ከወለጋዉ ቶሌ ቀበሌ ጭፍጨፋ ሸሽተው በሃርቡ መጠለያ ጣቢያ ተጠልለው የሚገጙ ተፈናቃዮችን ግንባር እንዲዘምቱ ግዳጅ ተጣለብን አሉ።

ከወለጋዉ ቶሌ ቀበሌ ጭፍጨፋ ሸሽተው በሃርቡ መጠለያ ጣቢያ ተጠልለው የሚገጙ ተፈናቃዮችን ግንባር እንዲዘምቱ ግዳጅ ተጣለብን አሉ።

ከወለጋዉ ቶሌ ቀበሌ ጭፍጨፋ ሸሽተው በሃርቡ መጠለያ ጣቢያ ተጠልለው የሚገጙ ተፈናቃዮችን ግንባር እንዲዘምቱ ግዳጅ ተጣለባቸው። ተፈናቃዮቸ ለንሥር ብሮድካስት እንደገለፁት የአካባቢው የመንግስት አካላት ከ18 ዓመት እስከ 35 ዓመት ያለ ማንኛውም ሰው ያለ ፍላጎት በግዳጅ መከላከያን እንዲቀላቀሉ ትዛዝ አስተላልፈዋል ብለዋል።

ከልሆነ ግን ምንም አይነት እርዳታ እደማይሰጣቸው እንደተነገራቸው ተፈናቃዮች ተናግረዋል። 10 ሰዎች ተገደው ዘምተዋል፣ እርዳታ ከሰኔ10 እስከ አሁን አልገባላቸዉም ነበር አሁን መስከረም16 & 18 ለያንዳንዳቸው 4000(፬ሺ) ብር ተረድተዋል፣ ይሁን እንጂ ያሁኑ እርዳታ ምን አልባት የስም መለያ ይሆናል ብለው ስላሰቡ ሁሉም ተፈናቃይ አልወሰዱም:: ተፈናቃዮች እርዳታውን ስንቀበል ስም እና እድሜ አይተው ለግዳጅ ይወስዱናል በሚል ስጋት ውስጥ መግባታቸውንና እርዳታ ባለመውሰዳቸውም ያሳደረባቸው ተፅኖ ከባድ እንደሆነ ገልፀዋል::

ከጭፍጨፋ የተረፍት ተፈናቃዩቹ አይደለም ግንባር ለመዝመትና መከላከያን ለመቀላቀል እነሱ እራሳቸው ገና ሃዘኑ ያልወጣላቸው; በሞራልም በስነ ልቦናም የደከሙ ወገኖች ናቸው:: የጤና እና ሌሎች መሰረታዊ ችግሮችም አሉባቸው። የስነልቦና ድጋፍም እላገኙም:: ስለሆነም መንግስት የተፈናቃዮችን ድርብርብ ችግርሮች መቀነስ ሲገባ መከላከያ ካልተቀላቀላችሁ እርዳታ አታገኙም የሚለውን እንቅስቃሴ አቁሞ መጀመሪያ እነሱን ወደነበሩበት እንዲመልስ ጥሪ እናደርጋለን::