዳንን  ከመሳሰሉ የአፍሪቃ ሀገራት ተርታ ነዉ ኢትዮጵያ የተመደበችዉ። የዉጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የገንዘብ ተቋማት የአሠራር ድክመት እንዲሁም የሀገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ ለስጋቱ መጨመር በምክንያትነት ተቀምጧል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያዉ አቶ ጌታቸዉ ተክለማርያም በሪፖርቱ የተጠቀሰዉ የስጋት መጠን መንግስት ከፍተኛ ሥራ መስራት እንዳለበት የሚያመላክት ነዉ ይላሉ። ኢትዮጵያ በመዋዕለ ንዋይ ፍሰት
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ፌስቡክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ10 የአፍሪካ ሀገራት ሀሰተኛ መረጃዎችን መቀነስ የሚያስችለውን ፕሮግራም ጀመረ

ፌስቡክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ10 የአፍሪካ ሀገራት ሀሰተኛ መረጃዎችን መቀነስ የሚያስችለውን ፕሮግራም ጀመረ! ፌስቡክ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች በሚገኙ ሀገራት በዛምቢያ ፣ ሶማሊያ ፣ ቡሪኪና ፋሶ ፣ ኡጋንዳ ፣ ታንዛኒያ ፣ በዲሞክራሲያዊ ረፐብሊክ ኮንጎ ፣ ኮትዲቫር ፣ ጊኔ ኮናክሬ እና ጋና ነው ሀሰተኛ መረጃዎችን መቀነስ የሚያስችለውን ፕሮግራም ነው የጀመረው:: ሶስተኛ ወገን መረጃ ማጥሪያ የተሰኘው ይህ ፕሮግራም ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመቀነስ የሚያስችል መሆኑን ፌስቡክ አስታውቋል:: ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፆችን መዝጋት፣ እውነተኛ የዜና አማራጮችን ማስተዋወቅ እና የማያስፈልጉ መልዕክቶችን ለሚልኩ አካላት የገንዝብ ድጋፍ የሚያደርጉትን መከላከል ይህ ፕሮግራም ከሚያከናውናቸው አሰራሮች ውስጥ ይካተታሉ ተብሏል፡፡ Via FBC
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ኢሕአዴግ ስሙን ከመቀየሩ በፊት ከስሕተቱ ይማር !!!

ከስም ለውጥ በፊት ስር ነቀል የመዋቅርና የፖሊሲ ለውጥ ሊጀመር ይገባል። ( ምንሊክ ሳልሳዊ) ኢሕአዴግ ስሙን ከመቀየሩ በፊት ከስሕተቱ ይማር !!! ከስም ለውጥ በፊት ስር ነቀል የመዋቅርና የፖሊሲ ለውጥ ሊጀመር ይገባል።ካሁን ቀደም እንዳልነው ኮማ ውስጥ ያለው አሮጌው ኢሕአዴግ ተቀብሮ አዲስ ኢሕአዴግ መወለድ አለበት። በየክልሉ የምናያቸው ችግሮች አባታቸው ኢሕአዴግ ነው ፤ ከየቦታው እየፈለቁ በሕዝብ መሓል ግጭት የሚፈጥሩት አባታቸው ኢሕአዴግ ነው ፣ በየሚዲያው የፖለቲካ ተላላፊ ወረርሽኝ የሚያሰራጩት አባታቸው ኢሕአዴግ ነው ፣ ሐገራችንን ለእርስ በርስ ጦርነት ለሃይማኖትና ለጎሳ ግጭት የሚዳርጉ ከባባድ አደጋዎችን እየፈጠሩ ያሉት በመንግስት ጉያ የተወሸቁት ሁከት ፈጣሪዎች፣ መዋቅሮችና ፖሊሲዎች አባታቸው ኢሕአዴግ ነው። ወዘተ ……. ያደፈው በሕዝብ ደምና ለቅሶ የጨቀየው ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ባለፉት አመታቶች በርካታ መንግስታዊ ወንጀሎችን ሰርቷል፤ አሁንም በተዝረከረከው መዋቅር የከፋ ሽብር በሕዝብ ላይ እያካሔደ ነው።ኢሕአዴግም ተዋኻደም አልተዋኻደም ፤ ኢሕአዴግ ኢሕአዴግ ነው። የስም ውሕደት ብቻውን ዋጋም የለውም ፤ በነብስም በስጋም ካልተቀየረ ለውጥም አያመጣም። ኦሕዴድም ብአዴንም ስማቸውን ቀይረዋል ግብራቸውን ግን አልቀየሩም።ሕወሓት ስሟንም ግብሯንም አልቀየረችም።ጥቂት አመራሮች ካልሆኑ በስተቀር ኢሕአዴግ እንደ ድርጅት ካለፉት ስሕተቶቹ ተምሮ አዲስ ነገር ለመፍጠር እየሰራ አይደለም።ባለህበት እርገጥ ሆኗል። ኢሕአዴግ በተከፋፈሉ ኃይሎች ተከቧል።ለስልጣን ከቋመጡ ኋይሎች ጀምሮ እስከ ለውጥ ፈላጊ ኃይሎች ድረስ እየተራወጡ ድርጅቱን ኮማ ውስጥ አስገብተውታል። አጋር ድርጅቶችም ቢሆኑ ወደ አሸናፊው ኃይል ለመቀላቀል እንደፔንዱለም እየተወዛወዙ ነው።እነዚህን ኃይሎች ለመለየት ከፍተኛ ፍጭት ቢኖርም የደፈረሰው እንዲጠራ ያበጠው መፈንዳት አለበት ። ኢሕአዴግን ለማመን ቢከብድም የመንግስት
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ለአሸንዳ/ሻደይ/አሸንድዬ/ሶለል በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለአሸንዳ/ሻደይ/አሸንድዬ/ሶለል በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እንኳን ለአሸንዳ/ሻደይ/አሸንድዬ/ሶለል በዓል በሰላም አደረሳችሁ! በሀገራችን ሴቶችን ወደ አደባባይ እንዲወጡ አስተዋጽዖ ሲያደርጉ ከኖሩት በዓሎቻችን መካከል አንዱ አሸንዳ/ ሻደይ/አሸንድዬ/ሶለል በዓል ነው። በዚህ ምድር አረንጓዴ በለበሰችበት በክረምቱ ወቅት በነሐሴ ወር አጋማሽ በትግራይና በአማራ ክልሎች በሚከበረው በዚህ በዓል ወጣት ሴቶች ልዩ የሆነ የሀገር ልብሳቸውን ለብሰውና ከወገባቸው ላይ እርጥብ ሰሌን በአንቀልባ መልክ አሥረው እያዜሙ ይወጣሉ። አደባባዮቻችን በአብዛኛው በወንዶች ብቻ ተይዘው በነበረበት በዚያ ዘመን እንደ አሸንዳ/ሻደይ/አሸንድዬ/ሶለል ያሉ በዓላት መኖራቸው በበረሐ እንደተገኙ ቀዝቃዛ ምንጮች የሚቆጠሩ ናቸው። ሴቶች በግጥሞቻቸው፣ በዜማዎቻቸውና በጭፈራዎቻቸው ሐሳባቸውን፣ ባህላቸውንና ምኞታቸውን እንዲገልጡ በማድረግም የማይተካ ሚና ነበራቸው። ለዚህም ነው እስከዛሬም ድረስ ወጣት ሴቶች ዓመቱን በሙሉ በጉጉት የሚጠብቁት በዓል የሆነው። የነሐሴ ወር፣ አንድ በዓል ለወንዶች አንድ በዓል ለሴቶች በመስጠት ፍትሐዊነቱን ያሳየ ወር ነው። ወጣት ወንዶች ችቦ ለኩሰው፣ ዳስ ሠርተው፣ ጅራፍ እያስጮኹ የቡሄን በዓል ያከብሩታል። ጭፈራው፣ ሆታው የወጣት ወንዶችን ሐሳብ የምንሰማበት፣ የደረሱበትን ደረጃ የምንለካበት፣ የነገውንም ምኞታቸውን የምናውቅበት ነው። እንዲሁም አሸንዳ/ ሻደይ/ አሸንድዬ/ ሶለል ደግሞ የወጣት ሴቶችን ድምጽና ሀሳቦቻቸዉን የምንሰማበት ወቅት ነው። የአሸንዳ/ሻደይ/አሸንድዬ/ሶለል በዓል እንደ ሕዝብ የነበረንን አብሮነትና የባህል ውርርስ የሚያሳይ ክዋኔ ነው። በዓሉ በተለያየ ስያሜ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ቢከበርም መሠረታዊ የሆነው መገለጫው ማኅበራዊና ባህላዊ ትሥሥርን የሚያሳይ ነው። የአሸንዳ/ሻደይ/አሸንድዬ/ሶለል በዓል ሃይማኖታዊ መነሻ የዕርገት በዓል በመሆኑ የሰዎችን ሥነ ልቡና ከፍ በማድረግ ታላቅ ዋጋ አለው። ከቀደመው ዘመን በላይ በዓሉ
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

በአፈር መደርመስ አደጋ 4 ሰዎች ሞቱ

(ኤፍ ቢ ሲ) በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የአፈር መደርመስ አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የመረጃ ኢንተለጀንስ ቡድን መሪ ሳጅን ጌታሁን ተስፋዬ እንደተናገሩት፥ አደጋው የተከሰተው በወረዳው ጋንታ ካንቻሜ ቀበሌ ልዩ ስሙ “መርከብ ጣቢያ” በሚባል ስፍራ ነው። አደጋው በአንድ ብሎኬት ማምረቻ ድርጅት ውስጥ መድረሱንም ተናግረዋል። የአደጋው መንስኤ የብሎኬት ማምረቻ ሰራተኞች አፈር በመቆፈር ላይ እያሉ በዙሪያው ከፍተኛ መጠን ያለው አፈር መደርመሱ መሆኑንም አስታውቀዋል ፡፡ ሳጅን ጌታሁን እንዳሉት በአደጋው በአፈር ቁፋሮ ላይ የነበሩ አራት ሰዎች ወድያውኑ ሕይወታቸው አልፏል። ከሟቾች መካከል ሁለቱ ወንድማማቾች መሆናቸውም ነው የተገለጸው። በቁፋሮ የወጣው የሟቾች አስክሬን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ምርመራ ተደርጎለት ለቤተሰቦቻቸው መሰጠቱንም የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ምሁራን የትምህርታቸውን ልክ፣ በየክልሎቻቸው ሲወስኑት የመታየቱ ነገር – ሸገር

Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Video

ኢሕአዴግ ከየት ወዴት? (ሙሉቀን ተስፋው)

ኢሕአዴግ ከየት ወዴት? (ሙሉቀን ተስፋው) ባለፉት ዓመታት በተደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል ለውጥ መፍጠር ቢቻልም ሥልጣኑን የተረከባው አካል ግልፅ የሆነ ፍኖተ ካርታ ባለማዘጋጀቱ የጠገበው ሒዶ የራበውና ሁሉም የእኛ ነው በሚሉ አካላት እጅ ወደቀ፡፡ እንደ ደቡብ አፍሪካው የANC በተራዘመ ሰላማዊ ትግል የመጣው የኢትዮጵያ ለውጥ በአግባቡ ኃላፊነት ከሚሰማቸው አካላት እጅ አለመውደቁ ለአገራችንና ለሕዝባችን ከመና ይልቅ ርግመትን አስከትሎ መምጣቱ ግልጽ እየሆነ ነው፡፡ የዶር ዐቢይ መንግሥት አንድም ሆን ብሎ፣ አሊም ካለማወቅና ከልምድ ማነስ በዘፈቀ እየሔደባቸው ያሉ መንገዶች አይደለም ለኢትዮጵያ ለኦሮሞ ሕዝብም የማይጠቅሙ ናቸው፡፡ በመጀመሪያ በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ አቢዮት (Revolution)፣ ተሀድሶ (Renaissance) ወይስ ጥገናዊ ለውጥ (Reform) ነው? በሚለው ላይ ስምምነት የለም፡፡ ጠሚው በተለያዩ ጊዜያት የሚያደርጓቸው ርእስ በእርሳቸው የሚጣረሱ ንግግሮችን ተስፋ የሚያደርገው ጎጋው ሕዝብ ቀናት አልፈው ወራት እየተተኩ በመጡ ቁጥር ምንም ጠብ የሚል ነገር አለመኖሩ ሕዝቡ የሰነቀው ተስፋ በአንዴ በንኖ የጠፋ ይመስላል፡፡ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ደጋፊ የነበሩ ተቃዋሚ ሲሆኑ፤ የድጋፍ ሰልፎች ወደተቃውሞ ሲቀየሩ፤ ሌላው ቀርቶ ውጭ የሚኖሩ ሀበሾች ሰልፍ እንዳይወጡ የሚያደርግ የአንድ ዓመት የዕፎታ ዘመን እንኳ ማምጣት አልተቻለም፡፡ የኢሕዴግ ጉዳይ! ከ2008 ዓም በኋላ ኢሕአዴግ እንደፓርቲ ነበር ማለት የማይቻል ቢሆንም በቅርቡ በሚደረገው የፓርቲው ስብሰባ ይፋዊ ፍች እንደሚደረግ ከወዲሁ መገመት ይቻላል፡፡ ኢሕአዴግ የፈረሰው በፓርቲው ውስጥ የነበረው በዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መረጃዎችን አፍኖ መያዝ ካቆመ በኋላ ነው ማለት ይቻላል፡፡ አሁን ላይ ያሉት ከአራቱም እህት ፓርቲዎች ፈጽመው አይናበቡም፤ የሚያወጧቸው መግለጫዎች እንኳንስ በአንድ
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ለሕዝብ ሲደርስ የነበረው መረጃ ፍጥነት የጎደለው እና ለውዥንብር የዳረገ ነበር ተባለ

ለሕዝብ ሲደርስ የነበረው መረጃ ፍጥነት የጎደለው እና ለውዥንብር የዳረገ ነበር ሲሉ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና የሥነ-ተግባቦት ትምህርት ክፍል ምሁር ገለጹ፡፡ (አብመድ) ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በባሕር ዳር በከፍተኛ መሪዎች ላይ የተፈፀመውን ጥቃት አስመልክቶ ለሕዝብ ሲደርስ የነበረው መረጃ ፍጥነት የጎደለው እና ለውዥንብር የዳረገ እንደነበር የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና የሥነ-ተግባቦት ትምህርት ክፍል ምሁሩ ዶክተር አደም ጫኔ ተናገሩ፡፡ በአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች ላይ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በባሕር ዳር በደረሰው ጥቃት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ለሕዝብ ሲደርሱ የነበሩ መረጃዎች ክልሉ በቀውስ ጊዜ ዕቅድ እየተመራ እንዳልነበረ ያሳዩ መሆኑንም ዶክተር አደም ገልጸዋል፡፡ ‹‹የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የመረጃ አሰጣጥ ፍጥነት የጎደላቸው እና ጉዳዩ በአሉባልታ መልኩ ከተሠራጨ በኋላ የደረሱ ናቸው፡፡ ይህም ሕዝቡ በተዛባ እና በይሆናል መረጃዎች መደናገር ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል›› ብለዋል፡፡ በሀገር እና በክልል ደረጃ ያሉ ትልልቅ ተቋማት የቀውስ ጊዜ ተግባቦት ዕቅድ አቅደው ‹‹ማን፣ መቼ፣ የትኛውን መረጃ በተደራጀ አግባብ መስጠት እንዳለበት ከቀውሱ በፊት መሥራት ነበረባቸው›› ያሉት ዶክተር አደም ‹‹በየትኛውም አካባቢ ቀውስ በሚከሰትበት ጊዜ የሥራ ኃላፊዎች በፍጥነት ለኅብረተሰቡ መረጃ ለማድረስ ዝግጁ ካልሆኑ በኅብረተሰቡ ውስጥ ውዥምብር ይፈጥራል›› ነው ያሉት፡፡ የተከሰተው ቀውስ ዜጎችን አስጨንቆ እንደነበርና ይህ ደግሞ ዜጎችን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ሰለሚወስዳቸው የሥራ ኃላፊዎች ከቻሉ ራሳቸው ካልሆነ ደግሞ በሚመለከተው አካል ወቅታዊ መረጃዎችን ወጥነት ባለው መልኩ ማድርስ እንደነበረባቸውም አመልክተዋል፡፡ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በደረሰው ጥቃት ‹‹እንዴት፣ ለምን፣ ማን
Posted in Ethiopian Drama, Ethiopian News

የሰሜን አሜሪካ የባህልና የስፖርት ፌስቲቫል በአትላንታ ተጀምሯል፡፡

የሰሜን አሜሪካ የባህልና የስፖርት ፌስቲቫል ኢትዮጵያን በማስተዋወቅ በኩል ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገለፀ፡፡ የሰሜን አሜሪካ የባህልና የስፖርት ፌስቲቫል በአትላንታ ተጀምሯል፡፡ Image may contain: 2 people, outdoor ለ36ተኛ ጊዜ በሚካሄደው በዚህ ፌስቲቫል ላይ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባላሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍፁም አረጋ ተገኝተው ፌስቲቫሉን በይፋ ከፍተዋል፡፡ አምባሳደር ፍጹም በመክፈቻ ንግግራቸው አትላንታ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት ብለዋል፡፡ ከ23 አመት በፊት በኢትዮጵውያን አትሌቶች የተገኘውን ድል በማስታወስ። የአሁኑ የስፖርት ፌስቲቫልም ወደፊት የሚዘከር ተጨማሪ አስደሳች ስፖርታዊ እና ሉሎች ትውስታዎች እንዲኖሩም ተመኝተዋል፡፡ የሰሜን አሜሪካ የባህልና የስፖርት ፌስቲቫል የእስካሁኑ ሂደት ኢትዮጵያን በማስተዋወቅ በኩል ከፍተኛ ሚና መጫወቱንም የፌደሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ ዐቢይ ኑርልኝ ተናግረዋል፡፡ የሰሜን አሜሪካው የባህልና የስፖርት ፌስተቫል በየዓመቱ 32 ቡድኖች ይሳተፉበታል፡፡ በ800 ተጫዋቾች 74 ግጥሚያዎችም ይደረግበታል፡፡Image may contain: 5 people, people smiling, people standing and outdoor ከስፖርቱ ባሻገርም አንዱን ቀን የኢትዮጵያ ቀን የሚል ስያሜ በመስጠት ስለ ሃገራቸው ባህልና ወግ ውይይት ያደርጉበታል፡፡ ለፌስቲቫሉ ከ 500 እስከ 1 ሚሊዮን ዶላር ወጭ የሚደረግ ሲሆን ከውድድሩ የሚተርፈው ገንዘብ ወደ ሃገር ቤት በመለክ ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ እንደሚደረግበት ተገልጿል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ብዙ ጊዜ ለውጥን እንጂ መለወጥን አንፈልግም።- ዶ/ር ገበያው ጥሩነህ

