ኬንያ የገቡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በመኪና አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ።

በህገወጥ መንገድ ወደ ኬንያ የገቡ 3 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በመኪና አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ።

በህገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ወደ ኬንያ የገቡ 3 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በኬንያ ሜሩ አውራጃ ውስጥ በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ማለፉን የኬንያው ዘ ስታር ጋዜጣ ዘግቧል።

አደጋው የሰው አዘዋዋሪዎቹ 10 ኢትዮጵያውያንን በፕሮቦክስ መኪና ጭነው ሲጓዙ ተሽከርካሪያቸው ከሌላ መኪና ጋር በመጋጨቱ የተከሰተ ሲሆን 8 ስደተኞች ከባድ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸውና ወደ ሆስፒታል መግባታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ባለፈው ማክሰኞ በሰሜን ምሥራቅ ኬንያ ወደ ናይሮቢ በህገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት በታጠቁ ግለሰቦሶች ታጅበው በሞተር ሳይክል ሲጓዙ የነበሩ ስምንት ኢትዮጵያዊያን በፖሊስ እንደተያዙ ተገልጿል።

በዚሁ እለት ሌሎች 7 ኢትዮጵያዊያን በታጠቁ አጃቢዎቻቸውና በፖሊስ መካከል የተኩስ ልውውጥ ከተደረገ በኋላ እንዳመለጡ ሲገለፅ በመርሳቢት ግዛትም፣ በተመሳሳይ በታጣቁ ግለሰቦች ታጅበው ሲጓዙ የነበሩ 25 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ነው የተባለው።