እኩልነትን ስንጠይቃቸው መጨፍለቁንና የበላይ መሆኑን መረጡ #ግርማካሳ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አንዳንዶች የኦሮሞ ፖለቲከኞች ላይ ታከራለህ ይሉኛል። ማክረር የሚለው ቃል ትንሽ ጠንከር ያለ ቃል ቢሆንም ፖለቲካቸውንና አመለካከታቸውን ግን ጠንከር ባለ መልኩ ቻሌንጅ ማድረግ ብቻ ሳይሆን አደገኛ እንደሆነ ጽፊያለሁ። ለዚያም ምክንያት አለኝ።

ከሶስት አመታት በፊት የኦሮሞ ተቃዉሞ (#Oromo Protest)  በሚል ብዙ ተቃወሞ በተወስኑ የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች በስፋት ይደረግ ነበር። በወለጋ፣ በሃረርጌ፣ በምእራብ ሸዋና በምእራብ አርሲ ዞን በዋናነት። ብዙ ወገኖች በአጋዚ ጦር ተገድለዋል። ብዙ ደም ፈሷል። በዚያን ወቅት፣ ኦሮሞው ለብቻው የኦሮሞ ጥያቄ ብቻ ይዞ፣ ሌላውን ማህበረሰባት ባገለለ መልኩ የሚያደርገው ትግል ዉጤት ሊያመጣለት ስላልቻለ፣  እንደውም የማህበርሰቡን ስቃይና ሰቆቃ ስላበዛው፣ የኦሮሞ ተቃወሞ(#Oromo Protest) ወደ ኢትዮጵያ ተቃዉሞ (#Ethiopia Protest) ለማዞር አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን ጀመርኩ። በጸረ-ሕወሃት አቋም ብቻ አብሮ መታገል በቂ ስላልሆነ፣ ከሕወሃት  በኋላ ቢያንስ በጊዜያዊነት ስለሚሆነው  የጋራ አጀንዳዎች ማስቀመጡ አስፈላጊ ነው በሚል፣  ስድስት ነጥቦችን ያካተተ፣  የኦሮሞ ታጋዮች ከሌላው ጋር ሊያቀራረብ የሚችል አጭር ሰነድ አዘጋጅቼ የኦሮሞ አክቲቪስት ለሚባሉት እንዲደርሳቸው አደረኩ።

ያቀረብኳቸው ስድስት ነጥቦች አራቱ ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል፣ የኦሮሞ አክቲቪስቶች የሚፈለጉትና የሚጠይቁት ነው። እነርሱ ከሌላው ጋር አብረው እንዲሰሩ በጣም ከነበረኝ ፍላጎት የተነሳ ርቄ በመሄድ ነበር ወደነርሱ የቀረብኩ። የነርሱን ድጋፍ ካገኘው ወደ ሌሎች ማህበረሰባትና አክቲቪስቶች ለመሂድ ነበር ያሰብኩት። ምን አልባትም ይሄን በመጻፊ እንዴት እንዲህ ትላለህ ብለው ብዙ ወገኖች ሊናደዱብኝ እንደሚችሉ አስብያለሁ። ግን “ግድ የለም፣ የኦሮሞ አክቲቪስቶች ከተስማሙ ፣ ሌሎች ቢናደዱብኝም፣  ደፍሬ፣ ተጋፍጬ እከራከራለሁ፣ አሳምናለሁ” ብዩ በመወሰን ነበር የተነሳሁት።

ሆኖም ግን የኦሮሞ አክቲቪስቶች አራቱን ተቀብለው ሁለቱን መቀበል አልፈለጉም። የሚከተለውን ነበር በውስጥ መስመር እንዲደርሳቸው አድርጌ የነበረው። ከሶስት አመታት በፊት።

=============================

መከራከር፣ መለያየት ቀላል ነው። ያሉ ልዩነቶችን ማስፋት ቀላል ነው። መፍትሄዎችን ግን ማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው። የኢትዮጵያ ችግር የሚፈታው ችግሮች በመዘርዘርና በማስፋት ሳይሆን ሁሉም አሸናፊ ሊሆኑበት የሚያደርግን የመፍትሄ ሐሳቦች በማቅረብ ነው።

የተለያዩ ወገኖችን በመፍትሄ ሀሳብ ዙሪያ ለማቀራረብ የሚከተሉትን ስድስት ነጥቦች አስቀምጫለሁ።

1. በፌዴራል አወቃቀር ዙሪያ የተለያዩ ልዩነቶችና አለመስማማቶች አሉ። ሆኖም ወደፊት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ተገንብቶ፣ ፓርቲዎች ያሏቸውን አቋም በግልጽና ያለፍርሃት ለሕዝብ አስተዋዉቀው፣ ሕዝብ ከፈለገ አሁን ያለው የአስተዳደር መዋቅሩእንዲቀጥል ማድረግም ሆነ መቀየር መብቱ እንደሆነ በማረጋገጥ፣ በጊዜያዊነት ግን አሁን ያለችው የኦሮሚያ ክልል እንዳለች እንድትቀጠል ቢደረግና፣  ለአስተዳደር አመችነት እንዲኖር ለዞኖች የበለጠ ስልጣን ቢሰጥ፣

2. አዲስ አበባ ለብቻዋ የፌዴራል መስተዳደር መሆኗ ቀርቶ፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉትን አካባቢዎች በማካተት ወይንም ከምስራቅ ሸዋ ወይንም ሰሜን ሸዋ ዞን ጋር በመቀላቀል፣ የራሷ ዞን ሆና፣ ሙሉ በሙሉ በኦሮሚያ ክልል ሥር ተደርጋ፣ በአዲስ አበባ በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለው ማህበረሰብ እንድ የተገነባዉ ግንብ ቢፈርስ፣

4. አቅም በፈቀደ መልኩ፣ በሕዝብ ይሁንታ፣  ኦሮምኛ፣ ትግሬኛ፣ ሶማሌኛ ከአማርኛ ጋር የፌዴራል የስራ ቋንቋ እንዲሆኑ  ቢደረግ

5. በኦሮሚያ (አዲስ አበባን ጨምሮ) አማርኛ፣ እንግሊዘኛ እንዲሁም አፋን ኦሮሞ፣   እንደ ደቡብ፣ ሶማሌ፣ አፋር በመሳሰሉ ክልሎች ኦሮምኛ ትምህርት ባይሰጥም ከእንግሊዘኛ እና ከአማርኛ በተጨማሪ ሌላ ሶስተኛ የኢትዮጵያ ቋንቋ ፣  በአማራው ክልል ከዘጠና በላይ በሚሆኑት አካባቢዎች (በጎጃም፣ በአብዛኛው ወሎ፣ በሸዋ) አፋን ኦሮሞ፣ በሰሜን ጎንደር እና ሰሜን ወሎ ትግሪኛ  በሁሉም ትምህርት ቤቶች ቢሰጡ፤

6. ማንም ኢትዮጵያዊ በማንኛውም የአገሪቷ ክፍል የመኖር፣ የመነገድ፣ ኢንቨስት የማድረግ፣ የመምረጥ፣ የመመረጥ ሙሉ መብት እንዲኖረው፣  ማንም ኢትዮጵያዊ በሃይማኖቱ፣ በጾታው፣ በብሄር ብሄረሰብ ማንነቱ አድሎና ልዩነት ሳይደረግበት፣ በተለይም በኦሮሚያ ኦሮሞ ይሁኑ አይሆኑ ሁሉም የክልሉ ነዋሪዎች እስከሆኑ ድረስ እኩል እንዲታዩ፣ እኩል ጥቅም እንዲያገኙ ቢደረግ፣

