በአሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማኀበር የሰላማዊ መፍትሄ ጥሪ አቀረበ።

ደሕንነት እና ፍትሕ ለትግራይ የተሰኘው በአሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማኀበር በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማቆም የሰላማዊ መፍትሄ ጥሪ አቀረበ። የማኀበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ኘሮፌሰር ሙሉጌታ ገብረእግዚአብሄር ለዶይቸ ቬለ እንደገለጹት ማኀበሩ ጥሪውን ያቀረበው ለአፍሪቃ ህብረትና ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፃፈው ግልጽ ደብዳቤ ነው። ስለጉዳዩ አስተያየት የሰጡን በፊኒክስ አሪዞና ነዋሪና የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ የሚከታተሉት ዶክተር ገበየሁ እጅጉ በበኩላቸው ሰላም አስፈላጊ ቢሆንም ህወሓት ሰላም ፈላጊ ድርጅት አይደለም ብለዋል።