ፋኖን ትጥቅ አስፈታለሁ በሚል ወደ ሸዋሮቢት ከተማ የገባው የብልፅግና ቡድን መከላከያ ሰራዊት፡ በህዝቡ ላይ ድብደባ እና ዘረፋ እየፈፀመ ነው ተባለ!
መሣሪያ ለመግፈፍ በሚል በከተማዋ ቤት ለቤት እየዞረ ፍተሻ እያካሄደ የሚገኘው የአብይ አህመድ መከላከያ ሰራዊት፡ ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ የጣት ቀለበት እና የአንገት ሀብል እንዲሁም የጆሮ ጌጦችን እየዘረፈ መሆኑን ነው የአማራ ድምፅ ያነጋገራቸው የከተማዋ ኗሪዎች የገለፁት።
በተጨማሪም፡ መሣሪያ ያለውን ሰው ካልጠቆማችሁን እንዲሁም ፋኖ ያለበትን ቦታ ካላሳያችሁን በሚል በተፈፅመባቸው ድብደባ አረጋውያንን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ተነግሯል።
በዚህም እየተፈፅመበት ያለውን ግፍና በደል ለመመከት ነፍጥ አንስቶ ወደ በርሃ የሚወርደው የከተማዋ ኗሪ ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ መምጣቱ ተገልጿል።
የተከፈተበትን ጥቃት ለመመከት ነፍጥ አንስቶ ፋኖዎችን የሚቀላቀለው ሰው ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ያስደነገጠው የዞኑ ብልፅግና ፅ/ቤት፡ ተጨማሪ የገዢው መንግስት ወታደር ወደ ከተማዋ እንዲገባ እያስደረገ መሆኑንም የአማራ ድምፅ ካሰባሰበው መረጃ ለማረጋገጥ ችሏል።
ይሄው የብልፅግና ቡድን ወታደር፡ ከሸዋሮቢት ከተማ በተጨማሪ በሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ፣ ብልባላ፣ ጋሼና፣ እስታይሽ፣ ሀሙሲት፣ ቀበሮ ሜዳ፣ ሳንቃ፣ ጎብየ፣ ሮቢት፣ ቆቦ፣ ዞብል፣ ጋቲራ፣ ተኩለሽ እና በሌሎች አከባቢዎች ላይ ልጆቻችሁ ፋኖ ናቸው ያሉበትን ጠቁሙ በሚል አራስ እናቶችን ጨምሮ አረጋውያን እና ታዳጊዎች ላይ ከባድ ድብደባ እየፈፀመ መሆኑን የአማራ ድምፅ ከሰሞኑ መዘገቡ አይዘነጋም።
ዘገባው የአማራ ድምፅ ነው።