በሚሉ ነጥቦች ላይ መግባባት መፍጠር ከቻልን ትግሉን አንድ ምእራፍ በትብብር ወደፊት ማሻገር እንችላለን።

=====================

የኦሮሞ አክቲቪስቶች ከላይ ከተቀመጡት ስድስት ነጥቦች  ሁለቱን መቀበል አልፈለጉም። አማርኝ በጭራሽ በኦሮሞ ክልል የስራ ቋንቋ መሆን የለበትም የሚል አቋም ያዙ። ሲከራከሩም “አማራ ክልል ኦሮሞኛ የስራ ቋንቋ ለምን አልሆነም ?”  ይላሉ። አማራ ክልል ከከሚሴ ውጭ፣ ኦሮምኛ ተናጋሪው ከ2% አይበልጣም። እንደዚያም ሆኖ የአማራ ክልል መንግስት በከሚሴ ላሉ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ራሳቸውን በራሳቸው በኦሮምኛ እንዲያስተዳደሩ ፈቅዷል። በኦሮሞ ክልል በአዳማ ልዩ 75%፣ በጂማ ልዩ 65%፣ በቡራዩ ልዩ 55%፣ በምስራቅ ሸዋ 33% ፣ በአርሲ 20% ….ኦሮምኛ ተናጋሪ ሳይሆኑም፣  ያን ያህል ኦሮምኛ የማይናገር ማህበረሰብ እያም፣  “አማርኛ ከመጣ ሞተን እንገኛለን”  ማለት አሳዝኞኛል።

ሌላው በኦሮሞ ክልል የሚኖሩ ዜጎች እኩል ይሁኑ መባሉም አልተመቻቸውም። የክልሉ ባለቤት ኦሮሞው ነው፣ ግን ኦሮሞ እንግዳ ተቀባይ ነውና ሌሎች መኖር ይችላሉ የሚል አቋም ነው ያላችው።

እንግዲህ አስቡት ስድስት ነጥብ አስቀምጬ፣ እነርሱ የሚፈለጉትን ዋና ዋናዎቹን እካትቼ፣ የመብት ጉዳይ ነዉና የሌሎች ማህበረሰባትን ጥያቄ የሚያስተናገዱ፣ በምንም መልኩ የኦሮሞው ጥቅምና መብት የማያሳንሱ፣ ሁለት ቀላል ጥያቄዎች ማስተናገድ አልፈለጉም። የነርሱን ብቻ የሌላው መመልከትን አማየት አልቻሉም።

ያን ጊዜ አንድ ነገር ተረዳሁ። የኦሮሞ ብሄረተኝነት ፖለቲካ በፍቅር ፣ በመከባበርና በእኩልነት ላይ የተመረኮዘ  ሳይሆን ፣ በመጨፍለቅና በመስፋፋት ላይ የተመረኮዘ እንቅስቃሴ መሆኑን ። ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለመስማማት በሚል ከነበረን አቋም በጣም ርቀን ወደነርሱ ብንመጣም እነርሱ ግን መቶ በመቶ የፈለጉት ካላገኙ የሚረኩ አለመሆናቸውም። ሙሉ ለሙሉ surrender አድርገን ፣ የነርሱን የበላይነት ተቀብለን እንድንኖር የሚፈለጉት እንጂ ለእኩልነትና ለፍት በፍጹም የቆሙ አለመሆናቸውን።  እነርሱ በሚቆጣጠሩት አካባቢዎች መጤ ፣ ሰፋሪ እያሉ ዜጎችን በግፍና በጭካኔ የሚያፈናቅሉትም ከዚህ ዘረኛ ፖለቲካቸው የተነሳ ነው። ሸገር የኛ ነው፣ ድሬዳው የኛ ነው፣ ⶁይሌ የኛ ነው፣ ሃረር የኛ ነው .. እያሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለነርሱ ሌላ ዜጋ ያለ አይመስላቸውም።

