ኢዴፓ በአገራዊ ምክክሩ ላይ ለመሳተፍ እንዲችል የተጣለበት ዕገዳ እንዲነሳለት ጥያቄ አቀረበ

ኢዴፓ በአገራዊ ምክክሩ ላይ ለመሳተፍ እንዲችል የተጣለበት ዕገዳ እንዲነሳለት ጥያቄ አቀረበ

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) በምርጫ ቦርድ የተጣለበትን ዕገዳ እንዲነሳለት የሚያስችል ድጋፍ እንዲያደርግለት ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ከ22 የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መካከል የ17 የኢዴፓ ብሔራዊ ምክር ቤትና ኦዲት ኢንስፔክሽን አባላት ፊርማ ያረፈበት የድጋፍ መጠየቂያ ደብዳቤ ግንቦት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ማስገባቱን የፓርቲው የቀድሞ ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