“ለውጥና መለወጥ ሁለት የተለያዩ ቃላቶች ናቸው፣ ብዙ ጊዜ ግን ለውጥን እንጂ መለወጥን አንፈልግም። ሳንለወጥ ደግሞ ለውጥ አይመጣም።” ዶ/ር ገበያው ጥሩነህ  
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Video

ዘመን ድራማ ክፍል 174

Posted in Ethiopian Drama, Video

ምዕራብ ወለጋ አሥር ሰዎች የጭነት መኪና ላይ አሸዋ ሲጭኑ ተገደሉ

ምዕራብ ወለጋ ላሎ አሳቢ ወረዳ ውስጥ ባለፈው ቅዳሜ “አሥር ሰዎች የጭነት መኪና ላይ አሸዋ ሲጭኑ ተገደሉ ሲል አንድ ከቅርብ ርቀት አየሁ” ያለ ግለሰብ ለቪኦኤ ቃሉን ሰጥቷል። የዞኑ የፀጥታ ፅህፈት ቤት ስለጉዳዩ እያጣራ መሆኑን ጠቅሶ “በሥፍራው ሲታኮሱ የነበሩት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው” በማለት ሁለት ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል::ትጥቅ አልፈታም፤ እስከመጨረሻው እዋጋለሁ ያለ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጣቂ አንጃ በአካባቢው የሚንቀሳቀስ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን “ደበሌ የሚባል የዚሁ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አፈንጋጭ ታጣቂዎች የምዕራብ ኦሮምያ ዞን መሪ ነው” የተባለ ግለሰብ በበኩሉ “ሰዎቹን የገደሉት የመከላከያ አባላት ናቸው፤ የተያዘ የኦነግ ታጣቂ የለም” ብሏል።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Video

አንድም የመንግስት አካል መጥቶ የጠየቀን የለም: ክረምት እየመጣ ነው ምንድን ነው የሚውጠን ? – ተፈናቃዮች

-ተቸግረናል በስጋት ውስጥ ነው ያለነው: ልጅ ይዤ ነው ከቤት የወጣሁት :አሁንም ነፍሰ ጡር ነኝ: የት እንደምወልድ እንኳ አላውቅም: አንድም የመንግስት አካል መጥቶ የጠየቀን የለም: ዝናቡ እየመጣ ነው ምንድን ነው የሚውጠን ? -መስራት እየቻልን መንግስት አፈናቅሎ ተረጂዎች ያደረገን ለምንድን ነው? “…መንግስት አልጎበኘንም ረስቶናል: መጪው ክረምት ነው :ጨለማ ነው እንዴት ነው የምንሆነው ? አቤት በሉልን ! ” የለገጣፎ ለገዳዲ ተፈናቃዮች ሮሮ    
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Video

አንጋፋው ድምጻዊ ሙሉቀን መለሰ አልሞተም

 
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Video

ማራኪዬ ከመድረክ ላይ ፡ በቴዲ አፍሮ

Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Ethiopian News, Music

በአገሪቱ ከሚታየው አለመረጋጋት አንፃር ቦርዱ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳን የመቀየር ስልጣን የለውም ተባለ።

የሥራ ጫናም ሆነ በአገሪቱ ከሚታየው አለመረጋጋት አንፃር ቦርዱ የምርጫው የጊዜ ወደፊት መገፋት እንለበት ቢያምን ይህን የማድረግ ሥልጣን አለው ወይ በሚል የተጠየቁት የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሥልጣን “የለውም” ብለዋል አያይዘውም ሊደረግ የሚችለውን አብራርተዋል።”ምርጫ ለማድረግ ያህል አናደርግም።ምርጫ በዜጎች ደህንነትና ሕይወት ላይ የተባባሰ ነገር ለማምጣት ብለን አናደርግም። ምርጫ የተሻለን ነገር ለማምጣት ነው መደረግ ያለበት። እስካሁን ከተደረጉ ምርጫዎች በአብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል ተአማኒነት ያገኘ እንዲሆን አድርገን ለሱ የሚያስፈልጉንን ነገሮች በኛም ፣ በተሳታፊዎችና በሰላሙ ሁኔታ መሬት ላይም መኖራቸውን አረጋግጠን ነው የምናደርገው። “ ብለዋል …. (ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)    
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Video

የፖለቲካ ፓርቲ ነን ብለው ወዲያና ወዲ የሚቀላምዱ አሉ – ታዋቂው እስፖርተኛ ግርማ ቸሩ

የፖለቲካ ፓርቲ ነን ብለው ወዲያና ወዲ የሚቀላምዱ አሉ – ታዋቂው እስፖርተኛ ግርማ ቸሩ Source : Ethiopis
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Video

በሐረማያ ዩንቨርስቲ ተቃውሞ ሁለት ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰማ።

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከትናንት፣ ሰኞ መጋቢት 23/2011 ዓ.ም. ጀምሮ የተቃውሞ ሰልፍ እያደረጉ መሆናቸው ታውቋል።በተቃውሞው ሁለት ተማሪዎች መጎዳታቸውን የገለፁት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዩኒቨርሲቲው ከአመሻሽ ጀምሮ መረጋጋቱን ገልፀዋል።በተቃውሞ ሰልፉ ኦሮምኛ ፌደራል ቋንቋ እንዲሆን እና ሌሎችም ጥያቄዎች መነሳታቸውን ቪኦኤ ያነጋገራቸው አመልክተዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Video

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጎሰኝነትና ጎጠኝነት አሁን ላይ ለወንጀል መባባስ መነሻ እየሆነ ነው አለ፡፡

Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Video

ኢትዮጵያዊነት ሱስ መሆኑን ምንጊዜም ያለ ሀፍረት እናገራለሁ – አቶ ለማ መገርሳ

ኢትዮጵያዊነት ሱስ መሆኑን ምንጊዜም ያለ ሀፍረት እናገራለሁ – የኢትዮጵያ ህዝብ ነገም ቢሆን ሊጠራጠረን አይገባም – አቶ ለማ መገርሳ
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Ethiopian News, Video

በወሬና በስሜት መጋለብ በመንጋ መነዳትን አቁመን አዲስ ስርዓት ስለመገንባት እናስብ – ዶር ብርሃኑ ነጋ

Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Video

ከፌደራሉ መንግሥትና ከተለያዩ ለጋሽ ድርጅቶች የተላኩ ተጨማሪ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታዎች ወደ ጌድኦ እየደረሱ ነው፡፡

በጌዲዮ ዞን ለረሀብ ለተጋለጡ ተፈናቃዮች ምግብ እየታደለ መሆኑን የአካባቢው ባለሥልጣናት ገለጹ፡፡ ባለሥልጣናቱ እንዳሉት በአሁኑወቅት ከፌደራሉ መንግሥትና ከተለያዩ ለጋሽ ድርጅቶች የተላኩ ተጨማሪ የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታዎች ወደ አካባቢው እየደረሱ ነው፡፡ በመጠለያ ጣቢያዎቹ የሚታየውን የውሃና የጤና አገልግሎት ችግሮችን ለመቅረፍ የፌደራሉ የሚንስቴር መሥሪያቤቶች ባደረጉት ድጋፍ ከነገ ጀምሮ አቅርቦቱን ለመጀመር የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጧል፡፡    
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Video

ርዳታ በጊዜው እየደረሰን አይደለም – የአማራ ክልል ተፈናቃዮች

በአማራ ክልል የሚገኙ አንዳንድ ተፈናቃዮች መንግሥት እያደረገላቸው ያለው ድጋፍ እየተሸሻለ እንደሆነ ሲገልፁ፣ ሌሎቹ ደግሞ ድጋፉ ወቅቱን ጠብቆ አይደርሰንም እያሉ ነው።የአማራ ክልል መንግሥት በበኩሉ ለተፈናቃይ ወገኖች ከተለያዩ አካላት የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ መቀጠሉን ይናገራል። በአማራ ክልል በ13 መጠለያ ጣቢያዎች ከ90 ሺህ በላይ ተፈናቃይ ወገኖች እንደሚገኙ ነው የተገለጸው። https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/C25A1BC6_2_dwdownload.mp3
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

የአሜሪካ ኤምባሲ ለዜጎቹ ያወጣው የደኅንነት ሥጋት ማስታወቂያ በመጥፎ አትተርጉሙብኝ አለ

ሰሞኑን የአሜሪካ ኤምባሲ ለዜጎቹ ያወጣው የደኅንነት ሥጋት ማስታወቂያ፣ በተለያዩ መንገዶች መተርጎም እንደማይገባው ቃል አቀባዩ ኒኮላስ ባርኔት አስገንዝበዋል። The U.S. Embassy is aware of the crash this morning of Ethiopian Airlines flight ET302. We extend our sincerest sympathies to all who are impacted by this tragic event. https://t.co/jHJ8HpGRiR — U.S. Embassy Addis (@USEmbassyAddis) March 10, 2019 ማሳሰቢያ በትላንትናው ዕለት እንደገና ተሻሽሎ የአሜሪካ ኤምባሲ ሠራተኞች ወደ አውሮፕላን ማረፊያው መጓዝ እንደሚችሉ ተገልፆ እንደነበርም አስታውቀዋል። ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ። የአሜሪካ ኤምባሲ ቃል አቀባይ ኒኮላስ ባርኔት
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ለዘንድሮ ይደረጋል የተባለው የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ምርጫ ጉዳይ የተሰማ ነገር የለም

Image result for ምርጫ ቦርድአንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ምርጫው ከሀገራዊው ምርጫ ጋር ቢካሄድ እንደሚሻል ተናግረዋል። ሌላው ደግሞ በዚህ ዓመት መካሄዱን መርጠዋል። ሦስተኛው አስተያየት ሰጭ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች መፍትሄ ሳይገኝ የነዚህ ሁለት ከተሞች ምርጫ ብቻ ሳይሆን ሀገራዊውንም ምርጫ ማካሄድ አይገባም ብለዋል። የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ዓመት የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋን ምርጫ ለዘንድሮ አስተላልፎ ነበር። ይሁን እና ዓመቱ ቢጋመስም በ2011 ይካሄዳል ስለተባለው የሁለቱ ከተሞች ምርጫ ከምርጫ ቦርድ በኩል የተሰማ ነገር የለም ይላል የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር። ዮሐንስ በጉዳዩ ላይ ካነጋገራቸው የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች አንዱ ምርጫው ከሀገራዊው ምርጫ ጋር ቢካሄድ እንደሚሻል ተናግረዋል። ሌላው ደግሞ በዚህ ዓመት መካሄዱን መርጠዋል። ሦስተኛው አስተያየት ሰጭ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች መፍትሄ ሳይገኝ የነዚህ ሁለት ከተሞች ምርጫ ብቻ ሳይሆን ሀገራዊውንም ምርጫ ማካሄድ አይገባም ብለዋል። ስለ ጉዳዩ የምርጫ ቦርድን አስተያየት ለማግኘት DW ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/B66D7367_2_dwdownload.mp3
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ቀኑ ድሎችን የምናወሳበት ብቻ ሳይሆን ፈተናዎችን ተገንዝበን ችግሮችን ለመፍታት የምንዘጋጅበት ነው – ጠ/ሚ ዶክተር አብይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን ስናከብር ድሎችን የምናወሳበት ብቻ ሳይሆን ፈተናዎችን ተገንዝበን ችግሮችን ለመፍታት የምንዘጋጅበት መሆኑን ገለጹ፡፡ Image may contain: 13 people, people smiling, people sitting   ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዛሬ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በተከበረው ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን ላይ ነው። ያለቤተሰብ ሀገር መገንባት አይቻልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሴቶች በቤተሰብ ሀላፊነት ውስጥ ያላቸው ሚና የማይተካ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ጠንካራ ሀገርን ለመገንባት ጠንካራ ሴቶች እንደሚያስፈልጉ በመግለጽ እናቶች ደምን፣ ጉልበትን፣ እውቀትን ሀብትን በማጋራት በአርዓያነት የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል፡፡ ከመጉረስ ማጉረስ፣ ከመግፋት ማቀፍ፣ ከመቀማት ማካፈል ውስጣዊ ደስታ የሚያጎናጽፍና ህሊናዊ እርካታ እንደሚሰጥም ከእናቶች መረዳት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ ሴቶች ባሎቻቸውን ልጆቻቸውን አጥተው ኢትዮጵያን ለዚህ ትውልድ ማቆየታቸውን በመጥቀስም፥ አሁን ላይ ሰውሰራሽ ግጭቶችን በመከላከልና የሀገሪቱን ሰላም በማስጠበቅ ሴቶች ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ጀግንነት በችግር ጊዜ እውነታን ይዞ መቆም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ አሁን ላይ በሀገሪቱ እየታዩ ያሉ ችግሮችን በመከላከል በኩል ሰፊ ስራዎች እንደሚጠበቁም ነው የተናገሩት፡፡ በዚህም ሴቶች መተሳሰብን፣ አንድነትን እና በጋራ መኖርን ታሳቢ ያደረጉ ስራወች ላይ በትኩረት እንዲሰሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የሰላም ወዳጆችና የአንድነት ፈላጊዎች ዝምታ ከዚህ በተቃራኒ የቆሙ የጥቂቶች ድምጽ ጎልቶ እንዲሰማ ማድረጉንም አንስተዋል፡፡ ትውልዱ ድልን በመጋራት ሽንፈትን ከመሸሽ አባዜ መውጣት እንዳለበት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ለዚህም የሴቶች የድርሻቸውን ሊወጡ እንደደሚገባ አሳስበዋል ሲል የዘገበው ኤፍ ቢሲ ነው።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ቀደማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ቁስቋም አካባቢ ለሚገነባ የህፃናት ማሳደጊያ ማዕከል የመሰረተ ድንጋይ አስቀመጡ

ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው በቁስቋም አካባቢ ለሚገነባ የህፃናት ማሳደጊያ ማዕከል የመሰረተ ድንጋይ አስቀመጡ፡፡ Image may contain: 4 people, people smiling በዚህ ወቀት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ ታዳጊዎች ላይ ተገቢው ስራ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ይህ የህፃናት ማሳደጊያ በእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰበትን የወይዘሮ ዘውድነሽ መሻሻ የህፃናት ማቆያ ማዕከልን የሚተካ ነው ተብሏል፡፡ እንደ ኤፍ ቢሲ ዘገባ ማዕከሉን የገና ዋዜማ ጠቅላይ ሚኒስት ዶክተር አብይ አህመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታየቸው መጎብኘታቸው የሚታወስ ነው፡፡ በዘላቂነት ታዳጊዎች የሚያድጉበት ማዕከሉ ቤተ መፅሀፍት፣ ትምህርት ቤት፣ የመመገቢያ አዳራሽ፣ የስልጠና ማዕከላት እና የመጫዎቻ ስፍራ ያካተተ ነው ተብሏል፡፡ የህፃናት ማሳደጊያው በስድስት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለ ሲሆን የግንባታው ወጪ በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት እና በአፍሮ ፂዮን ኮንሽትራክሽን ይሸፈናል ተብሏል፡፡ ለዚህ የህፃናት ማዕከል ግንባታ እስከ 20 ሚሊየን ብር ወጪ እንደሚደረግበት ተነግሯል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

በጅቡቲ በኩል ወደ ሀገር ሊገባ የነበረ ጥራቱን ያልጠበቀ ማዳበሪያ ላይ ዕርምጃ ተወሰደ

Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Video

ኤጄቶ የተባለው ቡድን የደኢህዴን ጉባዔ ላይ ጥሶ በመግባት በተሰብሳቢዎች ላይ ደብደባ ፈፀመ

ገከደቂቃዎችባለው ቡድን የደኢህዴን ጉባዔ ላይ ጥሶ በመግባት በተሰብሳቢዎች ላይ ደብደባ ፈፀመ በወሮ ሙፍሪያት የሚመራው የደኢህዴን አመራሮች በሲዳማ ኤጄቶች ከሀዋሳ ለቀው እንዲወጡ እየተደረጉ ይገኛል። ምክንያቱም በትላንትናው እለት በሀዋሳ ከተማ ባዘጋጁት ስብሰባ ላይ የሲዳማን የክልል ጥያቄ በማንቋሸሻቸው ነው ተብሏል!! Image may contain: 5 people, people standing, crowd and outdoor ዛሬ በሀዋሳ በመንግስት ሀላፊዎች ላይ የተፈፀመው ድብደባ! ጋዜጠኛ ኤሊያስ መሰረት እንደፃፈው ከደቂቃዎች በፊት የደቡብ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ከሆኑት ከዶ/ር ጌታሁን ጋረደው ጋር በስልክ አውርቼ ነበር። የነገሩኝ የሚከተለው ነው: የወላይታ ዞን ቱሪዝም እና ባህል ቢሮ ሀላፊ አቶ ፀጋ ስምዖን “በመጀመርያ በሶሻል ሚድያ እኔ በወጣቶች እንደታገትኩ የተገለፀው ሀሰት ነው። ጠዋት እኔ ስመራው የነበረው ስብሰባ ሌላ አዳራሽ ውስጥ ነበር። ወጣቶች መጥተው ስብሰባው ይቁም ሲሉ confront ሳናረጋቸው አመራሮችን ወዲያው በትነናል። የወላይታ ዞን ቱሪዝም እና ባህል ቢሮ ሀላፊ አቶ ፀጋ ስምዖን ላይ ግን ጥቃት ተፈፅሟል። ይህ ስብሰባ ይካሄድበት የነበረው አዳራሽ ውስጥ ከመጡት ወጣቶች ጋር ግጭት ነበር። ዝርዝሩን አላውቅም። አሁን ሰላም ነው። አቶ ፀጋ ለህክምና ሶዶ ደርሷል። ከትንሽ ደቂቃ በፊትም አናግሬዋለሁ።” ማነው ድብደባውን የፈፀመው ስላቸው “እከሌ ኤጄቶ ነው እከሌ አይደለም ለማለት አልችልም። ግን ሶሻል ሚድያ ላይ ኤጄቶ ስብሰባው እንዲበተን ይፈልጋል የሚል መልእክት ጠዋት ስብሰባ ከመግባቴ በፊት አንብቤ ነበር።”  
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማን አስጠነቀቁ

አፈ ጉባኤ ታገሰ ለምክትል ከንቲባ ታከለ የፃፉት ማስጠንቀቂያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ ከትናንት በስቲያ በፃፉት ደብዳቤ ለምክር ቤቱ እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ግንባታ ተብሎ የተተወውን ባሻ ወልዴ ሰፈር ያለውን ቦታ ለመናፈሻ አገልግሎት መዋሉን ተችተው በቦታው ያለው እንቅስቃሴ እንዲቆም አስጠንቅቀዋል። Image may contain: text Image may contain: text
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ቀውስ ለመፍታት ብሔራዊ መግባባት እና እርቅ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ቀውስ ለመፍታት ብሔራዊ መግባባት እና እርቅ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ። ይህ በተገለጸበት የኢትዮጵያውያን ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ መግባባት እና እርቀ ሰላም ዓለም አቀፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ዛሬ ባዘጋጀው የምክክር መድረክ በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ተገኝተዋል።ኮሚቴው በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ በሚኖሩ ፖለቲከኞች የተቋቋመ መሆኑም ተነግሯል። ዘገባው የጀርመን ድምጽ ነው ይህን ተጭነው ያዳምጡት  https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/BA547418_2_dwdownload.mp3 Image result for የኢትዮጵያውያን ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ መግባባት እና እርቀ ሰላም ዓለም አቀፍ አስተባባሪ ኮሚቴ    
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ከለገጣፎ የተፈናቀሉ 500 ያህል አባወራዎች የሚገኙበትን ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ አመለከቱ።

