የ35 የአማራ፣ 2 የአፋር ባለሃብቶችና ድርጅቶች የባንክ አካውንት ታገደ
የአማራ ሕዝብ ትግልን ሊደግፉ ይችላሉ በሚል፤ የአማራ ባለሃብቶችን ለማሠርና ንብረታቸውንም ልክ እንደ ትጥቁ ለማስፈታት እንቅስቃሴ መጀመሩን መዘገባችን ይታወቃል።
በኦሮሚያ ብልጽግና ሰዎች የሚመራው የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዛሬ ለሁሉም ባንኮች በጻፈው ደብዳቤ የ35 የአማራ ባለሃብቶች እንዲሁም 2 የአፋር ባለሃብቶች በባንክ ያላቸው ገንዘብ እንዲታገድ ለሁሉም ባንኮች የጻፈው ደብዳቤ ዘ-ሐበሻ እጅ ገብቷል።
ይህም በኦሮሚያ ብልጽግና እና በአማራ ብልጽግና መካከል ያለውን ሽኩቻ አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ የብልጽግና ምንጮች ይናገራሉ። ደብዳቤውን ተመልከቱት፤ ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እመጣለን። በነገራችን ላይ የሞቱ ሰዎችም ጭምር በ እገዳው ስማቸው ተጠቅሷል።
–
ምንጭ ዘሃበሻ
፟


