ብልፅግናዎች በጦርነት አላልቅ ያላቸውን ሕዝብ በፕሮፓጋንዳቸው እየቀለዱበት ነው ………… የአብይ ሚኒስትር የሆነችው ፍፁም የተባለች ፈጣሪን የማትፈራ ሴት በኢኮኖሚ በደቀቀው በድህነት በተዘፈቀው የኢኮኖሚ ሉዓላዊነቱ ለምዕራባውያን የፋይናንስ ተቋማት የተሸጠበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በሃሰት የቁጥር ቁልል እያሾፈችበት ይገኛል። … በጦርነት ሰብሉ እየወደ ያለው ገበሬ ምርቱ 400 ፐርሰንት አደገ ብለው በንቀት እየተሳለቁ ነው …. ከትምህርት ቤት ምገባ ጀምሮ በርካታ ሥራዎች አሉን ብለው ያሾፋሉ፤ ዜጎች ሰርተው ቤተሰባቸውን የሚመግቡበት የስራ ፖሊሲ ከመቅረጽ ይልቅ የድህነት አካል የሆነው የምገባ ፕሮግራም እያካሄዱ ይኮፈሱብናል። የእድገት ፖሊስን ቀርፆ በተግባር ላይ ማዋል እንጂ ተማሪን መመገብ የድህነት ቅነሳ አይደለም። …… ሴትየዋ ፈጣሪን ሳትፈራ የአቅመ ደካማ ቤቶች የማደስ እንዲሁም የገጠር እና የከተማ ኮሪደር ፕሮጀክቶች ያስገኟቸው ትሩፋቶች የዜጎችን ሕይወት ከማሻሻል አኳያ ትልቅ ሚና አላቸው ትላለች። በጣት የሚቆተሩ ቤቶችን ለፎቶ ፖለቲካና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ አድሶ ራስን ከፍ ማድረግ አሳፋሪ ነው፤ የኮሪደር ልማቱም ቢሆን በመቶ ሺዎችን ከቤታቸውና ከንግዳቸው አፈናቅሎ ተመጽዋች እና ስራፈት ደሃ አድርጓቸዋል። …. የኮሪደር ልማቱ የቆመው እኮ በእነ አሜሪካ ጫና እንደሆነ በደንብ ይታወቃል፤ የምዕራባውያን ኤምባሲዎች የተጫወቱት ሚና ተፈናቃይና ተመፅዋች እንዲቆም አድርጎታል ….. ውሸት ሲደራረብ እውነት ይሆንልናል የሚሉት የብልጽግና ሰዎች …. የአለም ባንክ የኢትዮጵያ የድህነት መጠን ወደ 43 ከመቶ ከፍ ይላል የአመታት ለውጥን ወደኃላ ይቀለብሳል ብሎ የተናገረበት መግለጫ አድምጠን ሳንጨርስ ….. ኢትዮጵያ የከፋ የብድር አዘቅት ውስጥ ትገኛለች የሚለውን መረጃ አንብበን ሳናጠናቅቅ …… የተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ኢትዮጵያ ደካማ ኢኮኖሚ ያላት አገር ሕዝቡም በድህነት ተዘፍቋል ብለው የጻፉበት ብዕር ሳይደርቅ እነ አብይ አሕመድ በውሸት የተሞላ ፕሮፓጋንዳቸውን እየረጩ ይገኛል። …… አለም የሚያውቃት ኢትዮጵያ/ሕዝቡ የሚኖርባት ኢትዮጵያ እና የአብይ ፕሮፓጋንዲስቶች የሚስሏት ኢትዮጵያ ሃራምባና ቆቦ ናቸው። ….. ሕዝብ እስከመቼ እየተናቀ ይቀጥላል ? ሕዝብ ራሱን ማስከበር ይጠበቅበታል ! ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ……. (ምንሊክ ሳልሳዊ)