ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ የዋሽንግተን ቡድን አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋራ ጥላቻ ውስጥ እንድትገባ ሠርተዋል ሲሉ ከሠሡ

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈ ወርቂ፣ “የዋሽንግተን ዲሲ ቡድን” ሲሉ በጠሩት አካል ላይ ክሥ አሰሙ። ፕሬዚዳንቱ ወቀሳውን ያሰሙት፣ ዛሬ በተከበረው 32ኛ ዓመት “የነፃነት በዓል” ላይ ነው።

ፕሬዚዳንቱ፣ የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር፣ በኤርትራ እና በሌሎች ሀገራት ላይ ያካሒደዋል ያሉት ፖሊሲ፣ “ለትውልድ የዘለቀ ጠበኛነትን አትርፏል፤” ሲሉ ከሠዋል፡፡ ዝርዝሩን ከዚህ ያገኙታል