የመካከለኛውን ዘመን የሰው ልጅ አመጣጥ የሚያሳይ አዲስ ግኝት ይፋ ሆነ

ኢትዮጵያ ሉሲ ወይም ድንቅነሽን ጨምሮ በርካታ ቅሪተ አካላትና በዓለም ረጅም ዕድሜ ያስቆጠሩ የድንጋይ መሣሪያዎች መገኛ በመሆን፤በጥንታዊ የሰው ልጅ አመጣጥ ላይ በሚደረገው ምርምር ጉልህ ስፍራ አላት።በቅርቡ የወጣ አንድ የጥናት ግኝት ደግሞ የሰዉ ዘር መገኛ ብቻ ሳትሆን በመካከለኛው ዘመን የሰው ልጅ አመጣጥ ምርምርም ቀዳሚ መሆኗን የሚያሳይ ነው።…