የኢትዮጵያ ጅቡቲን አውራ ጎዳና መንገድ መዘጋት

በአፋር ክልል ገዋኔ ወረዳ ትናንት ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ለ 8 ወራት ደመወዝ አልተከፈለንም ያሉና የመንግስት ሰራተኞች የመጠጥ ውኃ በአግባቡ እየቀረበ አይደለም የሚሉ የወረዳው ነዋሪዎች የኢትዮጵያ ጅቡቲን አውራ ጎዳና መንገድ ለሰዓታትበመዝጋት ተቃውሟቸውን ማሰማታቸው ተነገረ፡፡  ለተቃውሞወደ አደባባይ የወጡ የገዋኔ ነዋሪዎች እንደገለፁት በወረዳውየሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች በተገቢው መንገድ ደመወዝ እየደረሰን አይደለም ይላሉ፡፡  ‹‹ደመወዝ ከነጭማሪው ወደ 8 ወራት አልተከፈለንም፡፡ በ2017 ዓ.ም ግማሽ አለ፡፡ ከ2018 ዓ.ም ያልተከፈለ የደመወዝ ጉዳዩን ማን ይስማ፡፡››  ተጨማሪ https://www.dw.com/am/