ከሳምንታት በፊት ከለገጣፎ ከተማ ሕገወጥ ነው በሚል ቤታቸው የፈረሰባቸው 500 ያህል አባወራዎች የሚገኙበትን ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ አመለከቱ። እነዚህን ወገኖች ወደ ተጠለሉበት በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 10 በሚገኘው አያት መካነ ሕይወት መድኃኒዓለም ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ DW አነጋግሯቸዋል። ለቀናት ፀሐይ እና ብርድ ሲፈራረቅብን አስቸጋሪ ሕይወት ስንመራ ነበር ያሉት እነዚህ ቤተሰቦች የምግብ፣ የጤና፣ የህክምና እና የመጠለያ ችግር እየተፈራረቀባቸው የሰቀቀን ኑሮ እየገፉ መሆኑን ተናግረዋል። በቤተ ክርስቲያኑ ሕጻናት፣ አራስ እናቶች፣ ነፍሰጡሮች እና ሌሎችም ፈታኝ የጭንቅ ሕይወት እየገፉ መሆናቸውንና አሁን ዝናብ መዝነብ መጀመሩ ሌላ ጭንቀት እንደፈጠረባቸውም ነግረውናል፡፡ ለችግራችን መፍትሄ ፍለጋ ያልሄድንበት የለም ያሉት DW ያነጋገራቸው ዜጎች ተስፋቸው መሟጠጡንና ሀገር አልባነት እንደሚሰማቸው ተናግረዋል፡፡ በየእለቱ ደከመኝ ሳይልና ሳይሰለች ድጋፍ እያደረገልን ያለው የአዲስ አበባ ህዝብ ምስጋና ይድረሰው ያሉት ቤት አልባዎቹ ሰዎች በፈረሰባቸው ቤት እስከ 10 አመት የሚሆናቸውን ልጆች ወልደው እንዳሳደጉበት እና በነበራቸው ጥሩ የልማት ሥራ ተሳትፎ ከለገጣፎ ከተማ አስተዳደር የምስጋና የምስክር ወረቀት ያገኙበትንም ሰነድ አሳይተውናል፡፡ መንግሥት ችግራችንን ተመልክቶ መፍትሄ እንዲያበጅልን ሲሉም ጠያቄያቸውን አቅርበዋል፡፡ በቤተ ክርስቲያኑ በርከት ያሉ የፕላስቲክ ቤቶች የተወጠሩ ሲሆን በ 300 ሽህ ብር ተገዝቶ የነበረ የቤተክርስቲያኗ ትልቅ ድንኳን እና አንድ ሌላ አነስ ያለ የቀይ መስቀል ድንኳን ተዘርግቶ ሕጻናት እና እናቶች አርፈውበታል፡፡ https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/6098FDB5_2_dwdownload.mp3
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ጣና ሐይቅንና ሌሎችንም የውሀ አካላት ከጥፋት ይታደጋል የተባለ ኤጀንሲ ሊቋቋም ነው

ጣና ሐይቅንና ሌሎችንም የውሀ አካላት ከጥፋት ይታደጋል የተባለ ኤጀንሲ እንደሚቋቋም የአማራ ክልል አስታወቀ። የክልሉ የአካባቢ የደን እና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለሥልጣን የኤጀንሲው ዋና ተግባር የውሐ አካላትን ከጥፋት ማዳን ብቻ ይሆናል ብሏል። ኤጀንሲው የሚቋቋመው የአማራ ክልል ምክር ቤት ባለፈው ጥቅምት 2011 ዓ.ም. ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት ነው። የኤጀንሲው ማቋቋሚያ አዋጁ በክልሉ “ዝክረ ህግ” ጋዜጣ ፀድቆ ሰሞኑን መውጣቱን እና መስሪያ ቤቱን ለማቋቋም የሚያስችል ኮሚቴ መዋቀሩንም የአማራ ክልል አካባቢ፣ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጋሻው እሸቴ ተናግረዋል። ጣና ሐይቅ ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ እንቦጭ በተባለ አረም በመወረሩ በሐይቁ ህልውና ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል፡፡ አረሙን ለመከላከል በአገር ውስጥ ከሚገኙ ባለሀብቶችና ሌሎች ተቋማት ወደ 50 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን አቶ ጋሻው መናገራቸውን DW ዘግቧል።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አለም አቀፍ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመራ በረራ ወደ ኖርዌይ ኦስሎ ማድረግ ጀምሯል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አለም አቀፍ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመራ በረራ ወደ ኖርዌይ ኦስሎ ማድረግ ጀምሯል። Image may contain: 5 people, people smiling, people standing, suit and outdoor የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያምን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በረራውን የማስጀመር ስነ ስርዓት ተካሂዷል። የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዚሁ ወቅት፥ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመራ በረራ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ በመታደማቸው ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በነገው እለት የሚከበረውን አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ከአዲስ አበባ- ስቶኮልም ወደ ኦስሎ የሚደረገው በረራ በሴት የአብራሪዎች ቡድን የሚመራ ነው። በረራው ታሪካዊ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን የአውሮፕላኑ አብራሪ፣ የበረራ አስተናጋጅ እና መላው ሰራተኞች በኢትዮጵያውያን ሴቶች ሙሉ በሙሉ የሚመራ ነው ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ ባለፈም ከአየር ትራፊክ ቁጥጥር፣ የጭነት ቁጥጥር፣ የበረራ መለኪያ፣ የበረራ ደህነነት ቁጥጥር እና አጠቃላይ የአውሮፕላኑ ጉዞ ከትኬት ቢሮ ጀምሮ እስከ አውሮፕላኑ መነሻ ድረስ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመራ መሆኑን አየር መንገዱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም በሁሉም የበረራ ዘርፍ ብቁ የሆኑ ሴቶች ተቋሙ ስላለው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ዋና ስራ አስፈፃሚው ሴቶች ለአየር መንገዱ ስኬት ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸውም ነው የተናገሩት፡፡ በአፍሪካ ሴቶች ዋነኛ የሀብት መሰረት ቢሆኑም የፆታ እኩልነት አሁንም ድረስ እንደሌለ የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚው ሴቶች የሚገባቸውን ቦታ እንዲያገኙ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ አየር መንገዱ ይህንን ፕሮግራም የጀመረውም
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

የትግራይ ህዝብ በወንድም የአማራ ህዝብ ላይ አፈሙዝ የሚያዞርበት አንዳች ምክንያት የለም – የትግራይ ክልል መንግስት

ትላንት፣ ዛሬም ሆነ ነገ የትግራይ ህዝብ ዋነኛ አጀንዳ ሰላም፣ ዴሞክራሲና ልማት መሆኑን የትግራይ ክልል መንግስት ገለፀ። የክልሉ መንግስት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የትግራይ ህዝብና መንግስት የጦርነት አስከፊነት ስለሚረዱ፣ ዋነኛ አጀንዳቸው የሆነው ሰላም ማስፈን፣ ዲሞክራሲ ማስፋትና መልካም አስተዳደር ማንገስ እንዲሁም ፈጣንና ሁሉም በየደረጃው ተጠቃሚ የሚሆንበት ልማት ለማረጋገጥ በመታተር ላይ መሆናቸውን አንስቷል። የትግራይ ህዝብና መንግስት በ17 ዓመታት የትጥቅ ትግል ወቅት፣ ወታደራዊ ፋሽስት ደርግን ለመደምሰስ በተደረገው መራራ ትግል፣ የአማራ ህዝብ፣ ከወንድሙ የትግራይ ህዝብ ጎን ተሰልፎ ተገቢው መስዋእትነት መክፈሉን አስታውሷል። በመሆኑም የትግራይ ህዝብና መንግስት የታገሉለትን ህዝባዊ መሰመር አንግበዉ ወደፊት ከመገስገስ ውጪ በወንድም የአማራ ህዝብ ላይ አፈሙዝ የሚያዞርበት አንዳች ምክንያት የለም ነው ያለው።   በመሆኑም የትግራይ ህዝብና መንግስት ባለፉት ዓመታት፣ በተለያዩ ችግሮች የባከኑባቸውን ጊዚያት ለማካካስ፣ ሁለመናቸው ያቀዱት የዴሞክራሲና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት በመሯሯጥ ላይ ናቸው ብሏል። የክልሉ ህዝብና መንግስት በተያያዙት የበጋ ወቅትም ቢሆን አፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባራት በማሳለጥ ለ2011/2012 የክረምት ስራ ቅድመ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን መግለጫው አንስቷል። ስለሆነም ትላንትም ሆነ ዛሬ የትግራይ ህዝብና መንግስት ዋነኛ ጠላት ድህነት ያለው መግለጫው፥ አሁንም ቢሆን ጦርነታቸዉ ከድህነት ጋር በመሆኑ ማንኛውም ሰላም ወዳድ ዜጋ ስጋት ሊገባዉ አይገባም ብሏል። በአጭሩ የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዋነኝነት የአማራና የትግራይ ህዝቦች ሰላም ተረጋግጦ የልማት ተቋዳሽ የሚሆኑት፣ በሀገሪቱ ሕገ-መንግስት ተከብሮ፣ የሕግ የበላይነት ተረጋግጦ፣ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ ተጠናክሮ ሲቀጥል መሆኑን አስታውቋል። (ኤፍ.ቢ.ሲ)
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

በአዲስ አበባና ኦሮሚያ መካከል ያለው የአስተዳደር የወሰን ጉዳይ እልባት ሳይሰጠው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በእጣ መተላለፋቸው ተገቢ አይደለም – – የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት

የኦሮሚያ ክልል መንግስት በግልፅ ወይም በይፋ አዲስ አበባን የኦሮሞ ለማድረግ እሰራለሁ አለ !! No photo description available.   “በአዲስ አበባና ኦሮሚያ መካከል ያለው የአስተዳደር የወሰን ጉዳይ እልባት ሳይሰጠው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በእጣ መተላለፋቸው ተገቢ አይደለም- የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባና በኦሮሚያ መካከል ያለው የአስተዳደር የወሰን ጉዳይ እልባት ሳይሰጠው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በእጣ ለባለ ዕድለኞች መተላለፋቸው ተገቢ አለመሆኑን የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልልዊ መንግስት ገለፀ። የክልሉ መንግስት ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባወጣው መግለጫ የኦሮሚያ ክልል ጥያቄ እያነሳባቸው ባሉና የክልሉን ወሰን አልፈው የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በእጣ ለተጠቃሚዎች የማስተላለፍ ሂደት እንዳይተገበርም አቋም መያዙን ነው የገለፀው። የኦሮሚያ ክልል መንግስት በሁሉም አቅጣጫ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ደረጃ በደረጃ እየሰራ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫው አንስቷል። በዚህም ትላልቅ ስኬቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ነው መግለጫው የጠቆመው። የአዲስ አበባ ጉዳይም ይሁን ከዚሁ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጉዳዮች በሙሉ በቅደም ተከተላቸው መልስ እንዲያገኙ በተሃድሶ ከስምምነት ላይ የተደረሰበት መሆኑን በማንሳትም ይህም እየተሰራበት መሆኑን ነው ገልጿል። በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ መካከል ያለው የአስተዳደር የወሰን ጉዳይ አልባት እስከሚያገኝ የኦሮሚያ ክልልን ጥያቄ እያነሳባቸው ያሉ የክልሉን ወሰን አልፈው የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች በእጣ ማስተላለፍ ትክክል እንዳልሆነ የክልሉ መንግስት ያምናልም ነው ያለው። በመሆኑም ይህ ውሳኔ ስራ ላይ እንዳይውል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጠንካራ አቋም መያዙን በመግለፅ፥ ይህ አቋም በቀዳሚነት የህዝቡን ተጠቃሚነት በማስጠበቅ የመነጨ እንጂ የሀገሪቱን ብሄር ብሄረሰቦች አብሮ የመኖር እሴት ከመጥላት
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

በሀገሪቱ እየታዬ ያለው የደኅንነት ዋስትና አሳሰቢ መሆኑ የተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ክልሎችን ገቢ እያሳጣ ነው

(አብመድ) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሎች የሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎች ክልሎችን የሚገልጹ መለያ ኮዶችን እየተጠቀሙ አይደለም፡፡ በተለይ በአማራ ክልል የኮድ 2 እና 3 ተሽከርካሪዎች ሰሌዳዎች በአብዛኛው ‹‹አአ›› እና ‹‹ኢት›› እየሆኑ ነው፡፡ ከክልሎች ይልቅ ‹‹አአ›› እና ‹‹ኢት›› የሚሉ መለያ ኮዶችን እየተጠቀሙ ነው፤ ለዚህ ባለቤቶቹ የሚያቀርቡት ምክንያት ደግሞ በሀገሪቱ እየታዬ ያለው የደኅንነት ዋስትና አሳሰቢ መሆኑን ነው፡፡ ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ አሽከርካሪዎችም የአንድን ክልል ነዋሪነት የሚገልጽ ሰሌዳ ቁጥር አድርጎ መንቀሳቀስ ለጥቃት እያጋለጠ በመሆኑ ያለስጋት ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ ለመንቀሳቀስ አዲስ አበባ ወይም ኢትዮጵያ የሚል መለያ ያለው ሰሌዳ እንደ አማራጭ እንደሚጠቀሙ ነው የነገሩን፡፡ በሀገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣው ብሔር ተኮር ጥቃት የአንድን ክልል የሰሌዳ ቁጥር ይዞ በመላ ሀገሪቱ መንቀሳሰቀስን አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡ የክልል ስም የሚገልጽ ሰሌዳ ያላቸው ተሸከርካሪዎች ከራሳቸው ክልል ወጥተው ወደ ሌሎች ክልል ሲንቀሳቀሱ ፍተሻው የክልሉን ወሰን እንደተሻገሩ ይጀምራል፡፡ ተሽከርካሪውም የሌላ ሀገር ሰሌዳ ያለው ተደርጎ እንደሚቆጠር አሽከርካሪዎች ነግረውናል፡፡ ይህ ደግሞ ዜጎች በመላ ሀገሪቱ በነጻነት ተዘዋውረው እንዳይሰሩ እና እርስ በርስ ያላቸው ግንኙነት እየተራራቀ እንዲሄድ የሚያደርግ መሆኑን ነው ያብራሩት፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ ያነጋገርናቸው የአማራ ክልል መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የተሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክተር ወይዘሮ አሚነት ጀማል የተሸከርካሪ ሰሌዳ ቁጥር አሰጣጥ እንዳጠቃላይ ሲታይ አንዱን ክልል ከአንዱ ክልል ጋር አብሮ እንዳይሰራ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለአብነትም የሕዝብ ማመላለሻ ተሸከርከሪዎች ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል ተሻግረው እንዳይሰሩ መደረጉ ሌሎች ተሸከርካሪዎች በነጻነት እንዳይንቀሳቀሱ ለመደረጉ ምክንያት
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 105 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 105 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ Image may contain: outdoorበህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 105 ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የቡራዩ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ። ከቡራዩ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፥ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ በትናንትናው እለት ሌሊት ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት። ከጋምቤላ ክልል ወደ አማራ ክልል በርካታ የጦር መሳሪያዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው ተሽከርካሪም የፀጥታ አካላት በጥምረት በሰሩት ስራ ትናንት ሌሊት ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነግሯል። በቡራዩ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የፀጥታ ማረጋገጥ የስራ ሂደት ባለቤት ኢንስፔክተር አንተነህ ጌታነህ እንዳስታወቁት፥ የጦር መሳሪያዎቹ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ የቡራዩ ከተማ ፖሊስ፣ ልዩ ሀይል እና የብሄራዊ ደህንነት አገልግሎት በጋራ በሰሩት ስራ ትናንት በግምት ከሌሊቱ 6 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት ገደማ መካከል ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት። እንደ ኤፍ ቢሲ ዘገባ በወቅቱ በቡራዩ ከተማ አሸዋ ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተደረገ ፍተሻ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲባል ከስፍራው ተሽከርካሪውን በመሸሽ ለማምለጥ በመሞከር ላይ እያሉ በተደረገ ክትትል በአምቦ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አስታውቀዋል። በዚሁ መሰረት ለውዝ ጭኖ በነበረ አይሱዙ ኤፍ.ኤስ.አር የጭነት ተሽከርካሪ ላይ 42 ታጣፊና 63 ባለሰደፍ በድምሩ 105 ክላሽንኮቮች፣ 95 የክላሽንኮቭ መጋዝኖች እና 5 ጥይት በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም ከአይሱዙ ኤፍ.ኤስ.አር የጭነት ተሽከርካሪው ፊት በመሄድ ሁኔታዎችን ሲያመቻች የነበረ አንድ ዶልፊን ሚኒባስ ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ስድስት ኪሎ አካባቢ ባለቤቱን በጥይት ገደለ

አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ስድስት ኪሎ አካባቢ ባለቤቱን በጥይት ገደለ አዲስ አበባ ስድስት ኪሎ አካባቢ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል የስራ ባልደረባውና ባለቤቱ የሆነችውን የፖሊስ አባል ዛሬ ረፋድ ላይ በጥይት መግደሉ ተሰማ። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ምክትል ሃላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ምትኩ ለኢዜአ እንደገለጹት ተጠርጣሪው የፖሊስ አባል የሆነችውን የትዳር አጋሩን ስድስት ኪሎ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ካምፕ መግደሉን አረጋግጠዋል። መንስኤው ገና በመጣራት ላይ ቢሆንም ግድያው የተፈፀመው በመካከላቸው በተፈጠረው ጊዜያዊ አለመግባባት መሆኑም ታውቋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

በኦሮሚያ በተለያዩ ከተሞች ኮንዶሚኒየም በእጣ መተላለፉን በመቃወም ሰልፎች ተደረጉ

የኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም በእጣ እንዲተላለፉ ማድረጉን በመቃወም በኦሮሚያ በተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ተደረጉ ትናንት እጣ የወጣባቸው  በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የተገነቡ ናቸው በሚል የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር  ዛሬ በኦሮሚያ በተለያዩ ቦታዎች ሰላማዊ ሰልፎች ተደርገዋል፡፡ ሰላማዊ ሰልፎቹ በጉደር፣ ሆለታ፣ ሮቤ፣ ሸሸመኔ፣ ጭሮና ሌሎች ከተሞች ተደርገዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትናንትና ዕለት ለልማት ተነሺ አርሶ አደሮች የኮንዶሚኒየም ቤቶች ያለ እጣ እንዲሰጣቸው መወሰኑን ገልጾ ነበር፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥትን አደጋ ላይ የጣለው ምንድን ነው?

