የትናንት ታሪክ በውሸት ብዛት ሊፋቅ አይችልም ( የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር )

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረመስቀል፣ የኢትዮጵያው ብልጽግና ፓርቲ “አንቂዎች” እና “ተንታኞች”፣ የኤርትራ የነጻነት ትግል በውጭ ኃይሎች “ቀስቃሽነት” እና “ድጋፍ ሠጪነት” የተካሄደ እንደኾነ በመግለጽ ላይ ይገኛሉ በማለት ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሠፈሩት መልዕክት ከሠዋል። “የትናንት ታሪክ በውሸት ብዛት ሊፋቅ አይችልም” ያሉት የማነ፣ ኤርትራ በልጆቿ መስዕዋትነት ነጻነቷን ያገኘችው በየተራ በአሜሪካ እና በሶቪዬት ኅብረት ይደገፍ ከነበረ መንግሥት ጋር ተዋግታ ነው ብለዋል። ሌላው ቢቀር፣ በኤርትራ ላይ አስከፊ ግፍ የፈጸሙ ኃይሎች “ለታሪካዊ ወንጀሎቻቸው ይቅርታ መጠየቅ እንጂ በኤርትራ ቁስል ላይ ጨው መነስነስ አልነበረባቸውም” በማለት የማነ ወቅሰዋል።