በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ወደ ፍፃሜ ለማምጣት አሜሪካ ጠንካራ ዲኘሎማሲ እየተከተለች ነው። – የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት

ዩናይትድስቴትስ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት መቋጫ በሚያገኝበት መንገድ ላይ ትኩረት ሰጥታ በመሥራት ላይ መሆኗን አስታወቀች። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ኘራይስ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ወደ ፍፃሜ ለማምጣት አሜሪካ ጠንካራ ዲኘሎማሲ እየተከተለች ነው። በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ያለው ቀውስ ለዩናይትድስቴትስ ፈታኝ ሆኖ መቆየቱን አንድ የአሜሪካ አስተዳደር ከፍተኛ ባለሥልጣን መናገራቸው ተመልክቷል። DW