BBC Amharic ጎንደር በ16ኛው ክፍለ ዘመን በአፄ ፋሲለደስ እንደተቆረቆረች ይነገራል። ይሁን እንጂ ከአፄ ፋሲለደስ ንግሥና 300 ዓመታት ቀድማ በምንጮችና በተራሮች የተከበበች መንደር ነበረች ሲሉ የሚሞግቱም የታሪክ አዋቂዎች አሉ። ጎንደር ለ200 ዓመታት የኢትዮጵያ መናገሻ ሆና አገልግላለች። ባሏት ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ቅርሶች፣ ታሪካዊ ቦታዎች እንዲሁም ኃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቶች ትታወቃለች። የበርካታ ቱሪስቶች መዳረሻ ከሆኑ አካባቢዎች መካከል በዓለም የቅርስ መዝገብ የሰፈረው የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ጎንደርን ከፋሲል ግንብ ነጥሎ ማየት ይከብዳል። ስለ ጎንደር የተዜሙ ሙዚቃዎች የሚነግሩንም ይህንኑ ነው። ዛሬ ዛሬ ግን የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት ስም የሚነሳው በአስደናቂነቱ፣ በታሪካዊነቱና የኪነ ህንፃ ጥበቡ ብቻ ሳይሆን አደጋ የተጋረጠበት ቅርስ በመሆኑ ነው። በስፍራው ያገኘናቸው ጎብኚዎችም የፋሲል ግንብ ህልውና እንዳሳሰባቸው ገልፀውልናል። የአፄ ፋሲል ቤተ መንግሥት መቆየት ፋሲልን ሲጎበኝ የመጀመሪያው ነው። “በጣም የሚገርም ጥበብ ነው ያየሁት። ታሪካዊ ቦታ ነው። ታሪካዊ በመሆኑ ደግሞ ለትውልድ የሚተላለፍ መሆን ነበረበት” ይላል። መቆየት ቤተ መንግሥቱን ተሰነጣጥቆና ተሰባብሮ ሲያየው ስሜቱ እንደተነካ ገልጿል። “ለምን ጥገና አይደረግለትም?” ሲል የሁሉም የሆነውን ጥያቄ ይጠይቃል። መንግሥትና የሚመለከተው የቅርስ ጥበቃ አካል ምን እየሠራ እንደሆነ ማወቅና መከታተል ያስፈልጋል ሲልም አስተያየቱን ሰጥቷል። ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር የሄደው ሌላው ጎብኝ ሳሙኤል በለጠም “ቤተ መንግሥቱን ሳየው ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነው የተሰማኝ” ይላል። ጥበብ የተሞላበትን ኪነ ህንፃ ሲያይ በኢትዮጵያዊነቱ ኩራት ተሰምቶታል። በሌላ በኩል ደግሞ ቅርሱ ጥበቃና እንክብካቤ መነፈጉ አሳፍሮታል። ሳሙኤል ይህን የተደበላለቀ ስሜት ውጦ ዝም አላለም። በጉዳዩ
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

በሐረር ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት አደረሱ

በሀረሪ ክልል ማንነታቸው ያልታወቁ የመሬት ይገባናል ጥያቄ ያነሱ ግለሰቦች በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውና በርካታ ቤቶችንም ማፍረሳቸው ተገለፅ፡፡ በአሁኑ ሰዓት አካባቢው እየተረጋጋ መሆኑን የገለፁት ቅሬታ አቅራቢዎች ጥቃቱ ግን ብሔር ተኮር እንደሆነ ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚነገረው ስህተት ነው ብለዋል፤ ፖሊስ አካባቢውን አረጋግቻለሁ፣ እርቅ ለመፍጠርም ጥረት እያደረግኩ ነው ብሏል፡፡ የዐይን እማኞች በአካባቢው መከላከያ ሰራዊት ሰፍሮ ይገኛል ብለዋል፡፡ ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሠራተኞች ሥራ የማቆም አድማ መትተዋል።

ሠራተኞች አድማ የመቱበት ምክንያት በተደጋጋሚ ጊዜ አቅርበናል ያሉት የደመወዝ ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ መሆኑን ተናግረዋል። ሠራተኞቹ ደኅንነታቸው እንደማይጠበቅና ለፆታዊ ጥቃትና ለዝርፊያም እንደሚጋለጡ ገልፀዋል። በኢንቨስትመንት ኮሚሽን የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ በላይ ኃይለሚካኤል “ችግሩ የአንዳንድ ኩባንያዎችና የአስተዳደር በደል ነው” ብለዋል። ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

የክልል መንግሥታት የሃብት ክፍፍልን የተመለከተው ጉዳይ ፍተሻ እየተደረገበት መሆኑ ተሰማ

ላለፉት 3 ዓመታት ሲያገለግል የነበረው የበጀት ቀመር ድልድል እስከ 2012 ብቻ የሚያገለግል ሲሆን የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት የሃብት ክፍፍልን የተመለከተው ጉዳይ ፍተሻ እየረደረገበት በመሆኑ አሰራሩን የሚመለከት በአዋጅ ደረጃ የሚወጣ ህግ ለማዘጋጀት ምክክር እየተደረገ ነው ። የኢትዮጵያ የፌደሬሽን ምክር ቤት እስካሁን የበጀት ክፍፍል የሚያደርግ ቀመር ለ 7 ጊዜ ያዘጋጀና እያሻሻለ ጥቅም ላይ ያዋለ ቢሆንም ወጥ የሆነ የሕግ ማዕቀፍ እንዳልነበረው ነው የሚነገረው ፡፡ ይህም በመሆኑ ከተለያዩ አካላት የበጀት ፍትሃዊነት ጥያቄዎች እንዲነሱና ክልሎች ተደጋጋሚ የበጀት ድጎማ እና የገንዘብ ጥያቄዎችን እንዲያነሱ ሲያደርጋቸው ቆይቷል ። ላለፉት 3 አመታት ሲያገለግል የነበረው የበጀት ቀመር ድልድል እስከ 2012 ብቻ የሚያገለግል ሲሆን የፌዴራል እና የክልል መንግስታት የሃብት ክፍፍልን የተመለከተው ጉዳይ ፍተሻ እየረደረገበት በመሆኑ አሰራሩን የሚመለከት በአዋጅ ደረጃ የሚወጣ ህግ ለማዘጋጀት ምክክር እየተደረገ ነው ።ሕጉ ውይይት ከተደረገበት በሁዋላ በአሰራሩ ላይ የሚታዩ ችግሮችን በሚያስወግድ መንገድ ተዘጋጅቶ ይቀርባል ተብሏል፡፡ https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/4A946DBA_2_dwdownload.mp3
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

አዲሱ ፓርቲ፤ ይመጣልናል ወይስ ይመጣብናል? አያሌው አስረስ

Addis Admass አያሌው አስረስ   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ በኢሕአዴግ ሊቀመንበርነታቸውና በጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣናቸው፣ ከአምስቱ ክልሎች ማለትም ከጋምቤላ፣ ከቤንሻንጉል፣ ከሶማሊያ፣ ከአፋርና ከሐረሪ ከመጡ ሰዎች ጋር በጽ/ቤታቸው ሰሞኑን ተወያይተዋል፡፡ ተሰብሳቢዎቹ የመጡበት ብሔር ቢኖርም የመጡት የብሔር ውክልናን ለማጋነን ስላልሆነ፣ የየብሔራቸው ተወካይ አድርጌ ላያቸው አልፈለግሁም፡፡ የኢሕአዴግ ሊቀመንበሩ በመጪው ጊዜ ኢሕአዴግና አጋር ድርጅቶች የሚለው አጠራርም አሠራርም እንደሚቀር፣ ኢሕአዴግ ፈርሶ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚሳተፉበት ኅብረ ብሔራዊ ፓርቲ እንደሚደራጅ፣ ለዚሁም ጥናት እየተደረገ መሆኑን ገልጠዋል፡፡ የእነሱም ለስብሰባ መቀመጥ ለአዲሱ ፓርቲ ምሥረታ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ አዲስ ፓርቲ ለመመሥረት የተጀመረው እንቅስቃሴ፣ የኢሕአዴግን ሞት ለምንመኝ ለእኔና ለእኔ ቢጤዎች፤ ትልቅ የምሥራች መሆኑን የምገልጠው በድርብ መስመር ነው፡፡ የኢሕአዴግ መፍረስና በአዲስ ፓርቲ መተካት እፎይ የሚያሰኝ እርምጃ የሚሆነው፣ አዲሱ ፓርቲ ከኢሕአዴግ ተውሳክ የፀዳ ከሆነ ነው፡፡ የኢሕአዴግ ተውሳክ ምንድነው የሚለውን እመለስበታለሁ፡፡ ከዚያ በፊት እንደ እኔ ለውጥ ለሚፈልጉት ሁሉ አንድ ነገር ላስገንዝብ፡፡ መዲናችንን አዲስ አበባን እንደ ሞዴል እንውሰድ። አዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ልደታ፣ ጉለሌ፣ የካ፣ ቦሌ ወዘተ የሚባሉ ክፍለ ከተሞች አሏት፡፡ የየካ ኗሪ ሕዝብ የቦሌን፣ የየካው የላፍቶን ኗሪ አይተካም፡፡ ቢቆጠር ቢመዘገብ፣ የሚቆጠረውና የሚመዘገበው በዚያው በሚኖርበት በቦሌ፣ በየካ፣ በልደታ ወዘተ ነው፡፡ አዲሱ ፓርቲም ሲደራጅ አባል የሚያደርጋቸው ሰዎች፣ ፓርቲው የሚደራጅበት አካባቢ ሰዎች መሆናቸው ግድ ነው፡፡ ወላይታ ላይ የወላይታ ተወላጆች ቢበዙ ኃጢያት ሊሆን አይችልም፡፡ የከፋ ኃጢያት የሚሆነው እዚያ አካባቢ የሚኖር ትግሬ፣ ጉራጌ፣ አማራ፣ ኦሮሞ ወዘተ አባል እንዳይሆን ሲገፋና በፓርቲው
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

መወለድ ኩራት? ኩራት አይደለም፤ አይሆንም! ( ዮሃንስ ሰ )

Addis Admass ዮሃንስ ሰ ከመወለድ በኋላ፣ በስራ የሚቀዳጁት ስኬትና የግል ብቃት ነው ኩራት! “የሉሲ ጉዞ”፣ ሸክሙ ትልቅ ነው፤ የሰላምና የፍቅር መልእክትን ሰንቋል፡፡ ቢጨንቀን ነው። የጨነቀው ብዙ ነገር ያደርጋል፡፡ ሉሲን ከሞት ለማስነሳት ይሞክራል፡፡ በእውን ዮሚሊዩን ዓመታትን ተሻግራ፣ “ሕይወት አዳሽ” እንድትሆንልን፤ ቢያንስ ቢያንስ የማገገሚያ ተስፋ እንድትሰጠን፣ አልያም ጊዜያዊ የህመም ማስታገሻ ፋታ እንድታስገኝልን ላይ ታች የምንሯሯጠው፣ ቢጨንቀን ነው፡፡ አገር ምድሩ፣ በጭፍን አስተሳሰብ ሲሳከር፣ ሰው ቢጨነቅ አይበ ዛበትም፡፡ በተብረከረከ ኢኮኖሚና በተናጋ ኑሮ ላይ፣ ኢንቨስትመንትን የማስተጓጎልና የማውደድ፣ ትራንስፓርትን የመዝጋት የመዝረፍ አጥፊ ዘመቻ ሲቀጣጣል…… በዘር እንድንቧደን የሚቀሰቅሱ ክፉዎች እየገነኑ “በነፃነት ”በአገሬውን ሲያምሱ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጦር ሰራዊት ካልተሰማራ በቀር መረጋጋት የከበደው አገር ሲሆንብን፣ ያሳስባል፡፡ በህልውና ለመቆየትና ከፍፁም ጥፋት ለመዳን የሚረዳ ከሆነ፣ ሉሲን ከሞት ለመመለስ እስከ መመኘት ያደርሳል፡፡ በአንዳች ተዓምር የአገር አንድነት እንዲያገግም ብቻ ሳይሆን፣ ሰላምና ፍቅርም እንዲበርከትልን የምታግዘን ከሆነ፣ ሉሊን ከሞት እንድትመለስልን ብንመኝ ይፈረድብናል? በጭፍን እምነት መናቆርን፣ በጭፍን ስሜት መራኮትን፣ በዘረኝነት መጠፋፋትን እየሰበኩ እሳት የሚጭሩና የሚያራግቡ ምግባረ ብልሹ ጋጠወጦችና የለየላቸው የክፋት አበጋዞች የገነኑቦት ዘመን ላይ ነን፡፡ በይሁንታ ወይም በዝምታ ከመመልከት ይልቅ፣ ሳይረፍድብን አስቀድመን መከላከል ነበር የሚሻለን፡፡ ነገር ግን፣ አስቀድሞ መጠንቀቅና ጥፋትን መከላከል፣ እሳቱን ቶሎ ማብረድ፣ የተሳሳተውን ማስተካከልና የተጣመመውን መንገድ በጊዜ ማቃናት እየተቻለ፣ በተቃራኒው የጥፋት ጅምር ተለኩሶ ከዳር ዳር እስኪዳረስ በይሁንታ ወይም በዝምታ መጠበቅ የተላመደ አገር ሆነ፡፡ ጥቂቶቹ የክፋት አወራዎችና ጭፍራዎች፣ በየቦታው እየገነኑ፣ አሳፋሪ አስፀያፊያና ዘግናኝ የጥፋት
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

“ከህደት ተፈፀሞብናል” – ዶ/ር ደብረፅዮን

ሰላም ገረመው (Addis Admass) ወደ ትግራይ ክልል ያመራሁት ከክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዩን ገ/ሚካኤል ጋር ቃለ ምልልስ ለማድረግ ነበር፡፡ ጉዞዬን በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አድርጌ ባለፈው ማክሰኞ ማለዳ ላይ ትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ገባሁ፡፡ ከአየር ማረፈያው ጀምሮ ሆቴሌ ድረስ እንዲሁም በመቀሌ ቆይታዬ ሁሉ የትራንሰፖርት አገልግሎት የሰጡኝ ባለታክሲና ባለባጃጅ ፍፁም ትሁትና አንግዳ አክባሪ ናቸው፡፡ ያለ ክፍያ እንግድነቴን አክብረው አስተናግደውኛል፡፡ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ቢሮ በቀጠሮዬ ሰዓት ደረስኩ፡፡ በር ላይ የነበሩት ጥበቃዎች የተቀበሉኝ በአክብሮት ነው፡፡ ቋንቋቸውንአለመቻሌ የፈጠረብኝ ችግር አልነበረም፡፡ አስተርጓሚ ተመድቦልኝ ወደ ቢሮአቸው ተላኩ፡፡ ቢሮአቸው ስደርስ ዶ/ር ደብረፅዮን ከአሜሪካ ከጀርመን፣ ከኖርዌይና ከእስራኤል አምባሳደሮች ጋር ዉይይት ላይ ነበሩ፡፡ ተራዬ እስኪደርስ ግማሽ ሰዓት ያህል ጠብቄ ገባሁ፡፡ዶ/ር ደብረፅዮን ከወንበራቸው ተነሰተውበአክብሮት ተቀበሉኝ፡፡ ለጥያቄዎቼ ሁሉ ምላሸ ለመስጠት ፍቃደኝነታቸውንም ገለፁልኝ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰጡን ምላሾች የመጀመሪያው ክፍል እነሆ፡- የትግራይ ክልል ዋንኛ ችግር ምንድነው? የክልሉ ችግር ብዙ ነው፡፡ በስፋት በአገር ደረጃም ሆነ በክልላችን ችግሮች አሉ፡፡ አንዱ ችግር ድህነት ነው፤ ብዙ ተሰርቷል ነገር ግን መነሻችን በጣም ዝቅ ያለ ድህነት ውስጥ በመሆኑ ገና ብዙ ይቀራል፡፡ ብዙ ርቀት ሄደናል፤ ግን አሁንም የተሸከምነው ድህነት በጣም ትልቅ ነው፤ ስለዚህ ትልቁ ፈታኝ ስራችን ህብረተሰቡን ከድህነት ማውጣት ነው፡፡ ሌላው ችግር የመልካም አስተዳደር ነው። የመልካም አስተዳደር እጦት ሲኖር ድህነቱ እንዲባባስ ነው የሚያደርገው፤ ምክንያቱም አስተዳደሩ በጎ የአገልግሎት አሰጣጥ ከሌለው የህዝቡ ችግር እየተባባሰ ይመጣል፡፡ ሌላው ልማት የምንለው ጉዳይ ነው፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

32,653 የ20/80 ቤቶች እና 18,576 የ40/60 ቤቶች ዕጣ ወጣባቸው ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ከ51ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች በእጣ እያስተላለፈ ነው። የከተማ አስተዳድሩ እጣ ያወጣባቸው ቤቶች በ20/80 እና 40/60 የቤት ልማት መርሃ ግብርን ያካተተ ነው፡፡ Image may contain: one or more people, people sitting and crowd በዛሬው ስነ ስርዓት ዕጣ የወጣባቸው ቤቶች 32653 የ20/80 ቤቶች እና 18576 የ40/60 መርሃ ግብር ቤቶች ናቸው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ እንዳሉት ለእጣ ከቀረቡ ቤቶች ውስጥ ቤቶቹ በተሰሩባቸው አካባቢዎች ላሉ አርሶ አደሮችና የአርሶ አደር ልጆች እጣ ሳይገቡ እንዲያገኙ የከተማ አስተዳድሩ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ከተማዋ የምታኪሂደው የተቀናጀ ልማት ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነትን ያጋገጠ እንዲሆን በማድረግ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ከንቲባው አመልክተዋል፡፡ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ አቶ ዣንጥራር አባይ በእጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት አገራዊ የቤት ችግርን ለመፍታት የህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት ጭምር የቤት ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ ነው፡፡ እንደ ኢቢሲ ዘገባ በዘላቂነት የቤት ችግርን ለመፍታትም የግሉን ዘርፍ ማሳተፍ አማራጭ የሌለው ተግባር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ካለ ደረሰኝ ሲሸጡ የነበሩ 14 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የገቢዎች ሚኒስቴር ባካሄደው ድንገተኛ ዘመቻ ካለ ደረሰኝ ሲሸጡ የነበሩ 14 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። በሚኒስቴሩ የታክስ ማጭበርበር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ገዙ 8 ድርጅቶች ካለ ደረሰኝ በህገ ወጥ መንገድ ሲሸጡ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል። ድርጅቶቹ በመርካቶ፣ ሱማሌ ተራ፣ ሜክሲኮ፣ ጉርድ ሾላ፣ ሃያት እና ካራ አካባቢዎች የተያዙ ናቸው። በዚህም አማክ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ግሬስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ሉህንዳ፣ አይመን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ድኮ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፤ ውበት ጮራ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ሰናይ ዘመን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና ወራን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ናቸው ካለ ደረሰኝ ሲሸጡ የተያዙት። ከዚህ ጋር በተያያዘም 14 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል ሲል የዘገበው ኤፍ ቢሲ ነው።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

