በአማራ ክልል ያሉ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም የድጋፍ ጥያቄ ተጠየቀ

በአማራ ክልል ያሉ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም የድጋፍ ጥያቄ ተጠየቀ:: የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ ቤት ያወጣው ደብዳቤ እንደገለጸው በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም የምናደርገውን ጥረት ስለምትደግፉን እጅግ እናመሰግናለን፡፡ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና የሕዝብ ወዳጆች ድጋፍ ለማድረግ እንዲያስችላችሁ ከዚህ ቀደም ካስተዋወቅነው የባንክ አካውንት በተጨማሪ ሌሎች አካውንቶችንም ፈጥረናል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉት የባንክ አካውንቶች በደብዳቤ ጭምር ያረጋገጥናቸውና እውነተኛ እንዲሁም የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የሚያስተባብራቸው ስለሆነ ድጋፍ ስታደርጉ እነኝህን አካውንቶች ብቻ እንድትጠቀሙ እናሳስባለን፡፡ ተባብረን ተፈናቃዮችን እናቋቁም፡፡ ብሏል

Image may contain: text

በዚህም መሰረት የባንክ አካውንቶች፡-
1. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህር ዳር ቅርንጫፍ የሚገኘው አብክመ አደጋ መከላልና ዝግጁነት ፈንድ /ABKM ADEGA MEKELAKeLNA ZIGJUNET FUND “F” Account NO 1000258250811
2. በዓባይ ባንክ የሚገኘው አብክመ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ፈንድ / ANRS DISASTER PREVENTION AND READINESS FUND / Account NO 2562112504158017
3. በአቢሲኒያ ባንክ የሚገኘው አብክመ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ፈንድ / ANRS DISASTER PREVENTION AND PREPAREDNESS FUND /Account NO 16241137 መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ብሏል


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE