ብልፅግና በአዋጅ ያስቀመጠውን የመደበኛና ኢመደበኛ አደረጃጀትን በስልጠና ሰነዱ ክዶታል

ጌታቸው ሽፈራው  በአዋጅ በመደበኛ አደረጃጀት ማሸነፍ አልችልም ብለህ ባቀረብከው ጥሪ 150 ሺህ በላይ አርሶ አደር፣ በ10 ሽህ የሚቆጠር ፋኖ ዘምቶ ነው ያስቆመው። በአዋጅ ያወጅከውን በማሰልጠኛ ሰነድ ልትሽረው አትችልም!

እውነታው በአዋጅ የተቀመጠ ነው! በአዋጅ ያስቀመጥከውን፣ በስልጠና ሰነድ አትሽረውም!

ብልፅግና በስልጠና ሰነዱ የአማራ ክልልን አስተዋፅኦ ዘልሎታል። እንዲያውም በቀል ሊፈፅሙ ነው ሲል ለትግሬ ወራሪ የሚጠቅም ነውረኛ ፍረጃ አምጥቷል።

መደበኛ አደረጃጀት እያለ ይወቅሳል። ግን ይሄ ሁሉ ነውሩ በአዋጅ ተደንግጎ ተቀምጧል። የአማራ ክልል ጥቅምት 21/2014 ዓ/ም ባወጣው አዋጅ በመደበኛው አደረጃጀት ማሸነፍ እንደማይቻል ጠቅሶ አዋጅ አውጥቷል። የፈደራል መንግስቱም ጥቅምት 23/2014 ዓ/ም ባወጣው አዋጁ በመደበኛ አደረጃጀት ማሸነፍ እንደማይቻል ጠቅሶ አዋጅ አውጥቷል። የሁለቱም አዋጆች መረጃ ከታች ተያይዟል።

በመደበኛ አደረጃጀት ማሸነፍ አይቻልም ሲባል ኢመደበኛ በመሆነ መንገድ ፋኖም ሆነ አርሶ አደር ያሰለፈው አማራ ክልል ብቻ ነው። ሌላ ኢመደበኛ አደረጃጀት ያሰለፈ የለም። በመደበኛ አደረጃጀት ማሸነፍ አይቻልምና አግዙን ሲባል የዘመተው የአማራ ፋኖ እና የአማራ አርሶ አደር ነው። ሌላ አንድ የዘመተ፣ አገር ያዳነ ኢ መደበኛ አደረጃጀት የለም።

ይሄ እውነት በአዋጅ የተቀመጠ ነው። በአዋጅ ያፀደከውን በስልጠና ሰነድ ልትክደው አትችልም። የሁለቱም አዋጆች መረጃ ከታች ተያይዟል።

Image

Image