በጎጃም ጎንቻ ሲሶ እነሴ እና በወሎ መካነ ሰላም የገዳዩ ቡድን በፋኖ ሃይል ተደመሰሰ

(ኢትዮ 360- የካቲት 2/2016) በጎጃም ጎንቻ ሲሶ እነሴ ከ14 በላ ይየሚሆን የገዳዩ ቡድን ተደምስሶ 21ዱ ሲቆስል በወሎ መካነ ሰላም ደግሞ በፋኖ ሃይል ከ19 በላይ የሰው በላው ሃይል ተደምስሶ ወደ 60 የሚሆነው ደግሞ መቁሰሉን የፋኖ ሃይል አባላቱ ለኢትዮ 360 አስታወቁ።
በወረዳው ግንደወይን ከተማ በተደረገው በዚህ ውጊያ ከ14 በላይ የሚሆነው የገዳይ ቡድን ሲደመሰስ ከ21 በላይ የሚሆነው ደግሞ ቁስለኛ ሆንዋል ብለዋል።
በግንደወይን ደግሞ የሳሙኤል አወቀ መታሰቢያ ብርጌድ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ውስጥ የሚገኘውን የሰው በላው ሃይል ካምፕ አፈራርሶታል ብለዋል።
በተመሳሳይ በደንበጫ ዋድ ከተማ መሽጎ በነበረው የሰው በላው ሃይል ላይ የአካባቢው ፋኖ ተከታታይ የቦምብ ጥቃቶችን በማድረግ ምሽጉን ፍርስርሱን ማውጣቱን ተናግረዋል።
ምሽጉ የፈራረሰበት ገዳይ ቡድንም አመሻሹን ዋድ ከተማን ለቆ ወደ ደንበጫ ከተማ መፈርጠጡን ተናግረዋል።
ገዳይ ቡድኑ አካባቢውን ጥሎ መፈርጠጡን ተከትሎ የዋድ ኗሪ ወደ ቀየው መመለስ ጀምሯል ብለዋል።
ገዳዩ ቡድን ወደ አካባቢው መግባቱን ተከትሎ ነዋሪው ቀዬውን ለቆ ወደ ጫካና ገጠር ሸሽቶ እንደነበርም አስታውሰዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ ወሎ መካነ ሰላም የፋኖ ሃይል በፈጸመፈው መብረቃዊ ጥቃት ከ19 በላይ የሚሆነውን ገዳይ ቡድን ወደ አስከሬንነት ቀይሮታል ብለዋል።
ወደ 60 የሚሆነው ሃይሉ ቁስለኛ የሆነበት ገዳይ ቡድን በህይወት የተረፈውና ከአካባቢው የፈረጠጠውም ቢሆን በጣት የሚቆጠር መሆኑንም ገልጸዋ።
ወደ አክሬንነት የተቀየረውና ከ19 በላይ አስከሬን የተገኘው አውሮፕላን ማረፊያው አካባቢ ብቻ መሆኑንና ነገር ግን በየአካባቢው የወደቀው አከሬን ሲሰበሰብ ደግሞ ቁጥሩ ከዛም በላይ ነው ሲሉ ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።
የጠላ19ኙ በአየር ማረፊያ ሰፈር ብቻ የተቆጠሩ ናቸው።
ቀበሌ 3 እና ቀበሌ 4 ላይ በሦስት አቅጣጫዎች በተደረገው ውጊያም በገዳዩ ቡድን ላይ የደረሰው ጉዳት መካነ ሰላም ላይ ከደረሰአት በእጅጉ የከፋ ነው ብለዋል።
ይሄ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰአትም ገዳዩ ቡድን አስክሬቹን ወደ አሚጃ ጭኖ አለመጨረሱንም ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በመካነ ሰላምና ሳይንት አይቀጡ ቅጣት የተቀጣው የሰው በላው ቡድን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሃይሉን መቅደላ አምባ ላይ ማስፈሩን ጠቁመዋል።