‹‹ኦብነግ የታገለው የሶማሌ ህዝብ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ነው›› አቶ አብዱልራህማን መሀዲ – የኦብነግ ዋና ጸሃፊ

‹‹ኦብነግ የታገለው የሶማሌ ህዝብ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ነው›› አቶ አብዱልራህማን መሀዲ – የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ዋና ጸሃፊ

አቶ አብዱልራህማን መሀዲ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) መስራችና ዋና ጸሃፊ ናቸው፡፡ የተወለዱት በሶማሌ ክልል ቀብሪደሃር ሲሆን፤ ሶማሊያ ሞቃዲሾ ከሚገኘው ዩኒቨርሲቲ ማስተርስ ዲግሪ በማኔጅመንትና ቢዝነስ አድሚንስትሬሽን አግኝተዋል፡፡ በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲም ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡

ኦብነግ ከአመሰራረቱ አሁን እስካለበት ደረጃ ያሳለፈውን ሂደት በተመለከተ ከአዲስ ዘመን ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
አዲስ ዘመን፡- የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር መቼና የት በእነማን ተመሰረተ?

አቶ አብዱልራህማን፡- ኦብነግ የተመሰረተው እኤአ በ1984 ነው፡፡ ላለፉት 34 ዓመታት እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ የተመሰረተው ኦጋዴን ውስጥ ነው፡፡ መስራቾቹ ስድስት ናቸው፡፡ እኔ አንዱ ነኝ፡፡ ሶስቱ በህይወት የሉም፡፡ አንደኛው አሁን ብዙ ተሳትፎ አያደርግም፡፡

አዲስ ዘመን፡- ስማቸውን መጥቀስ ይችላሉ ?
አቶ አብዱልራህማን፡- አብዱልራህማን መሀዲ፣ ሼክ ኢብራሂም አብደላ፣ መሀመድ ኢስማኤል፣ አብዱላሂም መሳዲ፣ አብዱራህማን ዩሱፍ መገንና አብዲ ጌሌ ናቸው፡፡
አዲስ ዘመን፡- የተለያዩ ቢሮዎች በሀገር ውስጥና በውጭ አላችሁ?
አቶ አብዱልራህማን፡- በአጠቃላይ በዓለም ላይ ከ60 በላይ ቢሮዎች አሉን፡፡

በአሜሪካ፣ አውሮፓ፣ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በአፍሪካ ውስጥም፡፡ ቀደም ብሎ አዲስ አበባ ውስጥ ሕዋስ ነበረን፡፡ ድርጅታችን በጣም ሰፊ ነው፡፡
ለተጨማሪ ሊነኩን ይጫኑ

‹‹ኦብነግ የታገለው የሶማሌ ህዝብ ራሱን በራሱ  እንዲያስተዳድር ነው›› አቶ አብዱልራህማን መሀዲ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ዋና ጸሃፊ


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE