የኢትዮጵያዊነት አንደበቴ የተለወጠ ዕለት እኔ አልኖርም – ልዑል አስፋወሰን ዓሥራተ ካሣ፤ የአማራ ሕብረት ግንባር በአውሮፓ የዲፕሎማሲ ተጠሪ

“የአማራ ሕዝባዊ ግንባርን ለመቀላቀል ያበቃኝ ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የተከሰተው ሁኔታ ነው” ልዑል ዶ/ር አስፋወሰን ዓሥራተ ካሣ

ልዑል አስፋወሰን ዓሥራተ ካሣ፤ የኢትዮጵያ የመጨረሻው ንጉሠ ነገሥት ቀዳሚ አፄ ኃይለ ሥላሴ የዘውድ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ልዑል ዓሥራተ ካሣና የልዕልት ዙሪያሽ ወርቅ ልጅ ናቸው። በቅርቡ ስለምን የአማራ ሕብረት ግንባርን ተቀላቅለው በአውሮፓ የግንባሩ የዲፕሎማሲ ተጠሪ ለመሆን ግድ እንደተሰኙ ያስረዳሉ። “የኢትዮጵያዊነት አንደበቴ የተለወጠ ዕለት እኔ አልኖርም”ም ይላሉ።

ከታች የሚገኙትም ሁለቱንም ሊንኮች በመጫን ተከታታይ ሙሉ ቃለ መጠይቁን ያገኛሉ። የቃለመጠይቁ ክሬዲት www.sbs.com.au  ነው።


አንኳሮች
  • የአማራ ሕዝባዊ ግንባርን የመቀላቀል ውሳኔ መነሾ
  • የአማራ ማንነትና ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ ማንነት
  • የዘር ፖለቲካ ላይ የተደራጀ የፖለቲካ ፓርቲ አወቃቀር አሉታዊ ተፅዕኖዎችና የክልከላ አማራጭ መፍትሔዎች

https://www.sbs.com.au/language/amharic/am/podcast-episode/interview-with-prince-dr-asfa-wossen-asrate-kassa-amhara-popular-front/a4rnybn6p

ልዑል አስፋወሰን ዓሥራተ ካሣ – በአውሮፓ የአማራ ሕብረት ግንባር የዲፕሎማሲ ተጠሪ “መለስ ዜናዊና ኢሕአዴግ የጎሳ ብሔረተኝነትን ድል አድራጊ አደረጉ እንጂ፤ ፅንሰ ሃሳቡ የመጣው እ.አ.አ በ1960ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ ጊዜ ነው። ‘መላ ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች እሥር ቤት ሆነች ከማለት ይልቅ፤ የመላ ኢትዮጵያ ሕዝብ እሥር ቤት ውስጥ ነው ያለው’ ብለው ቢነሱ ኖሮ ዛሬ ያለንበት ሁኔታ ላይ አንደርስም ነበር” ይላሉ። ብሪክስን አስመልክተውም አገራዊ፣ አፍሪካዊና ዓለም አቀፋዊ አተያይ አላቸው።


አንኳሮች
  • የሕገ መንግሥታዊ መሻሻል አሥፈላጊነትና ሂደት
  • ጠንካራ መሠረት ላይ የቆመ አገራዊ የተቋም ግንባታ ወሳኝነት
  • የኢትዮጵያ የ2016 የወደፊት ጉዞ አማራጭ መንገዶች
  • የብሪክስ ፖለቲካዊና ምጣኔ ሃብታዊ የዓለም አቀፍ ሚዛን ተገዳዳሪነትና የኢትዮጵያ አባልነት ፋይዳዎች
 “እስከ መገንጠል የሚፈቅደው አንቀፅ 39 ሳይወለድ የሞተ አንቀፅ ነው፤ በማንኛውም ዓለም እንዲህ ያለ አስተሳሰብ የለም” ልዑል አስፋወሰን ዓሥራተ ካሣ

https://www.sbs.com.au/language/amharic/am/podcast-episode/interview-with-prince-dr-asfa-wossen-asrate-kassa-constitutional-reform/oszqdnb4y