ኤምሬቶች በሱዳን ጦርነት የሚያሳትፏቸውን የኮሎምቢያ ተዋጊዎች በቦሳሶ አስገብተው በኢትዮጵያ እንደሚያሻግሩ ታወቀ

በሱዳን ጦርነት ለሚዋጉ የኮሎምቢያ ተዋጊዎች የቦሳሶ ወደብ መሸጋገሪያ መሆኑ ተነገረ።

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የምታስተዳድረው በቦሳሶ የሚገኝ ወታደራዊ ማዘዣ ለተዋጊዎቹ መሸጋገሪያ መሆኑ ተገልጿል።

የቀድሞ የኮሎምቢያ ጦር አባላት ለግለሰባዊ ደህንነት ከተመለመሉ በኋላ ለሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል እንዲዋጉ ይደረጋሉ ተብሏል።

አንድ የኮሎምቢያ ተዋጊ 2600 ዶላር በወር የሚያስገኝለትን ኮንትራት መፈረሙን ገልፆ በኢትዮጵያ በኩል አድርጎ ወደ ፑንትላንድ ቦሳሶ ወደብ መወሰዱን በኋላም በዳርፉር መስፈሩን ገልጿል።

የቦሳሶ ወደብ መጀመሪያ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ሲሰራ የፑንትላንድ የባህር ኃይልን ለማሰልጠን ነበር ሲባል አሁን ሙሉ ለሙሉ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የምትቆጣጠረው ማዘዣ ነው ተብሏል።

ምንም እንኳን የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሱዳን ጦርነት ያላትን ተሳተፎ ብትክድም ከሰሞኑ የቦሳሶ ወደብ እንዴት የኮሎምቢያ ተዋጊዎች መሸጋገሪያ እንደሆነና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እየተጠቀመች እንደሆነ የሚያሳይ የምርመራ ዘገባ ወጥቷል።

ዘ ጋርዲያንና La Silla Vacia የተሰኘ የኮሎምቢያ ጋዜጣ በጉዳዩ ላይ የሰሩትን የምርመራ ሪፖርት ከዚህ ማንበብ (  https://www.theguardian.com/world/2025/oct/08/colombian-mercenaries-sudan-war  ) ይችላሉ።