8.3 ሚሊዮን በላይ ወገኖች አስቸኳይ የዕለት ደራሽ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል

Reporter Amharic : የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ማክሰኞ የካቲት 26 ቀን 2011 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ቅድመ ሪፖርት፣ በዚህ ዓመት ከ8.3 ሚሊዮን በላይ ወገኖች አስቸኳይ የዕለት ደራሽ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል አለ፡፡ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ሐሙስ የካቲት 28 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ ለኢትዮጵያ ድጋፍ በማድረግ እየተሳተፉ የሚገኙ አካላት ለዚህ ዓመት የሚያደርጉት የዕርዳታ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥበት መድረክ ይፋ እንደሚደረግ አስታውቋል፡፡ በዚህ መድረክ ከሚቀርቡ መረጃዎች መካከል ለአገሪቱ የሚያስፈልገው አስቸኳይ የዕለት ደራሽ ዕርዳታ ከ8.3 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ታሳቢ ያደርጋል ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ የዕርዳታ ምላሽ ዕቅድ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳና በተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች የኢትዮጵያ ቋሚ አስተባባሪ አኒያስ ሹማ፣ እንዲሁም ሌሎች ኃላፊዎች በሚገኙበት ይፋ ሲደረግ፣ በገንዘብ ምን ያህል እንደሚያስፈልግ በሚቀርበው ሰነድ እንደሚገለጽ ተመድ አስታውቋል፡፡ የዘንድሮ የተረጂዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር በአብዛኛው ተቀራራቢ ነው ያለው ተመድ፣ የተረጂዎች ቁጥር ያባባሰው ግን በአገሪቱ የተከሰቱ ግጭቶች ለበርካታ ዜጎች መፈናቀል መንስዔ በመሆናቸው እንደሆነ አስታውቋል፡፡ በመሆኑም በአማራ ክልል ከ90 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ያለው ተመድ፣ በደቡብ ክልል በተለይ በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ዕርዳታ ማቅረብ የሚቻልበት ባለመመቻቸቱ ወይም ምቹ ሁኔታ ባለመኖሩ፣ በርካቶች ትርጉም ያለው ዕርዳታ ማግኘት አልቻሉም ብሏል፡፡ በአማራ ክልል በተለይም ከመካከለኛውና ከምዕራብ ጎንደር አካባቢ የተፈናቀሉት ከ60 ሺሕ በላይ ነዋሪዎች እንደሆኑ፣ ለመፈናቀላቸው መንስዔውም በአማራና በቅማንት ማኅበረሰቦች መካከል የተቀሰቀሰው
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

በአየር ኃይል ማሰልጠኛ በተከሰተ የምግብ መመረዝ የአንድ ሰው ሕይወት አለፈ – በርካታ ሠልጣኞች ሆስፒታል ገብተዋል

በኢትዮጵያ አየር ኃይል ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት) ጠቅላይ መምርያ የትምህርት ማዕከል ምግብ ቤት በተከሰተ የምግብ መመረዝ፣ 270 ያህል ሠልጣኞች ታመው ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ፡፡ ታማኝ የዜና ምንጮች ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የካቲት 22 ቀን 2011 ዓ.ም. በትምህርት ማዕከሉ ምሳቸውን በመመገብ ላይ የነበሩ በርካታ ተማሪዎች በሕመም በምግብ አዳራሽ ውስጥ ወድቀዋል፡፡ ከ260 በላይ የሚሆኑ ዕጩ መኮንኖች ሆራ አካባቢ በሚገኘው የአየር ኃይል ሆስፒታልና በከተማው ሆስፒታል እንደተወሰዱ ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ ሠልጣኞች ሕክምና ተደርጎላቸው እንደወጡ፣ የአንድ ተማሪ ሕይወት ግን ማለፉን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ ለሠርግ ዕረፍት ወጥተው የነበሩ የአየር ኃይል የሕክምና ዳይሬክተር፣ ዕረፍታቸውን አቋርጠው የሕክምና ሥራውን ሲያተባብሩ እንደነበር ታውቋል፡፡ ሠልጣኞቹ የአውሮፕላን ጥገናና የማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ተማሪዎች እንደሆኑ የገለጹት ምንጮች፣ ሠልጣኝ አብራሪዎች በወቅቱ በምግብ ቤቱ አዳራሽ ውስጥ እንዳልነበሩ ተነግሯል፡፡ የምግብ መመረዙ በምን ምክንያት ሊከሰት እንደቻለ የፓስተር ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች ወደ ሥፍራው በማቅናት ናሙና እንደወሰዱ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ‹‹ጉዳዩ በምርመራ ላይ ነው፡፡ በባክቴሪያ የመጣው ወይስ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ወንጀል ነው የሚለው እየተጣራ ነው፤›› ብለዋል፡፡ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ አማካሪ የሆኑት ኮሎኔል ባሻ ደገፋ ዜናውን አስተባብለዋል፡፡ ‹‹የታመመም የሞተም ሰው የለንም፤›› ብለዋል፡፡ አየር ኃይል በአሁኑ ወቅት መሠረታዊ የሆነ የለውጥ ፕሮግራም በማካሄድ ላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ከ21 ዓመት በላይ የሆነ ሰው የጦር መሣሪያ ፈቃድ በማውጣት ሊታጠቅ ይችላል የሚል ሕግ ተረቀቀ

Reporter Amharic ከመከላከያ ሠራዊቱ ውጪ የሆኑ ሕግ አስከባሪ አካላት መታጠቅ የሚችሉትን የጦር መሣሪያ ዓይነት የሚወሰን ሕግ ተረቀቀ ከ21 ዓመት በላይ የሆነ ጤነኛ ሰው ለግለሰብ የሚፈቀድ የጦር መሣሪያ ፈቃድ በማውጣት ሊታጠቅ ይችላል በጦር መሣሪያ ንግድና በድለላ ለሚሰማሩ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ይሰጣል ከአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በስተቀር ሌሎች በክልል መንግሥታትና በፈዴራል መንግሥት የተደራጁ ሕግ አስከባሪ አካላት፣ መታጠቅ የሚችሉትን የጦር መሣሪያ ዓይነት የሚወስን ረቂቅ ሕግ ተጠናቆ ለውይይት ቀረበ። ረቂቅ ሕጉ የተዘጋጀው በፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሥር በተዋቀረ የሕግና ከጉዳዩ ጋር የተገናኘ የቴክኒክ ዕውቀት ባላቸው የባለሙያዎች ቡድን ሲሆን፣ የሕግ ሰነዱ ተጠናቆ በአሁኑ ወቅት ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገበት እንደሚገኝ ምንጮች ገልጸዋል። ሪፖርተር ያገኘው ረቂቅ የሕግ ሰነድ ‹‹የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የጦር መሣሪያ ቁጥጥር አዋጅ›› የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን፣ የጦር መሣሪያ ቁጥጥር የአገርንና የሕዝብን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ፣ እንዲሁም የዜጎችንና የሕዝቦችን መብትና ደኅንነት ለማስከበር አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ የተረቀቀ መሆኑን የሰነዱ መግቢያ ያስገነዝባል። በማከለም ግለሰቦች የታጠቋቸው የጦር መሣሪያዎች የኅብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ተግባር ብቻ ሊውል የሚቻልበትን አሠራር መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ እንዲሁም በሥራ ላይ ባሉ ሕጎችና አሠራሮች ያልተሸፈኑ ጉዳዮችን በዝርዝር ሕግ መደንገግና ወጥነት ያለው ሥርዓት መፍጠር በማስፈለጉ ሕጉ መዘጋጀቱን የሕግ ሰነዱ መግቢያ አንቀጾች ያስረዳሉ። ረቂቅ ሕጉ ለፀጥታ አስከባሪ አካላት የሚፈቀድ የጦር መሣሪያ ዓይነትና ብዛትን የሚደነግግ ሲሆን፣ የሕግ (ፀጥታ) አስከባሪ አካላት ለሚለውም የሕግ ትርጓሜ አካቷል። ‹‹ሕግ አስከባሪ ማለት
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

አዲስ አበባ ቤት ኪራይ አደገኛ ራስ ምታት ሆኗል

የቤት ኪራይ የብዙዎቻችን ኢትዮጵያዊያን ራስ ምታት!
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Video

የፈጣን አውቶብስ መስመር ግንባታ ምክንያት በአዲስ አበባ ከስድስት መቶ ቤቶች በላይ ይፈርሳሉ ተባለ፡፡

በአዲስ አበባ በቅርቡ ስራ ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀው የፈጣን አውቶብስ መስመር ግንባታ ምክንያት ከስድስት መቶ ቤቶች በላይ ይፈርሳሉ ተባለ፡፡ ቢ2 ተብሎ የሚጠራው የፈጣን አውቶብስ መስመር ከዊንጌት ተነስቶ በአውቶብስ ተራ አድርጎ በተክለሃይማኖት ሜክሲኮ፣ ከሜክሲኮ በቄራ አድርጎ ወደ ጎፋ፣ ከዚያም በጀርመን አደባባይ ጀሞ የሚደርስ መሆኑን ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሰምተናል፡፡ አጠቃላይ ርዝመቱም 17.4 ኪሎ ሜትር ነው ተብሏል፡፡ አውቶብሶች ብቻ እንዲጓዙበት ለሚገነባው መንገድ 127 ሚሊዮን ዩሮ ወይንም ዛሬ በዋለው ምንዛሬ አራት ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተብሏል፡፡ ከሚያስፈልገው 4 ቢሊየን ብር ውስጥም 2.7 ቢሊዮን ብሩ ከፈረንሳይ መንግስት በብድር መገኘቱን ከመንገዶች ባለስልጣን ሰምተናል፡፡ ቀሪው ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚሸፈን ነው ተብሏል፡፡ 17.4 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለውንና ከዌንጌት ተነስቶ በአውቶብስ ተራ፣ በሜክሲኮ፣ ቄራ፣ ጀርመን አደባባይ፣ ጆሞ የሚደርሰውን የፈጣን አውቶቡስ መስመር ግንባታ ለመጀመር መንገዱ በሚያልፍባቸው አካባቢዎች ከሚገኙ ተነሺዎች ጋር ውይይት ተጀምሯል ተብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት የመንገዶች ባለስልጣን ለይቶ የያዛቸው የልማት ተነሺዎች 665 ቤቶች፣ 396 የቤት አጥሮች 935 የመብራትና 90 የቴሌ ምሰሶዎች መሆናቸውን ሰምተናል፡፡ የነዚህ የወሰን ማስከበር ስራዎች እንደተጠናቀቁ የመንገዱ ግንባታ በ2012 በጀት አመት ለመጀመር ታቅዷል ተብሏል፡፡ የፈጣን አውቶብስ መስመሩን መገንባት በአዲስ አበባ የሚታየውን የትራፊክ መጨናነቅ ለማቃለልና የብዙሃን ትራንስፖርትን ለማስፋፋት ትልቅ እገዛ ያደርጋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ ከዚህ በኋላ የሚገነቡና የአዋጭነት ጥናት እየተካሄደባቸው ያሉ መስመሮች መኖራቸውም ተነግሯል፡፡ እነዚህም ከጦር ሀይሎች ቦሌ፣ ከቦሌ ለገሃር፣ ከሽሮ ሜዳ መገናኛ እና ከዊንጌት አየር ጤና
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ከ300 በላይ የሺሻ ዕቃዎች ተወገዱ

በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ 09 ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከ300 በላይ የሺሻ ዕቃዎች መወገዳቸውን የወረዳው ቢሮ ኃላፊ ኢንስፔክተር ገብረሚካኤል ወልደጊዮርጊስ አስታውቀዋል። ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት በተወሰደው እርምጃም የሺሻ ማስጨሻ ዕቃዎች፣ ዕፅ፣ እንዲሁም ጫት በወረዳው በሚገኝ ገላጣ ስፍራ ላይ በጥንቃቄ መወገዱ ተገልጿል፡፡ Image may contain: one or more people, crowd and outdoor በወረዳው በስፋት የሚስተዋለው አዋኪ ድርጊት፣ ሺሻ ማስጨስና ጫት ማስቃም መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው፤ በተለያየ ጊዜያት ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ቢሞከርም፤ ግለሰቦች ቤት በሚያከራዩበት ወቅት ተከራዩ ለምን ዓላማ እንደሚያውለው አለማጣራት ይስተዋላል ብለዋል። የወረዳው ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ኃላፊ የሆኑት ዋና ሳጂን ታሪኩ በበኩላቸው በርካታ ጊዜ በወረዳው የተለያዩ ወንጀሎች ከተሠሩ በኃላ ሺሻ ቤቶቹ መደበቂያ ይሆናሉ ብለዋል። እነዚህ ቤቶች ወንጀለኞች መሸሸጊያ ከመሆናቸውም በላይ ዕፁን ከተጠቀሙም በኃላም በተለያዩ ወንጀሎች ላይ ሲሳተፉ እንደሚስተዋልም ተገልጿል፡፡ Image may contain: 2 people, shoes and outdoor ህብረተሰቡም ለራሳቸው ልጆችና ነገ ሃገር ተረካቢ ለሆነው ትውልድ በማሰብ ይህን አዋኪ ድርጊት ከፀጥታ ኃይሎች ጎን በመሰለፍ እንዲከላከል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ Image may contain: one or more people and outdoor የክፍለ ከተማው ኃላፊ ሻምበል ተክላይ አረጋዊም እንደሚሉት በክፍለ ከተማው ውስጥ ከሚገኙት ወረዳዎች መካከል ሺሻና ጫት ቤት በስፋት የሚስተዋልበት ወረዳ 09 አንዱ እንደሆነ ተናግረው፤ በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ ለ3ተኛ ጊዜ እያስወገደ እንደሚገኝ አስታውሰዋል፡፡ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እየተካሄደ እንደሚገኝ አክለው ተናግረዋል፡፡ ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሕዝብ ግንኝነት ዳይሬክቶሬት
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በር ላይ በርካታ ሐሰተኛ የቢጫ ወባ ካርዶች በጠራራ ጸሐይ ይቸበችባሉ።

የሐሰተኛ (ፎርጅድ) የቢጫ ወባ ካርድ ነገር – BBC በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በር ላይ በርካታ ሐሰተኛ የቢጫ ወባ ካርዶች በጠራራ ጸሐይ ይቸበችባሉ። ሰዎች ክትባቱን ከመውሰድ ይልቅ ካርዱን ገዝተው መሄድ ይቀላቸዋል። ይህን ሁኔታ ለመግታት ጥፋተኞችን ሕግ ፊት የማቅረብ ሥራ ስንሠራ ቆይተናል ይላሉ ዶ/ር በየነ። “ሐሰተኛ ባለማኅተም ካርዶቹ ከሆስፒታሉ የሚወጡ ናቸው ወይ? በሚል ሲጠየቁም “የለም ሙሉ በሙሉ ውጭ ተመሳስለው የሚሠሩ ናቸው” ብለዋል። ዶ/ር በየነ ጨምረው ይህንን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ «ባር-ኮድ» ማንበብ የሚችል ዲጂታል ካርድ በመዘጋጀት ላይ እንደሆነ ነግረውናል። ይህ ካርድ በኮምፒውተር መረጋገጥ የሚችል የራሱ መለያ ቁጥር ስለሚኖረው በዚህ ዓመት መጨረሻ ቢጫ ካርዱን ይተካል ተብሎ ይጠበቃል። ለዚህ የሚረዱ መሣሪያዎች ግዢ ተጠናቆ ከቴሌ የቪፒኤን ፍቃድ እየተጠበቀ ነው። ይህ ዲጂታል ካርድ ተግባራዊ ሲሆን በተጭበረበረ ቢጫ ወባ ካርድ ከአገር የሚወጡ ዜጎችን በቀላሉ መቆጣጠር እንደሚቻልም ኃላፊው ለቢቢሲ ተናግረዋል። ቢጫ ወባ ክትባትን በርካታ ኤምባሲዎች ለተጓዦች በግዴታነት ያስቀምጣሉ። ኢትዮጵያም ይህንኑ ተግባራዊ የምታደርግባቸው ጎብኚዎች በርካታ ናቸው። ለመሆኑ ከአገር የሚወጡ ተጓዦች በሙሉ ቢጫ ወባ ክትባትን ለመከተብ ይገደዳሉ? አንዳንድ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ባለፈው ሳምንታት ምንጭ ጠቅሰው እንደዘገቡት ከሆነ ማንኛውም በቦሌ ከአገር የሚወጣ ዜጋና ወደ ከየትም አገር ወደ አገር ቤት የሚገባ ጎብኚ የቢጫ ወባ ክትባት መውሰዱን ያሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት መያዝ እንዳለበትና ይህም ግዴታ ሊደረግ እንደሆነ ዘግበዋል። ይህ ምን ያህል እውነት ነው በሚል ዶ/ር በየነ ሞገስ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ም/ዋና ዳይሬክተርን ጠይቀናቸው ነበር።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ከቤት ውጭ በአምስት ሺ ሜትር ሪከርድ መስበር ወይም ፈጣን ሰአት ማስመዝገብ እፈልጋለሁ – አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ

አሜሪካ ቦስተን ውስጥ በተካሄደ የአንድ ማይል (1.6 ኪሎ ሜትር) የቤት ውስጥ ውድድር ከ22 ዓመታት በፊት በሞሮኳዊው አትሌት ሂሻም አልገሩሽ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ሰብሮታል። ከትላንት በስቲያ እሁድ እለት በተደረገው በዚህ የቤት ውስጥ ውድድር 3፡47፡01 በመግባት ሪከርዱን አሻሽሏል። በዚህ ውድድር ላይ አሜሪካዊው ጆኒ ግሬጎሬክ 3፡49፡98 በመግባት በሁለተኛነት አጠናቋል። “ሪከርድ መስበር በጣም ደስ ይላል፤ አንድ ሰው የሚሮጠው የሆነ ነገር ለማግኘት ነው።” የሚለው አትሌቱ ለሯጭም ከፍተኛ ደረጃ እንደሆነ ይናገራል። “አንድ አትሌት በህይወቱ የሚያስደስተው ነገር ኦሎምፒክ ማሸነፍና የአለም ሪከርድ መስበር ነው። ስለዚህ በጣም ደስ ብሎኛል።” በማለት ለቢቢሲ ገልጿል። ሪከርድ በመስበሩ የሚያገኘው ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ ከቢቢሲ ለቀረበለት ጥያቄም ከዚህ ቀደም ሪከርድ የሚሰብር የሚያገኘውን ያህል እንደሆነ ተናግሯል። በአልግሩሽ ተይዞ የነበረውን ሬከርድ በአንድ ደቂቃ በአርባ አራት ሰከንዶች ያሻሻለው ዮሚፍ በሶስተኛው ሙከራ ሪከርድ መስበር እንደቻለም ተዘግቧል። የ21 አመቱ ዮሚፍ ከሶስት ሳምንታት በፊት ኒውዮርክ ውስጥ በተመሳሳይ ርቀት ውድድር ያደረገ ሲሆን፤ በወቅቱም በ0.01 ሴንቲ ሰከንድ ምክንያት ሪከርዱን ሳይሰብር ቀርቷል። በወቅቱ ስለነበረው ስሜትም አትሌቱ ለቢቢሲ ተናግሯል ” ያኔ በጣም ተሰምቶኝ ነበር፤ ውድድሩን ስጨርስ ዝቅ ብየ ቢሆን ኖሮ ሪከርዱን እሰብረው ነበር።” የሚለው አትሌቱ በቀጣይነትም ረጅምና መካከለኛ ርቀት የመሮጥ እቅድ እንዳለው ተናግሯል። “ትልቁ ሀሳቤ ከቤት ውጭ በአምስት ሺ ሜትር ሪከርድ መስበር ወይም ፈጣን ሰአት ማስመዝገብ እፈልጋለሁ” ብሏል። ዮሚፍ ያስመዘገበው ሰአት በኢትዮጵያም ውስጥ ፈጣኑ ሲሆን ይህም በአማን ወቴ 3፡48፡60 ተይዞ
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Sports

የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አስተዳደር ስኬቶች እና ተግዳሮቶች ምንድናቸው? የወደፊት አቅጣጫውስ?

