በመቶዎች የሚቆጠሩ ከአል-ሺፋ ሆስፒታል ሲሸሹ፤ በርካቶች በመጠለያ ጣብያ ውስጥ ተገደሉ

ታማሚዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ቅዳሜ ዕለት ጋዛ ከተማ ከሚገኘው ትልቁ ሆስፒታል ለቀው እየሸሹ ይገኛሉ።
አንዳንድ የሕክምና ባለሙያዎች ሆስፒታሉን ለቀው እንዲወጡ እንደተነገራቸው ቢገልጹም እስራኤል ግን አስተባብላለች።
የተኩስ ድምጽ እየተሰማ ብዙዎች በፈራረሱት መንገዶች ሲጓዙ ታይተዋል።…