በአዲስ አበባ የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች የሥራ ማቆም አድማ ቀጥሏል

በአዲስ አበባ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩት የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች ከሰኞ ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ እንደመቱ መሆናቸውን ሸገር ራዲዮ ዘግቧል።

የሕዝብ ማመላላሻ አውቶብሶች ሥራ ያቆሙት፣ ከሁለትና ሦስት ወራት በላይ ውል እንደማይታደሰላቸውና ተገቢው ክፍያ በወቅቱ እንደማይተከፈላቸው በመግለጽ ነው። የከተማው አስተዳደር ግን አውቶብሶቹ በዛሬው ዕለት ሥራቸውን እንዲጀምሩ አዟል።

ከቀናት በፊት አስተዳደሩ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ምክንያት በማድረግ ታሪፍ በሚጨምሩ ወይም በነባሩ የስምሪት መስመራቸው የማይቀጥሉ ከሆነ የሥራ ውላቸውን እንደሚያቋርጥ መግለጡ ይታወሳል።