በግሪክ የተካሄደዉ ምርጫ እና ዉጤቱ

በግሪክ ባለፈው ዕሁድ የተደረገው ምርጫ በጠቅላይ ሚኒስተር ኪሪያኮ ሚትሶታኪስ የሚመራው የመሀል ቀኙ የአዲሱ ዴሞክርሲ ፓርቲ፤ ከተቃውሚው የግራው ሲሪዛ ፓርቲ በከፍተኛ ልዩነት አሸናፊ ሁኗል። ሆኖም ግን አሽናፊነቱ መንግስት ለመመስረት የሚያስችል አብላጫ የፓርላም ወንበር ያስገኘ ባለመሆኑ ዳግም ምርጫን የሚያስቀር አልሆነም።…