የኦሮሞ ብሄረተኝነት በእኩልነት ላይ ቢመሰረት ኖሮ  ችግር አልነበረም። ኦሮሞዉን በመጥቀም ላይ ቢመሰረት ኖሮ ችግር አልነበረዉም። አፋን ኦሮሞ በማሳደግና በማስፋፋት ላይ ቢመሰረት ኖሮ ችግር አልነበረም።  ግን ሌላውን በማጥፋት፣ በማጥቃት፣ በማፈናቀል፣ የሌላዉን መብት በመርገጥ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ በጣም አደገኛና የአገር ጠንቅ ነው ወደሚል አቋም እንድሄድ አድርጎኛል።

የኦሮሞ ብሄረተኞች አንደኛ የኦሮሞ ክልል ከሚሉት ከኦሮሞነት በቀር ምንም ነገር እንዳይኖር ለማድረግ ትልቅ ዘመቻ ጀምረዋል። ኦሮሞ ያልሆኑን ከኦሮሞ ክልል በግፍና በጭክኔ የሚፈናቀሉት ፣ የዘር ማጽዳት ወንጀሎችን የሚደረጉት፣ ከዚህ የተነሳ ነው። በለገጣፎ ዜጎች ከአማራ ክልልና ከደቡብ ክልል የምጣችሁ ናችሁ ፣ ኦሮሞ አይደላችሁም ተብለው ነው ቤታቸው እየፈረሰ ከⷃቸው እንዲነሱ የተደረገው።  ሁለተኛ ኦሮሞ ክልል ውስጥ የሌሉ ግን እነርሱ የኦሮሞ ናቸው ያላቸውን ቦታዎች ለመቆጣጠርና በነዚያ ቦታዎች ለመስፋፋት፣ የኦሮሞ ግዛት የሚሉትን ለማተለቅ (ልክ ሶኢያድ ባሬና ሂትለር ሲያደረግ እንደነበረው)  በሁሉም አቅጣጫ እኩይ ተግባራት ጀምረዋል። በሃረር ከሃረሬዎች ጋር፣ በባሌ፣ በቦረና፣ በሃረርጌ  ከሶማሌዎች ጋር፣ በድረዳዋ ከሶማሌና ሌሎች ማህበረሰባት ጋር፣ በአዲስ አበባ ከአዲስ አበቤ ጋር፣ በሸዋ ከጉራጌ፣ ከንባታ፣ አማራዎች ጋር፣ በቤኒሻንጉል ከጉሙዞች ጋር፣ በጉጂ ከጌደኦዎች፣ ከቡርጂዎች ጋር ፣ ምን አልባት በድንበር ከማያዋስናቸው ከትግራይ በሥተቀር፣ ከሁሉን ጋር ግጭት ጋር ግጭቱን ገብተዋል። የኦሮሞ የበላይነት ለማስፈን ስለሚሰሩ ብቻ !!!!!!!!! ከኦሮሞነት ውጭ ሌላ ነገር ምንም ስለማይታያቸው።

ለዚህ ነው እነዚህ  ጽንፈኛ ሃይላት ሊያምጡት የሚችለውን ትልቅ ጉዳት  ስልተረዳው ሕዝብ አላማቸውንና አጀንዳቸውን ከወዲሁ አውቆ አስፈላጌውን ዝግጅትና ጥንቃቄ  እንዲያደርግ ግፊት እያደረኩ ያለሁት። እነዚህ ቡድኖች አገርንና ሕዝቡን፣ ራሱ የኦሮሞ ማህበረሰብ ጨምሮ ሊጠቅሙ ሳይሆን፣ አገርን ወደ ከፋ ዉድቀት ለመዳረግ የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ህዝብ እንድ ሲያድ ባሬ፣ እንደ ግራዚያኒ ሊመለከታቸው ይገባል ባይ ነኝ። እነዚህ ቡድኖች  የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላትበሆኑት፣ እንደ ግብጽ ባሉ፣ ከበስተጀርባ  ከፍተኛ ሰዉር ደጋፍ የሚያገኙ እንደሆነም ብዙዎች ይናግራሉ።