ኦነግ ሸኔ በምዕራብ ሸዋ የጮቢ ደብረ መድኃኒት መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ በሙሉ አውድሟል።

May be an image of outdoorsየኦነግ ሸኔ ቡድኑ በምዕራብ ሸዋ ዞን ሀገረ ስብከት በጮቢ ወረዳ የጮቢ ደብረ መድኃኒት መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን ሙሉ በሙሉ አውድሟል። የቤተ ክርስቲያኑ ሰበካ ጉባኤ አባላት እንደገለፁት ከሆነ ቤተ እምነቱ ከ150 ዓመት በላይ እድሜ የነበረው ነው። በከተማው የሚኖሩ የእምነቱ ተከታዮች ለዘመናት ይገለገሉበት የነበረ ቅዱስ ስፍራ እንደነበረም ነው ያስረዱት።
ኦነግ ሸኔ ቤተ እምነትን ሳይቀር በማቃጠል አረመኔያዊና ጭካኔ የተሞላበት ተግባር በመፈፀም ፀረ ሕዝብነቱን በግልፅ አሳይቷል ነው ያሉት። የወረዳው አስተዳደርና ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ጀልቀባ ጨቀሳ በበኩላቸው በከተማዋ የሚገኙ የጤና ተቋማት፣ አምቡላንስና ትምህርት ቤት ጨምሮ የሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ የመንግሥት የአስተዳደር ተቋማት ሙሉ በሙሉ በሸኔ የወደሙ ሲሆን የሚሊሻ ቤቶች፣ ሆቴሎች እና አንዳንድ የከተማው ነዋሪ ቤቶችም የአሸባሪው ጥቃት ሰለባ ሆነዋል ብለዋል።
May be an image of outdoors and treeኦነግ ሸኔ በጮቢ ወረዳ ብቻ ከ178 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የመንግስትና የግለሰቦችን ንብረት ማውደሙንም አክለዋል። ኦነግ ሸኔወደ ከተማዋ በድንገት ዘልቆ ከገባ በኋላ በቆበት የአንድ ቀን ውሎ የሕዝብ አገልግሎት ሰጭ የመንግሥት ተቋማትን ሙሉ በሙሉ ወድሟል። ሆኖም አሸባሪውን ከወረዳው ለማስወጣት የአካባቢው የፀጥታ ኃይል የተሳካ ኦፕሬሽን በማድረግና 35 የሽብር ቡድኑ አባላትን በመደምሰስ ወረዳዋን ማስለቀቅ ተችሏል ተብሏል።
በወረዳው የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት እና የጥቃቱ ሰለባዎችን መልሶ ለማቋቋም ስለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ለመጠየቅ ዋልታ የምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎችን በስልክም ሆነ በአካል ለማግኘት ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።
May be an image of outdoors