በርካቶችን ለሞት፣ ሺዎችን ለመፈናቀል እየዳረገ ያለው ማባሪያ ያላገኘው የሆሮ ጉዱሩው ጥቃት  

በኦሮሚያ ክልል፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በተፈፀሙ ተከታታይ ጥቃቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውን ጥቃቱን ሸሽተው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው የሄዱ የዐይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ። ቢቢሲ ያነጋገራቸውና ጥቃቱን ሸሽተው ወደ አማራ ክልል የሄዱ እና እዚያው ወለጋ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ሰዎች እንደተናገሩት ጥቃቱ ከተጀመረ ሳምንታት ተቆጥረዋል።…