BBC – የቢቢሲ አማርኛ ባልደረቦች በተለያዩ ስፍራዎች ጉዞ በማድረግ ከተለያዩ የማህብረሰብ ክፍል አባላት ጋር በበርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይቶች በማድረግ ላይ ናቸው። ከነዚህም አንዱ ትናንት ሰኞ የካቲት 25 ረፋድ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ተግባቦት ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር የውይይት መድረክ በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ተዘጋጅቶ ነበር። ቢሰጥ አያሌው (ዶ/ር) የጋዜጠኝነት እና ተግባቦት ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ ዳዊት አሞኝ (ዶ/ር) የሂውማኒቲስ ፋካሊቲ ኃላፊ እና አደም ጫኔ (ዶ/ር) የሂውማኒቲስ ፋካሊቲ የውይይቱ ዋነኛ ጭብጥ የነበረውም ወደ ስልጣን ከመጣ አንድ ዓመት ለመድፈን የተቃረበው የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አስተዳደር ስኬቶች እና ተግዳሮቶች ምንድናቸው? የወደፊት አቅጣጫውስ? የሚል ሲሆን ትኩረቱንም በመገናኛ ብዙሃን ላይ አድርጎ ነበር። በውይይቱ ላይ ቢሰጥ አያሌው (ዶ/ር) የጋዜጠኝነት እና ተግባቦት ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ ዳዊት አሞኝ (ዶ/ር) የሂውማኒቲስ ፋካሊቲ ኃላፊ እና አደም ጫኔ (ዶ/ር) የሂውማኒቲስ ፋካሊቲ ምክትል ኃላፊ በመወያያ ርዕሱ ላይ አስተያየታቸውን ያጋሩ ሲሆን፤ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና መምህራን የውይይቱ ታዳሚዎች ነበሩ። ውይይቱ የተጀመረው ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በመገናኛ ብዙሃን ላይ የታዩት በጎ ለውጦች ምንድናቸው በሚለው የመወያያ ጥያቄ ነበር። ዶ/ር አደም በመገናኛ ብዙሃን ዙሪያ ታይተዋል ካሏቸው ለውጦች መካከል የሚዲያ ምህዳሩ መከፈት መጀመሩን በዋናነት ያነሳሉ። ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ወደ 20 የሚጠጉ አዲስ የህትመት እና የብሮድካስት ሚዲያዎች መፈጠራቸውን እና ከሃገር ውጪ የነበሩ መገናኛ ብዙሃን ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጋቸውን የሚዲያው ምህዳር እየሰፋ ስለመሆኑ ማሳያ መሆናቸውን ዶ/ር አደም ይናገራሉ። ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ ታዳሚዎች መካከል ”ከዚህ በተጨማሪ አይነኬ ይባሉ የነበሩ ጉዳዮች በመንግሥት ሚዲያዎች ሁሉ ሲቀርቡ እያየን ነው፤ በርካታ ድምጾችም
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

በአማራ ክልል ከ91 ሺ በላይ ተፈናቃዮች በከፋ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ገለፁ።

በማዕከላዊና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች በቅርቡ በተፈጠረው ግጭት ቤት ንብረታቸውን ጥለው የሸሹና በመጠለያ ጣብያ ውስጥ ያሉ ተፈናቃዮች በከፋ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ገለፁ። በዚሁ አካባቢ ያሉና ዘንድሮ በክልልም ሆነ በሀገርቀፍ ደረጃ ብሄራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችም እስካሁን የፈተና ፎርም አልሞሉም ይላሉ – የማዕከላዊ ጎንደር የዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ።የክልሉ የመንግሥት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት በበኩሉ በክልሉ ከ91ሺ በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ። ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም በቢልየን የሚቆጠር ብር ያስፈልጋል ይህንን ገንዘብ የሚያሰባስብ ግብረ ኃይል ተቋቁሟል። በተለይ በማዕከላዊና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች ያሉ ተፈናቃዮችን በሁለት ወራት ውስጥ ወደ ቀያቸው ለመመለስ መንግሥት ቁሳቁሶችን እያሟላ ሲሆን የተማሪዎችን ችግርም ለመፍታት ዕቅድ ተይዟል ብለዋል የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አሰማኸኝ አስረስ።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Video

የሶማሊላንዷን የወደብ ከተማ በርበራን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኝ አውራ ጎዳና ሊሠራ ነው።

VOA : ሰሜን ምዕራባዊቱን ተገንጣይ ክልል የባሕር እንቅስቃሴዎች መናኸሪያ ሊያደርጋት ይችላል የተባለው መንገድ ግንባታ ማስጀመሪያ የመሠረት ደንጊያ ባለፈው ሣምንት ተጥሏል። የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ መሠረቱን ያኖሩበት ሥነ-ሥርዓት የተከናወነው ዋና ከተማዪቱ ሃርጌሳ ውስጥ ሲሆን የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሙስጠፋ ከማልና በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የዱባዩ የወደብ ላይ አገልግሎቶችና አቅርቦቶች ድጋፍ ሰጭ ኩባንያ ዲፒ ወርልድ ባለሥልጣናትም ተገኝተዋል። 111 ሚሊየን ዶላር እንደሚፈጅ የተነገረለት የበርበራ ሲቪል አይሮፕላን ጣቢያ ግንባታን የሚያካትተው ፕሮጀክት በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑን የሶማሊላንድ የትራንስፖርትና መንገዶች ልማት ሚኒስትር አብዱላሂ አቦኮር ኦስማን ተናግረዋል። ከበርበራ ወደብ ኢትዮጵያ ድንበር የሚያደርሰው አውራ ጎዳና 245 ኪሎ ሜትር የሚሠራው ከአስፋልት ጋር ተመሣሣይ በሆነ ታርማክ ሲሆን 21 ኪሎሜትር ተላላፊና የማቆራረጫ መንገዶችንና ሰባት ድልድዮችን የሚያካትት እንደሆነ ታውቋል። ይህ የበርበራ-ኢትዮጵያ መንገድ ግንባታ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ፣ በሶማሊላንድና በዲፒ ወርልድ መካከል በአመዛኙ በርበራ ወደብን ለማዘመን በሚል የተፈረመ ለሰላሣ ዓመታት የሚዘልቅ የ442 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት አካል ነው። አዲሱ የበርበራ ኮሪዶር ያለማቋረጥ የሚያድገውን የኢትዮጵያን ወጭ ንግድ ለማቀላጠፍ የሚያግዝ ከመሆኑ በተጨማሪ የራሷ የባሕር በር የሌላትን የመቶ ሚሊዮን ሕዝብ ሃገር ኢትዮጵያን ከጂቡቲ ወደብ ብቸኛ ጥገኛነት ለማላቀቅ የሚያስችል አማራጭ እንዲኖራት እንደሚያደርግ የአካባቢው የምጣኔ ኃብት ኤክስፐርቶች ይጠቁማሉ።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

በደቡብ ክልል የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ተገቢውን ድጋፍ ባለማግኘታችው በችግር ላይ መውደቃቸውን ተናገሩ

DW : በደቡብ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ተከስተው በነበሩ ግጭቶች ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ተገቢውን ድጋፍ ባለማግኘታችው በችግር ላይ መውደቃቸውን እየተናገሩ ነው።በአሁኑ ወቅት አልፎ አልፎ በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር የተነሳም ወደ ቀድሞ አካባቢያቸው ለመመለስ ሥጋት እንዳደረባቸው ተፈናቃዮቹ ለዲ ደብሊው ገልጸዋል። የደቡብ ክልል የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ የዕርዳታ አቅርቦቱ አልፎ አልፎ በተለያዩ ምክንያቶች ከሚያጋጥመው የቀናት መዘግየት በስተቀር በተያዘው ዕቅድ መሠረት እየተከናወነ ይገኛል ብሏል። ወደ ቀድሞ ቀዬያቸው ለመመለስ ያጋጠማቸውን የፀጥታ ሥጋት ለመቅረፍም ከፌደራሉ የሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጋር በጥምረት እየተሠራ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ አስታውቋል። https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/577B9D1D_2_dwdownload.mp3  
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ለማበድ እንኳን አገር ያስፈልጋል፤ በአገር ጉዳይ ምሁራንም ሆኑ የሃይማኖት አባቶች ገለልተኛ መሆን አይችሉም – መጋቤ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ

… 16 ዓመት ሙሉ ትምህርት ላይ ቆይቶ ጭንቅላቱ ምንም ያልተዘራበት ሆኖ ይገኛል። ምሁራን ገለልተኛ መሆን የለባቸውም፤ ማንም ከአገር ጉዳይ ገለልተኛ ሊሆን አይችልም። አገር ሲኖር ነው ሁሉም ነገር የሚሆነው። አገር ከሌለ ማንም ሊኖር አይችልም። ለማበድ እንኳን አገር ያስፈልጋል፤ በአገር ጉዳይ ምሁራንም ሆኑ የሃይማኖት አባቶች ገለልተኛ መሆን አይችሉም። በአገር ጉዳይ ላይ ማንም ነው መሥራት ያለበት፤ የአስተሳሰብ ቀረጻ ላይ መሰራት አለበት። አንድ ኢትዮጵያዊ አሜሪካ ውስጥ ቢያብድ ማደንዘዣ ተወግቶ ቦሌ ይጣላል። አንድ ሰው ‹‹እግዚአብሔር የለም›› ማለት ይችላል፤ ‹‹ኢትዮጵያ የለችም›› ማለት ግን አይችልም። እግዚአብሔር የለም ቢል የሚመጣውን ራሱ ይቀበላል፤ ኢትዮጵያ የለችም ካለ ግን ሀገሩን ለቆ ኬንያ መግባት አለበት። ከየካቲት 23 አዲስ ዘመን ቅዳሜ ዕትም ላይ የተወሰደ ለተጨማሪ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/Ama/?p=6023#
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሥራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸው ተሰማ፡፡

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሥራቸውን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸው ተሰማ፡፡ ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ ዩኒቨርስቲውን ለ13 አመታት አገልግለዋል፡፡ ይሁንና የፕሬዝዳንትነቱን ቦታ መልቀቃቸውን ለዩኒቨርስቲው ማሳወቃቸውን ሰምተናል፡፡ በዩኒቨርስቲው የአለም አቀፍና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ተወካይ ወ/ሮ ይዳኙ ማንደፍሮ ለሸገር እንደነገሩት ዶ/ር ደሳለኝ ስልጣናቸውን ለመልቀቃቸው ዝርዝር ምክንያት አልተናገሩም፡፡ ዶ/ር ደሳለኝ በፕሬዝደንትነት ዘመናቸው የጎንደር ዩኒቨርስቲ ውጤታማ እንዲሆን አስችለውታል ተብሏል፡፡ Image may contain: 1 person, suit
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ስለ ኢትዮጵያውያን ጀግንነት የኢጣሊያዊቷ ጋዜጠኛ ጥያቄ እና የካስትሮ ወሽመጥ ቆራጭ መልስ!

≪የኢጣሊያዊቷ ጋዜጠኛ ጥያቄ እና የካስትሮ ወሽመጥ ቆራጭ መልስ!≫ የካቲት 26 1970  ብሔራዊ ድላችን !!! የመስፋፋት ፖሊሲ አራማጁ የሶማሊያ መንግስት በዕብሪተኛው መሪ «በዚያድ ባሬ» ትዕዛዝ የኢትዮጵያን ግዛት ዘልቆ ገባ። ምዕራባዊያኑ ያስታጠቁት ዘመናዊ መሳሪያው፣ ለአመታት የተዘጋጀበት ጠንካራ የጦር ኃይል ሀገራችን ከነበረችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር እጅግ የማይቋቋሙት ጠላት ቢሆንም፣ የፈለገ ቁርሾ ውስጥ ቢገባና እርስ በእርስ ሲባላ ቢቆይም ለባዕድ ወራሪ አንድነቱን ጠግኖ ለሀገሩ መውደቅ የደሙ መለያ የሆነው አበሻ ከያለበት ተጠራርቶ በሀገር ላይ ያንጃበበውን የወረራ ጥቃት ለመቀልበስ ወደፊት አለ። ምንም አይነት የተደራጀ የጦር ኃይል በጊዜው ያልነበራት ኢትዮጵያ በወቅቱ ያቀረበችውን የእናት ሀገር ጥሪ በመቀበል በአጭር ጊዜ 300 ሺህ የሚሊሺያ ሰራዊት ለስልጠና ታጠቅ ጦር ሰፈር ገባ። ከነበረው አጭርና አንገብጋቢ ጊዜ ከሶስት ወር ያልዘለለ ስልጠና የወሰደው ህዝባዊ ጦር ግዛታችንን አልፎ የገባውን ወራሪውን ጦር ሊጠራርግ ወደ ምስራቁ የሀገራችን ክፍል ዘመተ። አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ አንድ ጊዜ ግሩም አርጎ የግማሽ ሰአት ዶክመንተሪ ፊልም የሰራለት የእነ_ጄኔራል ፋንታ በላይ እና የእነ ጄኔራል ለገሰ ተፈራ የአየር ኃይል ምርጥ ብቃት ምስጋና ይግባውና ከሰማይ የቦንብ ውርጅብኝ በተደጋጋሚ እያዘነበ የምድሩን ውጊያ አቀለለው። የሶማሊያ ጦር በአየር ኃይል ፓይለቶቻችን ከላይ እንደእባብ እየተቀጠቀጠ ፍርክርክሱ ሲወጣ፣ እግረኛው ጦር አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የዚያድ ባሬን ጥጋበኛ ጦር አስተነፈሰው። ካራማራ ላይ በተካሄደው ከባድ ውጊያ ከፍተኛ መስዕዋትነት ተከፍሎ የተወረረው የኢትዮጵያ መሬቶች ከጠላት መዳፍ ተላቀቀ። ሶማሊያም የእፍረት ካባዋን ተከናንባና ሁለተኛ አይለምደኝም ብላ በመጣችበት እግሯ
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

የትግራይ ልዩ ሃይል በማይካድራ ከተማ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ እንግልትና ወከባ እያደረሰባቸው መሆኑ ተነገረ::

የትግራይ ልዩ ሃይል በማይካድራ ከተማ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ እንግልትና ወከባ አያደረሰባቸው መሆኑ ተነገረ:: በማይካድራ የሚገኙት የአማራ ተወላጆች እንደተናገሩት በትግራይ ልዩ ሃይል እንግልትና ወከባ እየደረሰብን ነው ብለዋል። በከተማይቱ ትልናት ማታ ጠንከር ያለ ፍተሻ ሲካሄድ አምሽቷል።ቁጥራቸው ያልታወቀ የአማራ ተወላጅ ወጣቶች በትግራይ ልዩ ሃይል ታፍነው ተወስደዋል ሲሉ አክለው በስልክ ያነጋገርናቸው ወጣቶች ገልጸዋል። በምን ምክንያት ነው እንዲህ አይነት ወከባና እንግልት እየደረሰባችሁ የሚገኘው? ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ ወጣቶቹ ሲመልሱ “በእራሳችን መሬት፣መሬታችን መወሰዳቸው ሳያንስ፣ግፍ እየተፈጸመብን የሚገኘው አማራ በመሆናችን ነው።አማርኛ ስንናገር አጥንት ድረስ ሰርገው የሚገቡ ስድቦችን ይሰድቡናል።ከዱላቸው በላይ ስድባው ያመናል።” ሲሉ ተናግረዋል።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ውረሱ ተብለን ነው የተላክነው ያሉ ሕገወጥ ታጣቂዎች በሐረር በርካታ ቤቶችን አፈረሱ።

Image may contain: one or more people and outdoorሐረር ቢራ ፋብሪካ በላይ በትናንትናው እለት ብዙ ቤት አፍርሰዋል ለግዜዉ መከላከያ ደርሶ ባያስጥላቸዉ ኖሮ ጉዳቱ ከዚህ የከፋ ይሆን ነበር። በሰዉ ላይም ጉዳት ደርሷል። አፍራሾቹ የሚሉት ዉረሱ ተብለን ነዉ የተላክነዉ ነዉ የሚሉት ህጋዊ የሆነዉን የነዋሪዎች ቤት እንዲያፈርሱ እና መሬቱን እንዲዎርሱ የላከዉ አካል ማንነቱ ይደረስበታል…አሁንም በቦታዉ መከላከያ ሰራዊት ቢኖሩም አፍራሾቹ በአገባቢዉ ከሚገኝ ጋራ ስር ተደብቀዉ ይገኛሉ። የሐረር ደግሞ የተለየ ነዉ ቤቱ ህጋዊ አፍራሹ ህገወጥ ናቸዉ። እንደምታዩት የቤቶቹን ጣርያ በድንጋይ በሳስተዉታል ክልሉ የህግ የበላይነትን ማስከበር ካቃተዉ ቆየ ነዋሪዎች በሰላም ወጥተዉ የመግባት ህልዉናቸዉ አደጋ ላይ ነዉ በዚህ ጉዳይ ነዋሪዉ ዝም ሊል አይገባም።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ከቆዳ የሚሰሩ ባህላዊ ቁሶች ትኩረት ተነፍገዋል ተባለ

