ሕወሓት የሚባል ድርጅት ሕልውናው ይቁምና አመራሮቹ በምሕረት ሰደት ወደ ሌላ ሶስተኛ አገር ይዘዋወሩ – ኸርማን ኮኸን

የቀድሞ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ኃላፊ የነበረውና የሕወሓት አፍቃሪው ኸርማን ኮኸን ሕወሓት የሚባል ድርጅት ይክሰምና አመራሮቹ በምሕረት ሰደት ወደ ሌላ ሶስተኛ አገር ይዘዋወሩ ብሏል።

ኸርማን ኮኸን በትዊተር ገጹ ላይ እንዳሰፈረው ኢትዮጵያ ውስጥ ህወሀት የማይቀረውን የሚቀበልበት ጊዜ ነው። የአብይ መንግስት ወታደራዊ የበላይነት አለው። የትግራይን ህዝብ የበለጠ ችግር ለመታደግ ህወሀት ህልውናውን ማቆም አለበት እና አመራሩ ወደ ምህረት ስደት ይሂድ ።