የባህርዳር መለያ ባህላዊ ጥበብ የጣና ሃይቅ ዳርቻዋ የባህር ዳር ከተማ በስፋት ከምትታወቅባቸው ነገሮች መካከል ከቆዳ የሚሰሩት ባህላዊ ቁሶች ይገኙበታል። ከተለያዩ የእንስሳት ቆዳ የሚሠሩት እንደ መቀመጫ፣ አገልግል እና ከበሮ ያሉ ባህላዊ መገልገያዎች የበርካቶችን ቀልብ የሚስቡ የጥብበ ሥራዎች ናቸው። እኒህን መሰል ባህላዊ ቁሶች ከእንስሳት ቆዳ በመስራት ቤተሰብ ከሚያስተዳድሩ የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል አንዱ ገብረመድህን አሞኘ አንዱ ነው። ገብረመድህን ለበርካታ ዓመታት የቆዳ ውጤቶቹን ሰርቶ እየሸጠ የቤተሰቡን የዕለት ፍላጎት ከመሸፈን ውጪ ይህ ነው የሚባል ለውጥ እንዳላስገኘለት ይናገራል። ይሁን እንጂ ገብረመድህን እንደሚለው ከሆነ ለእነዚህ ባህላዊ ጥበባት ትኩረት ቢሰጥ ከእንድ ቤተሰብ አልፈው ለሃገርም ከፍተኛ ገቢ ያስገኛሉ ይላል። የባህር ዳር የጥበብ ስራዎች የቆዳ ውጤት የሆኑ ባህላዊ የጥበብ ሥራዎች በውጪ ጎብኚዎች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት እንዳላቸው የሚናገራው ገብረመድህን እንደማሳያም በባህላዊ መንገድ በቆዳ ሽፋን የሚሰራው መቀመጫ ምን ያክል በውጪ ሃገር ዜጎች ዘንድ ተወዳጅ እንደሆነ ሲያስረዳ ”ቱሪስቶች በጣም ነው የሚወዱት። ገዝተው ይዘው መሄድ ይፈልጋሉ፤ ግን ከባድ ስለሆነ መውሰድ አይችሉም። አማራጭ ስለሌላቸው ፎቶ ተነስተውበት ነው የሚሄዱት” ይላል። ለሥራው ግብዓት የሚሆነውን ቆዳ ከአርሶ አደሩ እንደሚገዛ ከዚያም ቆዳውን ቆራርጦ የተለያዩ ባህላዊ መገልገያዎችን እንደሚሰራ፤ ሥራውም እጅግ አድካሚ እና ጊዜ የሚወስድ መሆኑንም ይናገራል። ገብረመድህን እንደሚለው ከሆነ እኚህ መሰል እቃዎች በውጪ ሃገር ጎብኚዎች ዘንድ ተወዳጅ ስለሆኑ ወደ ውጪ ሃገር ተልከው ቢሸጡ ቀላል የማይባል የውጪ ምንዛሪ ለሃገር ሊያስገኙ እንደሚችሉ ዕምነት አለው። ይህ እንዲሆን ግን መንግሥት ለጥበብ ሥራው ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት የፈጠራ ችሎታን ማዳበር እና በእጅ
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ለላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት የተሰራው የአደጋ መከላከያ መጠለያ ለቅርሱ አደጋ ሆኗል ተባለ

ለላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት የተሰራው የአደጋ መከላከያ መጠለያ ራሱ ለቅርሱ አደጋ ሆኗል በማለት የከተማዋ ነዋሪዎች በተለያየ ጊዜ ቅሬታቸውን ለመንግሥት አቅርበዋል። በጥቅምት ወር 2011 ዓ.ምም ከከተማዋ የተወጣጣ ኮሚቴ ም/ጠ/ሚ/ር ደመቀ መኮንን ድረስ በመሄድ ይህንኑ ቅሬታቸውን አሰምተዋል። BBC Amharic በወቅቱ ም/ጠቅላይ ሚንስትሩ ጥቅምት ወር ሳያልቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ ተዘጋጅቶ መጠለያውን ለማንሳትና ጥገናውን ለማከናወን የሚጠበቀውን 300 ሚሊዮን ብር እንደሚሰበሰብ ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል። በሳምንታት ልዩነት ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በስፍራው በመገኘት መንግሥት ቅርሱን እንደሚጠግን ለነዋሪዎቹ ቃል ገብተው ነበር። ይህን ተከትሎ ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ አወሮፓ ባመሩበት ወቅት ቅርሱ የሚጠገንበትን ድጋፍ ጠይቀው ከፈረንሳይ መንግሥት አዎንታዊ ምላሽ አግኝተዋል። ይሁንና የተሰራው ጊዜያዊ መጠለያ አንደኛ ምሰሶው የተተከለው የቅርሱ አለት ላይ በመሆኑ በነፋስ ሃይል በሚወዛወዝበት ጊዜ ቅርሱ እንዲሰነጠቅ እያደረገው ነው፣ ሁለተኛ መጠለያው ለአመታት የቆየ በመሆኑ ቅርሱ ዝናብና ጸሐይ ስለማያገኝ የቅርሱ ጣሪያ ወደ አፈርነት እየተቀየረ ነው፤ በአጠቃላይ ደግሞ የመጠለያው የአገልግሎት ዘመን ስላለቀ በቅርሱ ላይ ወድቆ አብያተ ክርስቲያናቱን ያወድማል የሚል ስጋት እንዳላቸው ነዋሪዎቹ በተደጋጋሚ ያነሳሉ። የላሊበላ ከተማ ከንቲባ ሙሉጌታ ወልደሚካኤል እንደሚሉት ደግሞ “መጠለያው ሲደረግ በሃላፊነት ስሜት ፣ በግልጸኝነት እና ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ የተሰራ ባለመሆኑ በዘላቂነት ቅርሶቹን መታደግ አልተቻለም”። የባህልና ቱሪዝም ሚንስትሯ ዶር ሂሩት ካሳው ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ “የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት መንግሥት አስፈላጊውን ጥገና ለማድረግ እየሰራ ነው” ብለዋል። ላሊበላ ከ900 አመት በፊት በኢትዮጵያውያን ተሰርቶ አሁን ግን የአውሮፓውያንን እርዳታ እየሻተ ነው። ከ10 አመት
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

የጠ/ሚ ዐብይ ትልቁ ስኬት ብዙ ሰው በተስፋ እንዲኖር ማድረጋቸው ነው – ዶ/ር ዮናስ አዳዬ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በአንድ አመት ውስጥ ምን አከናወኑ? BBC Amharic ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት ጥናት ሶስተኛ ዲግሪያቸውን ይማሩ በነበረበት ወቅት ዮናስ አዳዬ( ፒ ኤች ዲ) የትምህርት ክፍሉ የአካዳሚክ ዳይሬክተር ነበሩ፤ የመመረቂያ ጽሁፋቸውንም በቅርበት ተከታትለዋል፡፡ ለሶሰት ዓመታት በነበራቸው ቆይታ እያንዳንዱን ጊዜና ሰዓት በአግባቡ የመጠቀም መርህን ይከተሉ እንደነበር ያወሳሉ፡፡ “ሰዓት በማክበር አንደኛ ናቸው፤ ሁልጊዜም መጀመሪያ የሚገኙት እሳቸው ነበሩ፤ ያኔ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ነበሩ፡፡ ብዙ ጊዜ ፒ ኤች ዲ አራት ዓመት ይፈጃል፤ እርሳቸው ግን በዓለማቀፍ ደረጃ በተቀመጠው የሶስት ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ ነው ያጠናቀቁት፤ብስለታቸውን ያየሁት መጀመሪያ የጥናት መነሻ ሀሳባቸውን ሰያቀርቡ ነው፤ በእስልምናና ክርስትና ኃይማኖቶች ፍልስፍና ላይ ተመስርተው በአጋሮ አካባቢ የነበረውን ልምድ ነበር ያጠኑት፤ የመደመር ፍልስፍናን ያኔም ያንጸባርቁ ነበር ” ይላሉ፡፡ አሁን ደግሞ ዐቢይ አህመድ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣን ከመጡ ዓመት ሊደፍን የተቃረበበት ጊዜ ነው፡፡ እስካሁን ያሳለፏቸው ዓበይት ኢኮኖሚዊና ፖለቲካዊ ውሳኔዎች እያሳረፉት ባለው ተጽዕኖ ዙሪያ ዮናስ አዳዬን ጨምሮ የየዘርፉ ምሁራን ኃሳባቸውን አካፍለውናል፡፡ ፖለቲካ በሰላምና ደህንነት ተቋም ጥናት መምህርና ተመራመማሪው ዮናስ አዳዬ(ፒ ኤች ዲ) እንደሚሉት የዐብይ ትልቁ ስኬት ብዙ ሰው በተስፋ እንዲኖር ማድረጋቸው ነው፡፡ “ያለጥፋታቸው ኃሳባቸው ስለተለየ ብቻ ጥፋተኛ፣ ወንጀለኛ፣ ነውጠኛ ተብለው የታሰሩ፣ ብሎም ለማመን የሚከብድ ግፍና መከራ ሲደርስባቸው የቆዩ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከእስር እንዲፈቱ ከማድረጋቸውም በላይ ካሁን በኋላም ይህ መሰል በደል እንደማይፈጸም የሚያሳዩ ማሻሻያዎችን ለማድረግ መነሳታቸው ትልቅ
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ከአንድ ሺህ የሚበልጡ ሕገወጥ አሠሪ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ታገዱ

የአዲስ አበባ አስተዳደር የሠራተኛ እና ማሕበራዊ ጉዳዮች ቢሮ በከተማዋ የሚገኙ ከአንድ ሺህ የሚበልጡ ሕገወጥ አሠሪ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎችን አገደ። ሕጋዊ አሠራርን የተከተሉት 315 ብቻ መሆናቸውንም አስታወቀ። እንዲያም ሆኖ ከእነዚሁ ውስጥም 159ኙ በሕገወጥ ተግባር ላይ መገኘታቸውን ይህን ለማጣራት የተካሄደው የምርመራ ውጤት ማሳየቱን የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ጳውሎስ ለDW ገልፀዋል። «ከ317ቱ ሕጋዊ ኤጀንሲዎች ውስጥ 159 የሚሆኑት ከተቀጣሪዎች ገንዘብ በመቀበል በደንቡ ከተፈቀደላቸው ውጪ ሲንቀሳቀሱ፤ እንደዚሁም ደግሞ ፈቃድ ባወጡበት ቦታ ላይ ሳይገኙ በራሳቸው ጊዜ ቢሮ ቀይረው ሲሰሩ የተገኙ ናቸው። እና እነዚሁ በድምሩ 159 የሚሆኑት ላይ አስተዳደራዊ ርምጃ ተወስዷል።»ዘርፉ ከሕግ ቁጥጥር እና አሠራር ውጭ መቆየቱን አክለው የገለፁት ኃላፊዋ የችግሮቹን አይነት በማጣራት ርምጃ መወሰዱንም አመልክተዋል። ሌሎች ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው የተሳሳተ ማስታወቂያ በመለጠፍ እና ሕጋዊ በማስመሰል ይንቀሳቀሱ የነበሩ 20 የሚሆኑ ኤጀንሲዎች ላይ ደግሞ ሕጋዊ ርምጃ መወሰዱንም አስረድተዋል። አሠሪ እና ሠራተኛ እናገናኛለን የሚሉት ኤጀንዲዎች በሕጉ መሠረት ለአገልግሎታቸው ክፍያ መቀበል ያለባቸው ከቀጣሪው ሆኖ ሳለ ከተቀጣሪ የሚወስዱት ክፍያ ሕገወጥ ድርጊት መሆኑ ነው የተገለፀው። ቁጥጥር እና ክትትሉ እንደሚቀጥል በመግለፅም ኅብረተሰቡ ሕጋዊ የሆኑትን በመለየት እንዲጠቀም፤ ሕገወጦችን ደግሞ በመጠቆም እንዲተባበር መጠየቁንም ከአዲስ አበባ ሰሎሞን ሙጬ የላከልን ዘገባ ያስረዳል።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ፌዴራሊዝምና ዲሞክራሲያዊ ሽግግር በኢትዮጵያ – DW ውይይት

የኢትዮጵያን የፌዴራል ሥርዓት አንዳንዶች በኢትዮጵያውያን መካከል መቃቃር እና ግጭት እንዲስፋፋ ያደረገ «የጎሣ ፌዴራሊዝም» ሲሉ ይኮንኑታል። ሌሎች በበኩላቸው፦ ኢትዮጵያውያን ቋንቋቸውን እና ባሕላቸውን እንዲያዳብሩ እድል ፈጥሯል በማለት ያወድሱታል። ኢትዮጵያ ኅዳር 29 ቀን፣ 1987 ዓ.ም በአዋጅ በጸደቀው ሕገ-መንግሥት መሰረት ካለፉት ኹለት ዐሥርተ-ዓመታት በላይ የምትመራው ቋንቋን መሰረት ባደረገ የፌዴራል ሥርዓት ነው። ይኽን ሥርዓት አንዳንዶች በኢትዮጵያውያን መካከል መቃቃር እና ግጭት እንዲስፋፋ ያደረገ «የጎሣ ፌዴራሊዝም» ሲሉ ይኮንኑታል። ሌሎች በበኩላቸው፦ ኢትዮጵያውያን ቋንቋቸውን እና ባሕላቸውን እንዲያዳብሩ እድል ፈጥሯል በማለት ያወድሱታል። ዲሞክራሲያዊ የለውጥ ሽግግር ላይ መኾኗ የሚነገርላት ኢትዮጵያ ፖለቲከኞቿ ሁሉን የሚያግባባ ኹነኛ የፖለቲካ ሥርዓት ለመመስረት ቁርጠኝነታቸውን ሲገልጡ ይደመጣል። መንግሥትም የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ካላቸው ድርጅቶች ጋር ተቀራርቦ ለመሥራት ዝግጁ መኾኑን በተደጋጋሚ ይናገራል። በዚሁ ሳምንት እንደውም ገዢው ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶቹ ወደ አንድ ሀገራዊ ፓርቲ እንደሚቀየሩ ይፋ አድርጓል።  በሌላ በኩል የመንግሥት አካል የኾነው የኦሮሞ ዲሞክራሲ ፓርቲ በምኅጻሩ ኦዲፒ፦ «በፌዴራሊዝሙ አንደራደም» የሚል መግለጫ ሰጠ መባሉ መነጋገሪያ ኾኗል።  መግለጫው ኢትዮጵያ ጀምሬዋለሁ ባለችው ዲሞክራሲያዊ ሽግግር ሒደት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይፈጥራል የሚል ስጋታቸውን የሚገልጡም ተበራክተዋል። «ፌዴራሊዝምና ዲሞክራሲያዊ ሽግግር በኢትዮጵያ» የውይይቱ ርእስ ነው። ሙሉ ውይይቱን ለማድመጥ እታች ካለው የድምፅ ማጫወቻ ማግኘት ይቻላል።  https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/BED24380_2_dwdownload.mp3
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

በወልቃይት ጠገዴ በዳንሻ በተፈጠረ ግጭት የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ

ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በዳንሻ እየተስተዋለ ባለው ግጭት የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉ የትግራይ ክልል መንግስት ዐስታውቋል፡፡ የከተማዋ ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በተሽከርካሪዎች ላይ እየወሰዱት ያለው እርምጃ የተቃወሙ ወጣቶች ከፖሊስ ጋር ወደ ግጭት ገብተው እንደሰነበቱ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ግጭቱ በመስጋት የዳንሻ ነዋሪዎች ከተማዋ ለቀው በአቅራብያቸው ወደሚገኙ አካባቢዎች መሰደዳቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ በምዕራብ ትግራይ ዞን ፀገዴ ወረዳ የምትገኘው ዳንሻ ከተማ ካሳለፍተው ሳምንት ጀምሮ ግጭት ስታስተናግድ ሰንብታለች፡፡ የአካባቢው ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች «ሕገ ወጥ» ያልዋቸው ሞተር ብስክሌቶችና ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች መያዝ መጀመራቸው ተከትሎ በተከሰተው አለመግባባት ወደ ሁከት ገብታ የሰነበተችው ዳንሻ ከረቡዕ የካቲት 20 ጀምሮ በከተማዋ በተስተዋለ ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ ከሞቱት በተጨማሪ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዜጎች ጉዳት ደርሶባቸው በተለያዩ ሆስፒታሎች እየታከሙ መሆኑ ነዋሪዎች ነግረውናል፡፡ በፖሊስና እርምጃው በተቃወሙ ወጣቶች መካከል የተከሰተው ግጭቱ እየተባባሰ መቀጠሉ ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች ዳንሻን እየለቀቁ መሆኑ ሰምተናል፡፡ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት የሚተዳደር የነበረው በድህንነት ስጋት ምክንያት ከተማዋ ለቆ አሁን ሑመራ እንዳለ የነገረን ፀሐዬ የተባለ አስተያየት ሰጪ በግል ንብረቱ ጨምሮ በብዙዎች ሀብት ላይ ውድመት መድረሱ ለDW ተናግሯል፡፡ https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/DD54A628_2_dwdownload.mp3 እንደ ምንጮቻችን መረጃ ግጭቱ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ የከተማዋ የመንግስት መስሪያቤቶች፣ የግል ድርጅቶች፣ የፋይናንስ ተቋማትና ሌሎች አገልግሎት አቋርጠው ሰንብተዋል፡፡ ዛሬ በከተማዋ ቅኝት ማድረጉ የነገረን ተመስገን ካሳሁን የተባለ የአይን እማኝ፡ ዳንሻ ዛሬ በአንፃራዊነት ተረጋግታ ውላለች ብሏል፡፡ የተወሰነ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መመልከቱም ተናግሯል፡፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ግጭቱ ለማብረድ ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የእሳት ቃጠሎ 4ኛ ቀኑን ይዟል::

በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የእሳት ቃጠሎ ደረሰበት፡፡ በፓርኩ የተከሰተው የእሳት አደጋ 4ኛ ቀኑን ይዟል:: የአደጋው መንስኤ በውል ባይታወቅም አደጋውን አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ የአደጋው መንስኤም እየተጣራ እንደሚገኝ የፓርኩ የስራ ኃላፊዎች ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ገልፀዋል ። በፓርኩ ላይ የደረሰውን አደጋ መጠን የሚያጣራ የባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው መላኩም ተገልጿል። በአሁኑ ሰዓት የአካባቢው ፖሊስ ፣ መከላከያና ህብረተሰቡ በጋራ በመሆን ቃጠሎውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እያደረጉ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

የኦዴፓ ክንብንብ ሲወርድ

የኦዴፓ ክንብንብ ሲወርድ በMeskerem Abera ሃገራችን ኢትዮጵያ ከህወሃት አረመኔያዊ አገዛዝ ለመላቀቅ ባደረገችው የትግል ምጥ “የለማ ቡድን” የተባለ የድንገቴ ልጅ ታቀፈች፡፡ይህ ቡድን አለ ወይስ የለም የሚለው ራሱ ሲያጠራጥር ነበረ፡፡መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ ደግሞ ከህወሃት ባርነት ነፃ የመሆን አለመሆኑ ነገር ብዙ ሲያከራክር ቆየ፡፡ከህወሃት ነፃ መሆኑን ፈጣሪ ጌታውን ራሱን ህወሃትን ከስልጣን ገፍትሮ ጥሎ አሳየ፡፡በስተመጨረሻው እንደ አውሬ አድርጎት የነበረውን ህወሃትን ገፍትሮ በጣለ ቅፅበት ኦዴፓ የኢትዮጵያን ህዝብም በአደንዛዥ ፍቅር ጣለ፡፡የፍቅር ብዛት ትንታግ ተቃዋሚውን ገራም ባለሟል፣አዋቂውን አላዋቂ፣ተጠራጣሪውን አማኝ አደረገለት፡፡የወዳጅ ጠላቱ በፍቅር ሰመመን ውስጥ መውደቅ ኦዴፓ የሚሰራው ሁሉ በመላዕክት ጉባኤ የተወሰነ ቅዱስ ሃሳብ ተደርጎ እንዲወሰድ አደረገ፡፡ብዙው ሰው በፅኑ ፍቅር መመታቱን ያጤነው ኦዴፓ ከአባቱ ኦነግ፣ከጌታው ህወሃት የወረሰውን ዘረኝነቱን ፈራ ተባ ሳይል ያስኬደው ጀመር፡፡ የመጀመሪያው የኦዴፓ እውነተኛ ማንነት የተገለጠው ስልጣን በያዘ ማግስት ህግ ጠረማምሶ የአዲስ አበባ ምክርቤት አባል ያልሆነ ሰው የከተማዋ ከንቲባ አድርጎ ሲሾም ነው፡፡ ኦዴፓ የፌደራል ስልጣን ላይ ተስተካክሎ ሳይቀመጥ ገና እንዲ ያለ ህግ የመጣስ ድፍረት ያሳየው በአዲስ አበባ ላይ የነበረውን አላማ ለማስፈፀም ካለው ጉጉት አንፃር ነው፡፡ታከለ ዑማ የአዲስ አበባ ከንቲባ ተደርጎ የተሾመው ሰውየው ከኦሮሞነቱ በተጨማሪ የሰፈረበት የኦነግ መንፈስ ብርታት ስለተፈለገ ጭምር ነው እንጅ በአዲስ አበባ ካውንስል ውስጥ ኦሮሞ ፈልጎ ማግኘት አስቸግሮ አይደለም፡፡ከሁሉም በላይ ግራ አጋቢው አዲስ አበባን መምራት ያለበት ኦሮሞ ብቻ ነው የሚለው ህግ ከየት እንደመጣ ነው፡፡ የኦዴፓ ክንብንብ የወረደበት ሌላው አጋጣሚ የኦነግ ሼኔ አመራሮችን ወደ አዲስ አበባ
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

አፋር ፦ ከአብዓላ ወደ መቀሌ የሚያስኬደው መንገድ በሕዝብ ተቃውሞ ተዘጋ

አፋር አብዓላ ወደመቀሌ የሚያስኬደው መንግድ ዛሬ ተዘጋ ከ400 ያለነሱ መኪኖች መንገዱ በመዘጋቱ ቆመው ይገኛሉ። የመንገዱ መዘጋቱ መንስኤው ደግሞ በአፋር ክልል በአብዓላ ወረዳ በተለይ በከተማይቱ የሚታየው የህገወጥ የመሬት ወረራ ፣የፍትህ እጦታ የፈረጠመ የሙስና ችግር መሆኑ ይተገራል። በየቀኑ ሠው ይታሰራል ነገር ግን ወዲያ ሠው የእጅ መንሽንያ ከፈለው ከእስር ይለቀቃል። በአብዓላ የተደራጁ የወያኔ አመራሮች የአፋር የወያኔ ሚሊሺያዎች ተደራጀተው መሬት እንደቁና ቆሎ የሚቸበቸብበት ከተማ ነች። በትንሿ የወያኔ መናሃሪያ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ በመሆን ላይ ይገኛሉ። በወጣቶች ቁጥጥር ስር የገቡ የቀንጅቦች ሆቴል ንብረቶች እንዳሉም ይነገራል። ወዲያ የምታመሩ መንገደኞች መንገዱ የተዘጋ በመሆኑ ለግዜው መንገድ እስከሚከፈት ጠብቁ።ለማንኛውም የአብዓላ ወጣቶች ሠለማዊና ንብረቶችን የመጠበቅ የተለመደ ሐላፊነቶችን አደራ ተወጡ። በተለይ የቆሙ መኪኖች አደጋ እንዳይደርስባቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ አይለያችሁ።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

በለገጣፎ ለገዳዲ መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ዜጎች መንግስት ድጋፍ እያደረገልን አይደለም አሉ

በለገጣፎ ለገዳዲ መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ዜጎች መንግስት ድጋፍ እያደረገልን አይደለም ሲሉ ቅሬታቸውን ገለፁ ።
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama, Video

ጣና አሁንም ከእንቦጭ አልዳነም ተባለ ።

ጣና አሁንም ከእንቦጭ አልዳነም! (አብመድ) ጣናን ከእንቦጭ ለማዳን ከቴክኖሎጂ ይልቅ የህዝቡ ጉልበት ልዩነት ፈጥሯል፡፡ በጣና ሃይቅ ላይ የተከሰተውን የእንቦጭ አረም ለመቆጣጠር ባለፉት ሰባት ዓመታት በህዝቡና በመንግስት የተለያዩ መፍትሄዎች እየተወሰዱ ነው፡፡ አረሙ ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን ለማድረግ እየተሰራም ነው ተብሏል፡፡ የእንቦጭ አረም በባህሪው ተስፋፊ መሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ በሃይቁ ላይ እና በዙሪያው በሚገኙ የአርሶ አደሮች ማሳ ላይ እየተስፋፋ ነው፡፡ የጣና ሃይቅን ከሚያዋስኑት ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደርና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች ውስጥ በሁለቱ ዞኖች እንቦጭ ተከስቷል፡፡ በደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ በሦስት ወረዳዎች እና በማዕከላዊ ጎንደር ውስጥ ደግሞ ሦስት ወረዳዎች በሚገኙ 20 ቀበሌዎች ላይ አረሙ ተከስቷል፡፡ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ የአብክመ የአካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን እና የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር አመራሮችና ባለሙያዎች አረሙ የሚገኝበትን ደረጃ ተመልክተዋል፡፡ የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት የጋዜጠኞች ቡድንም በምልከታው ተሳትፏል፡፡ በመስክ ጉብኝቱ ተዘዋውረን ለማረጋገጥ እንደቻልነውም እንቦጭ ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን የሚደረገው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ የተለያየ የአፈፃፀም ደረጃ እንዳለው አረጋግጠናል፡፡ በ485 ሄክታር ላይ አረሙ የተከሰተበት የፎገራ ወረዳ በ468 ሄክታር ያለውን አረም በማፅዳት የተሻለ አፈፃፀም አስመዝግቧል፡፡ ‹‹ከቴክኖሎጂ አማራጮች ይልቅ የህዝቡ ጉልበት አረሙን በመቆጣጠር ልዩነት ፈጥሯል፤›› ያሉት የፎገራ ወረዳ አካባቢ ጥበቃ ጽ.ቤት ባለሙያ ወይዘሮ ደብሬ ካሳ እንቦጭ በባህሪው በፍጥነት ተዛማጅ በመሆኑ አረሙን ለመቆጣጠር በሁሉም ወረዳዎች እኩል አለመፈፀማቸው በታሰበው ልክ ውጤታማ አለማድረጉን ነግረውናል፡፡ በፎገራ ወረዳ የእንቦጭ አረም ከሃይቁ ክልል በመውጣት በግለሰቦች ማሳ
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

47 ኢትዮጵያውያን በአደንዛዥ ዕፅና ጫት ዝውውር ወንጀል በቻይና በቁጥጥር ስር ውለዋል።

47 ኢትዮጵያውያን በአደንዛዥ ዕፅና ጫት ዝውውር ወንጀል በቻይና በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው ዛሬ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያውያኑ በቁጥጥር ስር የዋሉት በህገወጥ ደላሎች አማካኝነት የነፃ ትምህርት እድል አግኝታችኋል በሚል ተታለው ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ወደ ቻይና ካቀኑ በኋላ በደላሎች የተነገራቸው ነፃ የትምህርት እድል ሀሰት መሆኑ ሲነገራቸው በሀገሪቱ የተለያዩ ግዛቶች በአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ተሳትፈው ተገኝተዋል ተብሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ወደ ቻይና በሚጓዙበት ወቅት መልዕክት አድርሱልን በሚል ምንነቱን የማያውቁትን እሽግ በመያዝ ወደ ሀገሪቱ ሲገቡ በሚደረግ ፍተሻ አደንዛዥ ዕፅ ወይም ጫት ይዘው በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል አቶ ነብያት፡፡ የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ በቻይና በሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲና ቆንፅላዎች በኩል ክትትል እየተደረገበት ነው የተባለ ሲሆን ህገወጥ ደላሎች በሁለቱም ሀገራት እንደሚገኙና ጥብቅ ክትትል በማድረግ መሰል ወንጀለኞችን ለመከላከል ኢትዮጵያና ቻይና በጋራ እየሰሩ ስለመሆኑም በመግለጫው ተነግሯል፡፡ አሁን በቁጥጥር ስር ከዋሉት ኢትዮጵያውያን ውስጥ የተወሰኑት የፍርድ ቅጣት ያገኙ ሲሆን ሌሎችም የፍርድ ሂደታቸውን እየተከታተሉ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ በአጭበርባሪዎች በመታለል ለአላስፈላጊ እንግልት ከመዳረግ በፊት የሚገኙ ነፃ የትምህርት እድሎችን ትክክለኛነት ማረጋገጥና ጉዞ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ ቃል አቀባዩ በተጨማሪም ህገ ወጥ ስደት አሁንም ተባብሶ መቀጠሉን የተናገሩ ሲሆን በሁለት ሳምንታት ብቻ 747 ኢትዮጵያውያን በህገወጥ መንገድ ወደ የመን ለመግባት ሲሞክሩ መያዛቸውን እና ወደ ስደተኛ መጠለያ ጣቢያ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህ ሳምንትም 1 ሺህ 40 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ እንዲሁም 1
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአለም ላይ ብዙ አገሮችን በማካለል በአለም አራተኛ ሆነ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአለም ላይ ብዙ አገሮችን በማካለል/መዳረሻዎችን በማረግ በአለም አራተኛ ሆኗል። ከላይ የተቀመጡት የቱርክ፣ የፈረንሳይ እና የእንግሊዝ አየር መንገዶች ሲሆኑ እነ ኤምሬትስ፣ የኳታር አየር መንገድ፣ የጀርመኑ ሉፍታንዛ፣ የካናዳ አየር መንገድ እና የሩስያው ኤሮፍሎትን ግን ለመቅደም ችሏል። Via Amb. Henok Teferra Shawl
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

አማጋ የስፖንጅ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 23 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደረሰ

(ኤፍ.ቢ.ሲ) በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አማጋ የስፖንጅ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 23 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደረሰ፡፡ Image may contain: one or more people, cloud, sky and outdoorበእሳት አደጋው ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካካል ስምንቱ የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን ሰራተኞች ናቸው። 15ቱ ደግሞ የፋብሪካው ሰራተኞች መሆናቸውን የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባላስልጣን የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል፡፡ አደጋው የደረሰው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍል ከተማ ወረዳ አምስት የኢንዱስተሪ ዞን አማጋ የስፖንጅ ፋብሪካ ላይ መሆኑን አቶ ንጋቱ ገልጸዋል፡፡ በአደጋው አብዛኛው ፍብሪካው ክፍል መውደሙን የገለጹት የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ ፋብሪካው የሚጠቀማቸው ግብዓቶች ተጠቀጣጣይ መሆናቸው አደጋውን አባብሰውታል ብለዋል፡፡ አደጋው 4 ሰዓት ተኩል ላይ የተከሰተ ሲሆን÷ 11 ተሽክርካሪዎችን፣ ሁለት አምቡላንሶችን፣ 85 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችን ያሰማራው ባለስልጣኑ በ4 ሰዓታት ውስጥ እሳቱን ለመቆጣጠር ችሏል፡፡ 98 ሺህ ሊትር ውሃ፣ 25 ሺ ሊትር ኬሚካል እሳቱን ለማጥፋትና ለመቆጣጠር አግልግሎት ላይ ውሏል፡፡
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ፣ ኅብረ ብሔራዊቷ ኢትዮጵያና የዓድዋ ድል ምስጢር

ያኮረፈ ሁሉ ‹‹ይቅር ይበሉኝ ጃንሆይ›› እያለ እሳቸውም ‹‹ምሬሃለሁ›› እያሉ …፡፡ Image may contain: one or more people, outdoor and textመላው አፍሪካውያን በባርነት ረግረግ በሚዳክሩበት በዚያ ወቅት፤ የአፍሪካውያን አባቶች በልጆቻቸው ፊት ክብራቸው እንዳደፈ ሸማ በነተበበት በዚያ ዘመን፤ ሀገር በጭቆና ማቅ የጣር ድምፆች በረክተውባት ነበር፡፡ ጀርባዋ ሲናጥ፣ ወኔዋ ሲኮሰምን፣ ቅስሟ ሲሰበር፣ የተጎሰመው ነጋሪት፣ የተነፋው ጡሩንባ፣ የተነገረው ዓዋጅ፣ በዓለም ታሪክ የፋሺስቶች ድንበር የለሽ የትዕቢት ዘረኝነት ቅኝ ግዛት የማያንበረክካት የጥቁር ሕዝቦች ቀንዲል ሀገር እንድትፈጠር ምክንያት ሁኗል፡፡ በዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት የተፈጠረችው ኅብረ ብሔራዊቷ ኢትዮጵያ እና የዓድዋ ድል ምስጢር ምንድን ነው? በየአከባቢው ዓፄ ምኒልክ ላይ አኩርፈው ፊናቸውን ይዘው በዱር በገደሉ የነበሩ መኳንንት የክተት ዓዋጅ በመላው ሀገሬቱ ከተነገረ ወዲህ ‹‹ሀገሬ ካንቺ በፊት እኔ›› ብለው በአንድነት ያለምንም ልዩነት ዘምተው ድል ያደረጉ አባቶች መነሻ ምንድን ነው? ለእነዚህ ሁሉ መነሻው ‹‹የሠመረው የክተት ዓዋጅ እና በሀገር ፍቅር የነደዱ፤ ሕይወታቸውን ያለስስት የገበሩ ጀግኖችን ያነሳሳው የክተት አዋጅ ነው›› ብለውናል የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህሩ ዶክተር አየነው ማሞ፡፡ ታሪካዊው የክተት አዋጅ፡- “እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ፤ እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ፡፡ ከእንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉም ነውና ስለእኔ ሞት አላዝንም፡፡ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም፤ ወደፊትም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም አገር የሚያጠፋ፤ ሃይማኖትን የሚለውጥ፣ በፊት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባሕር አልፎ መጥቷል፡፡ እኔም የአገሬን ከብት ማለቅ፤ የሰውን መድከም ዓይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር፡፡ አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

በኢትዮጵያ የተለያዩ አስተሳሰቦችን የሚያንፀባርቁ መገናኛ ብዙሃን እንዲስፋፉ የሚያደርግ የሚዲያ ፖሊሲ ያስፈልጋታል ተባለ፡፡

በኢትዮጵያ የተለያዩ አስተሳሰቦችን የሚያንፀባርቁ መገናኛ ብዙሃን እንዲስፋፉ የሚያደርግ የሚዲያ ፖሊሲ ያስፈልጋታል ተባለ፡፡ “በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ሥርዓት ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ሚና” በሚል ርዕስ በሂልተን ሆቴል የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ በውይይቱ ላይ የመነሻ ሀሳብ ያቀረቡት የፎርቹን ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ ታምራት ገብረጊዮርጊስ እንዳሉት በአገራችን መብዛት ያለባቸው በራሳቸው ገቢ ማመንጨት የሚችሉና የተለያዩ አስተሳሰቦችን የሚያንፀባርቁ መገናኛ ብዙሃን ናቸው፡፡ መገናኛ ብዙሃኑ ለሙያ ሥነ-ምግባራቸው ታማኝ መሆን እንዳለባቸውም ተናግረዋል፡፡ አቶ ታምራት እንዳሉት በአሁኑ ወቅት ሁለት ፅንፍ የያዙ መገናኛ ብዙሃን አሉ፡፡ መገናኛ ብዙሃን የሚወክሉት የህብረተሰብ ክፍል ስላለ ወደፊትም መቀጠላቸው አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ ይህ ግን አጠቃላይ የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በሁለት ፅንፍ ተከፍለው ሊቆሙ ይገባል ማለት እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጓት መገናኛ ብዙሃን አንድ አቋም ሳይሆን የተለያዩ አስተሳሰቦችን የሚያንፀባርቁ ሊሆኑ ይገባል ሲሉም አክለዋል፡፡ የሚዲያ ፖሊሲ ሲቀረፅም እንዲህ ዓይነት መገናኛ ብዙሃን እንዲስፋፉ የሚያደርግ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡ መንግስታዊ ባልሆነው የጀርመኑ ፍሬድሪክ ኤበርት እስቲፍቱንግ አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው በዚሁ መድረክ ላይ ሌሎች የመወያያ ሀሳቦችም እየቀረቡ ነው፡፡ Sheger FM
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama

ቀይ ቀበሮ መገኛ የሆነችው በባሌ ጎባ ሳነቴ ተራራ ላይ የሚገኘው ደን እየተቃጠለ ነው

Image may contain: fire and sky የብርቅየ ቀይ ቀበሮ መገኛ የሆነችው በባሌ ጎባ ሳነቴ ተራራ ላይ የሚገኘው ደን ከትላንት ጠዋት ጀምሮ እየተቃጠለ ነው ሰደድ እሳቱ አሁንም ቢሆን እየተቃጠለ ነው ሲሉ ምንጮች ገለፁ:: ቦታው በጣም ቀዝቃዛ ስለሆነ ቃጠሎ በራሱ አይነሳም ምናልባት የሰው እጅ ሳይኖርበት እንዳልቀረም ምንጮቻችን አክለው ጠቅሰዋል :: ለከተማው ቅርብ ስለሆነ አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ ጎባ ከተማ መድረሱ አይቀርም ሲሉም ነዋሪዎች ስጋታቸውን ተናግርዋል ::   Image may contain: one or more people, people standing, sky, cloud, outdoor and nature Image may contain: nature and outdoor  
Posted in Amharic News, Ethiopian Drama
Follow us on Facebook
Follow us on Facebook